የቅድስት ሞኒካ ቅሪተ አካልን (አጽም) ወደ ሌላ ቦታ የማዛወር ሂደት
አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ
እ.አ.አ. በ 387 ዓ.ም. የጥንታዊ ክርስትና ዘመን ድንቅ ሰው እና የቅዱስ አውግስጢኖስ እናት የሆነችው ቅድስት ሞኒካ በኦስቲያ ቲቤሪና ከተማ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፏን ታሪኳ የሚገልጽ ሲሆን፥ ለበርካታ ክፍለ ዘመናት መቃብሯ በኦስቲያ ይገኝ እንደነበር እና በዚያን ዘመን ከተገኙ እጅግ ጠቃሚ የአርኪኦሎጂ ማስረጃዎች መካከል አንዱ ደራሲ አኒሲየስ አውቼኒዮ በግጥም መልክ ያዘጋጀው የውዳሴ ጽሁፍ ሲሆን፥ የዚህ ጽሑፍ አንዱ ክፍል እ.አ.አ. በ 1945 ዓ.ም. ኦስቲያ በሚገኘው የአሁኑ የቅዱስ አውሪያ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ባለው ግቢ ውስጥ በሚገኝ የመቃብር ድንጋይ ላይ መገኘቱ እና ድንጋዩ በመካከለኛው ዘመን ለሌላ የቀብር ሥነ ሥርዓት እንደገና ጥቅም ላይ ውሎ እንደነበር እንደሚታመን፣ እንዲሁም ይህ ግኝት የቅድስትዋ መቃብር ትክክለኛና የመጀመሪያ ቦታ በዚያው የመቃብር ስፍራ አካባቢ እንደነበር ማረጋገጡን ታሪካቸው ይናገራል።
የቅዱስ አካል (አጽም) ግኝት
ከቅድስት ሞኒካ መቃብር በተለየ መልኩ፣ የቅዱስ ቅሪተ አካሏ (አጽሟ) ታሪክ ፈጽሞ የተለየ መሆኑ የሚነገር ሲሆን፥ የመቃብሩ ቦታ ተረስቶ በነበረበት እና በ12ኛው ክፍለ ዘመን ከአሩዋይስ የመጡ አንድ ቀኖናዊ ካህን አካሉን ሰርቀው ወደ ፈረንሳይ ወስደዋል ተብሎ የሚነገረው ታሪክ ውድቅ በተደረገበት ወቅት፥ ትክክለኛው የታሪክ ነጥብ የተከሰተው እ.አ.አ. በ 1430 ዓ.ም. ሚያዝያ ወር ላይ ሲሆን፥ የቅዱስ አውገስጢኖስ መነኮሳት ማኅበር አባላት፣ በሰብዓዊነት አቀንቃኙ አንድሪያ ቢግሊያ ድጋፍ እንዲሁም በጳጳሳዊ የተቀደሱ ቅርሶች ጠባቂ ፒዬትሮ አሳልሂት እገዛ፣ የቅድስትዋን ቅዱስ አካል ለመፈለግና መልሶ ለማግኘት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ማርቲን አምስተኛ ፈቃድ ማግኘታቸው ታሪካቸው ይገልፃል።
ይሄንን ተከትሎ አንድ የካህናት ቡድን ወደ ኦስቲያ ተጉዞ፣ እዚያም በአንድ የአካባቢው ነዋሪ መሪነት በቅዱስ አውሪያ ቤተክርስቲያን መሠዊያ ስር ቅሪቶቹ መገኘታቸው ተከትሎ ማህበሩ ቅሪቶቹ ወደ ሮም እንዲዛወሩ መጠየቁ የሚገለጽ ሲሆን፥ እ.አ.አ. በ 1430 ዓ.ም. በሆሳዕና ዕለት የቅድስት ሞኒካ ቅሪተ አካል በተአምራት እና በታላቅ የአምልኮ ሥነ ስርዓት ታጅቦ ሮም የደረሰ ሲሆን፥ ቅሪተ አካሉ መጀመሪያ ላይ በካምፖ ማርዚዮ አካባቢ በሚገኘውና የመጀመሪያው ማህበሩ መቀመጫ በነበረው በቅዱስ ትሪፎኔ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀምጠው እንደነበርና እዚያም ለሃያ ዓመታት በማህበሩ ገዳማዊያት እህቶች ጥበቃ እና እንክብካቤ ሥር መቆየታቸው ይነገራል።
ወደ ቅዱስ አውገስቲን የሮማ ባዚሊካ መዘዋወሩ
የቅርሶቹ የመጨረሻ ማረፊያ ቦታ የተቋቋመው፣ ቅዱስ ቅርሶቹ በክብር ወደ ቅዱስ አውገስጢኖስ ባዚሊካ በተላለፉበት ወቅት እ.አ.አ በ 1455 ዓ.ም. በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ካሊክተስ ሳልሳዊ ዘመን ሲሆን፥ ማፊዮ ቬጂዮ ይሄንን ፕሮጀክት በመምራት የጸሎት ቤቱን እና በኢሳያ ዳ ፒሳ የተቀረጸውን መካነ መቃብር ግንባታ በገንዘብ መርዳቱን፥ ብሎም የመጀመሪያው ሐውልት የቅዱስ ቁርባን ትርጉምን የሚያሳዩ የወርቅ ቅርሶች ያሉት የእምነ በረድ ሥራን ያካተተ መሆኑን እና ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በጸሎት ቤቱ በግራ በኩል ባለው ግድግዳ ላይ እንደሚታይ ተነግሯል።
በዚህ መሠዊያ ዙሪያ በተለይም ከሄርማይቶች ማኅበር ጋር በመንፈሳዊ ሁኔታ የተሳሰሩ ወንድ እና ሴት ምዕመናን የቅዱስ አውገስጢኒዮስ ማህበር ካህናት እና መነኮሳት የአለባበስ ሥርዓት አካል የሆነውን ረጅም የቆዳ ቀበቶ በማሰር ጥልቅ የሆነ የአምልኮ ሥነ ስርዓቶች ይካሄዱ እንደነበር ተገልጿል።
የሟች ቅሪቶቹ እውቅና ማግኘት
እ.አ.አ. ከ 1758 እስከ 1760 ዓ.ም. መካከል በሚገኙ ዓመታት የቅዱስ አውገስቲን ባዚሊካ ውስጠኛ ክፍል በሉዊጂ ቫንቪቴሊ መሪነት ዋና ዋና የተሃድሶ ሥራዎች ተደርጎለት ሌላ ጉልህ የሆነ ምዕራፍ መጀመሩ የተነገረ ሲሆን፥ ይህ ሥራ በአስራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን ከድንጋይ የተሰራ ጥንታዊ የመቃብር ስፍራ ማፍረስን እና የቅድስት ሞኒካን ቅሪተ አካል በአዲስ መሠዊያ ስር ማዛወርን እንደሚያካትት ተነግሯል።
በዚህ ወቅት፣ ማለትም እ.አ.አ. ነሐሴ 1 ቀን 1760 ዓ.ም. ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ኤርባ እና የቅሪተ አካላት ጠባቂው ዶን አጎስቲኖ በተገኙበት የህግ አግባብ እና ክብር በተሞላበት ሁኔታ ቅሪተ አካላቱ ምርመራ እንደተደረገባቸው የተነገረ ሲሆን፥ ይሄንን ተከትሎ የተዘጋጀው ሪፖርት የተከናወኑትን ተግባራት በዝርዝር እንደሚገልጽ ተነግሯል።
ጥንታዊው ከእንጨት የተሰራው የሬሳ ሣጥን ሲከፈት፣ በቦታው የነበሩ ሰዎች በውስጡ ሁለት የተለያዩ ንብርብሮች መኖራቸው ያረጋገጡ ሲሆን፥ በመጀመሪያው ንብርብር ውስጥ በርካታ ቅዱሳን አጥንቶች መገኘታቸው፤ ነገር ግን ወደ ሣጥኑ ታችኛው ክፍል ሲደረስ፣ በአመድ የተሸፈነ እና በቱርኩዋይዝ የድንጋይ ማሰሪያዎች ባጌጠ ውድ ጨርቅ ስር ሁለተኛው ንብርብር መታየቱ፥ እዚያም፣ የአራት ማዕዘን ቅርጽ ባለው ሰሌዳ ላይ በሮማን እና በጎይቲክ ፊደላት ‘ሞኒካ’ የሚል ስም የተቀረጸበት ከነሃስ የተሰራ ሜዳሊያ አጠገብ የቅድስትዋ ቅሪተ አካል ተቀምጦ እንደነበር ተገልጿል።
የቅድስት ሞኒካ ጸሎት ቤትእነዚህ ውድ የሆኑ ቅሪተ አካላት እንደገና ተሰባስበውና በጨርቅ ተጠቅልለው፣ ከውስጥ በናስ በተሸፈነ እና የመታሰቢያ ጽሑፍ በተለጠፈበት አዲስ የነሃስ ሣጥን ውስጥ የተቀመጡ ሲሆን፥ ከዚህም ባሻገር በብፁዕ ካርዲናል ኦዴስካልቺ አማካኝነት በማሸጊያ ሰም መታሸጋቸው፣ መነኮሳቱ እና ካርዲናሉ ለቅድስትዋ በዓል የሚዘመሩትን መዝሙራት እየዘመሩ፣ ሣጥኑን ወደ አዲሱ የቅድስት ሞኒካ ጸሎት ቤት በክብር ማዘዋወራቸው ተነግሯል።
የሬሳ ሣጥኑ አረንጓዴ ቀለም በተቀባ እና በላዩም ላይ “እዚህ የቅድስት እናት ሞኒካ አካል አርፏል” የሚል ጽሑፍ ያለበት የእብነ በረድ ክዳን የተደረገበት ከፔፔሪኖ ድንጋይ በተሠራ ማቆያ ውስጥ የተቀመጠ ሲሆን፤ ከመሠዊያው በላይ በአርቲስት ጆቫኒ ጎታርዲ የተሳለ አዲስ ሥዕል መሰቀሉ እና ይህ ሥዕል 'ማዶና ዴላ ሲንቱራ' የተሰኘችውና የሄርማይታዊያን ማኅበር ሰማያዊ ጠባቂ የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ቅዱስ ቀበቶውን ለአውገስቲን እና ለሞኒካ ስትሰጥ የሚያሳይ ሲሆን፥ ቅዱስ አውገስቲን እና ሞኒካም ህፃኑን አቅፋ በዙፋን ላይ ከተቀመጠችው ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ግራና ቀኝ ቆመው እንደሚታዩ ተነግሯል።
የቅዱስ አውግስጢኖስ ማኅበር ‘እናት’
የቅድስት ሞኒካ ቅዱስ አጽም ወደ ሮም መዛወር፣ በማህበሩ ዘንድ እንደ ልጅ የሚታይ አክብሮትን ከመግለጽ ያለፈ ትርጉም የነበረው መሆኑ የተነገረ ሲሆን፥ የማኅበሩ አባላት የመንፈሳዊ አባታቸው እናት የነበረችውን ቅድስት ሞኒካን አጽም በኃላፊነት በመረከብ፣ ራሳቸውን የሂፖው ቅዱስ አውገስጢኖስ ህጋዊ ወራሾች እና ‘ልጆች’ አድርገው ለመላው ዓለም ማስተዋወቅ እንደቻሉ እና የማኅበሩ ‘ቅድስት እናት’ በመባል የተከበረችው ሞኒካ፣ በተለይም እርሷን ለሚያከብሩት ሰዎች የሴትነት ቅድስና ፍጹም ምሳሌ በመሆን፣ የከፍተኛ መንፈሳዊ አገልግሎት እና አምልኮ ማዕከል መሆኗ ተገልጿል።
በዛሬው ጊዜ በሮማው ባዚሊካ ውስጥ በሚገኘው መቃብሯ ፊት ለፊት የሚቆሙት እና የራሳቸውን ልብ እንደ ስጦታ እንዲያቀርቡ የተጋበዙት
ምዕመናን የጥንቷ ቤተክርስቲያን እናት የሆነችውን ብቻ ሳይሆን፣ ለዘመናት እርሷን የማንነታቸው መሰረት አድርገው የቆጠሩትን፣ በእርሷም ጸሎት እና እንባ አማካይነት ወደ እምነት የመጣው ታላቁ አባት አውገስጢኖስን በመሳሰሉ ሰዎች ውስጥ የጸጋ ምንጭ ሆኖ ያገኙትን መንፈሳዊ ቤተሰብ ሕያው ልብ ያከብራሉ ተብሏል።