ፈልግ

አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት  (AFP or licensors)

የአሜሪካ ካቶሊካዊ ጳጳሳት፥ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከዛቻቸው እንዲመለሱ አሳሰቡ

የአሜሪካ ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት ቴህራን የሆርሙዝን የባህር ወሽመጥ እንደገና ለመክፈት ካልተስማማች ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “መላውን የኢራን ስልጣኔ አጠፋለሁ” ሲሉ ካቀረቡት ዛቻ እንዲሪቁ ጥሪ አቅርበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

“ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከጦርነት ማዕበል እንዲመለሱ እና ለሰላም ሲባል ተጨማሪ ሕይወት ከመጥፋቱ በፊት ለፍትሃዊ ስምምነት እንዲደራደሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ” ሲሉ የአሜሪካ ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፖል ኤስ. ኮክሌይ ተናግረዋል።

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፖል ማክሰኞ መጋቢት 29/2018 ዓ. ም. በሰጡት መግለጫ፥ ፕሬዝዳንቱ ማክሰኞ ምሽት ለጭነት መርከቦች መሸጋገሪያ አስፈላጊ የሆነውን የሆርሙዝ ቀጥተኛ መንገድ ለመክፈት ስምምነት ላይ ካልተደረሰ በኢራን ላይ ሙሉ ጥቃት እንደሚሰነዝሩ ማስፈራሪያ መስጠታቸውን አውግዘዋል።

የኢራን የሲቪል መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ማድረግን ጨምሮ እየጨመረ የመጣውን ወታደራዊ እርምጃን በመቃወም በሕማማት ሳምንት እና በብርሃነ ትንሳኤው ወቅት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ ያስተላለፉትን የሰላም ጥሪ ሊቀ ጳጳስ ኮክሌይ በመግለጫቸው ገልጸው፥ ቅዳሜ ሚያዝያ 3/2018 ዓ. ም. ስለ ሰላም በሚፈጸም የጸሎት ሥነ-ሥርዓት ላይ በጎ ፈቃድ ያላቸውን ሰዎች በሙሉ እንዲገኙ ጋብዘዋል።

“ለብጹዓን ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ምእመናን እና እውነተኛ ሰላምን የሚናፍቁ ሰዎች በሙሉ በአውታረ መረብም ሆነ በቁምስናዎች፣ በጸሎት ቤቶች ወይም ጌታ በልባቸው ውስጥ በሚያስቀምጥላቸው ጸጥታ በተሞላበት ሁኔታ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ጋር በመሆን በዓለማችን ሰላም እንዲሰፍን ልዩ ልመናዬን አቀርባለሁ” ሲሉ ሊቀ ጳጳስ ኮክሌይ ተናግረዋል።

 

08 Apr 2026, 16:33