ፈልግ

በሶሪያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ተወካይ በኢድሊብ ግዛት የሚገኙ የክርስቲያን መንደሮችን በጎበኙበት ወቅት በሶሪያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ተወካይ በኢድሊብ ግዛት የሚገኙ የክርስቲያን መንደሮችን በጎበኙበት ወቅት  

በሶሪያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ተወካይ በኢድሊብ ግዛት የሚገኙ የክርስቲያን መንደሮችን ጎበኙ

በሶሪያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ተወካይ ሊቀ ጳጳስ ሉዊጂ ሮቤርቶ ኮና በሃገሪቱ የኢድሊብ ግዛት ውስጥ የሚገኙ ሦስት ታሪካዊ የክርስቲያን መንደሮችን መጎብኘታቸው የተነገረ ሲሆን፥ ለዓመታት የጦርነት፣ የመፈናቀል እና የመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ለደረሰባቸው የአከባቢው ማህበረሰቦች ማበረታቻ መስጠታቸው ተነግሯል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በሶሪያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ተወካይ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ኮና ከዚህን በፊት ከሰኔ 19 እስከ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ የሚገኙትን እና የክርስቲያን መንደር የሆኑ የያኩቢ፣ ክናዬ እና የጋሳኒህ መንደሮችን መጎብኘታቸው የሚታወስ ሲሆን፥ ለዓመታት በተካሄደው ጦርነት፣ መፈናቀል እና በቅርብ ጊዜ ደግሞ አስከፊው የመሬት መንቀጥቀጥ ባደረሰው አደጋ እጅግ የተጎዱት የአከባቢው ማህበረሰብ ለሊቀ ጳጳሱ ሞቅ ያለ አቀባበል ማድረጋቸው ተነግሯል።

ሊቀ ጳጳስ ኮና በጉብኝታቸው ወቅት የአካባቢውን ነዋሪዎች ፍርሃትና ተስፋ ካዳመጡ በኋላ ምዕመናን በአሁኑ ወቅት ባለው እርግጠኛ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን እምነታቸውን በእግዚአብሔር ላይ እንዲጥሉ ማበረታታቸው ተገልጿል።

በኢድሊብ ግዛት ውስጥ በሚገኙት እና በግብርና በሚታወቁ ኮረብታዎች አከባቢዎች የሚገኙት እና ከሶሪያ ጥንታዊ የክርስቲያን ማህበረሰቦች መካከል የአንዱ መኖሪያ የሆኑት እነዚህ መንደሮች በአንድ ወቅት "እስላማዊ መንግሥት" (Islamic State) ተብሎ የሚጠራው ቡድን ጠንካራ ይዞታ ሆነው የነበሩ ሲሆን፥ የሊቀ ጳጳሱ ጉብኝት ሊሳካ የቻለው በቅርብ ዓመታት ውስጥ በተከሰቱት ችግሮች መካከል እምነትን በመጠበቅ እና ተስፋን በማጽናት የአካባቢውን አብያተ ክርስቲያናት ማገልገላቸውን በቀጠሉት የፍራንቺስካዊያን መነኮሳት በስፍራው መገኘት አማካኝነት እንደሆነ ተመላክቷል።

በሶሪያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ተወካዩ በቆይታቸው የትምህርት እና የጤና አጠባበቅ ተነሳሽነቶችን ጨምሮ በገዳማት የሚደገፉ የማህበረሰብ ተቋማትን የጎበኙ ሲሆን፥ ከዚህም በተጨማሪ በግጭቱና በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው ህይወታቸው በእጅጉ የተጎዳውን የአከባቢው ነዋሪዎችን ምስክርነቶች ማዳመጣቸው ተነግሯል።

ተሞክሯቸውን ካካፈሉት መካከል ሃይማኖታዊ ስደትን እና ግጭት ተቋቁመው የሚገኙ እንዲሁም የመኖሪያ ቤቶቻቸውን እና መተዳደሪያቸውን ያጡ ሰዎች እንደሚገኙበት የተነገረ ሲሆን፥ ታሪኮቻቸው የእነዚህን ማህበረሰቦች ስቃይ እና በአባቶቻቸው መሬቶች ላይ ጸንተው ለመቆየት ያላቸውን ቁርጠኝነት ያንፀባርቃሉ ተብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ ሊቀ ጳጳስ ኮና የመንደሮቹን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለማረጋገጥ የስልጠና፣ የሥራ ዕድሎች እና የድጋፍ አስፈላጊነትን የገለጹትን የአከባቢው ወጣቶች ያለባቸውን ስጋቶች ያዳመጡ ሲሆን፥ በውይይቱ ወቅት ከተነሱት ሀሳቦች መካከል ቱሪዝምን ለማበረታታት እና የአካባቢውን ኢኮኖሚ ለማደስ የሚረዱ ባህላዊ ሕንፃዎችን የማደስ አስፈላጊነት እንደተነሳ ተገልጿል።

ሊቀ ጳጳስ ኮና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ከመገናኘታቸው በተጨማሪ ከበርካታ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን፥ ከእነዚህም መካከል ምክትል የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አብደል ቃደር ታሃን፣ የፖለቲካ ጉዳዮች ዋና ሴክሬታሪያት አህመድ ሃሲናት፣ የፓርላማ አባል ሙስጠፋ ሙሳ፣ የአል-ሹጉር አውራጃ ዳይሬክተር አብደል ራዛቅ አሉሽ እና በዳርኩሽ የሚገኘው የአል-ራህማ ሆስፒታል ዳይሬክተር አህመድ ጋንዶር ይገኙበታል ተብሏል። 

16 Jul 2026, 15:31