ፈልግ

በአውሮፓ ሕብረት ክልል ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቶያን ጳጳሳት ጉባሄ  አባላት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት በአውሮፓ ሕብረት ክልል ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቶያን ጳጳሳት ጉባሄ አባላት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በአውሮፓ አህጉር ውስጥ የሚገኙ ጳጳሳት የሰላምን ዓላማ እንዲያራምዱ ጥሪ አቀረቡ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅርቡ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ማሪያኖ ክሮሺያታን አዲሱ በአውሮፓ ሕብረት ክልል ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቶያን ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን አስመልክቶ በቫቲካን ባደረጉት ንግግር ጳጳሳቱ የሰላምን ዓላማ እንዲያራምዱ ጋብዘዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በአውሮፓ ኅብረት ቀጠና ውስጥ ለሚገኙ ጳጳሳት እና ከአዲሱ ሊቀ ጳጳስ ማሪያኖ ክሮሺያታ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት “ሁለቱ የአውሮፓ መስራች አባቶች ሁለቱ ታላላቅ ሕልሞች የሆኑትን የአንድነት ህልም እና የሰላም ህልም” እንዳይዘነጉ ጠይቀዋል።

ሐሙስ መጋቢት 15/2015 ዓ.ም ጠዋት ለታዳሚው በይፋ የቀረቡት የአውሮፓ ህብረት የጳጳሳት ጉባሄ ኮሚሽን (COMCE) ልዑካን ረቡዕ በጸደይ ምልአተ ጉባኤያቸው ማጠቃለያ ላይ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ክሮሺያታን የመረጡት የልዑካን ቡድን አባላት ነበሩ። በዚሁ አጋጣሚ አራት ምክትል ፕሬዚዳንቶችም ተመርጠዋል፡ ጳጳስ አንትዋን ሄሩርድ፣ ኑኖ ብራስ ዳ ሲልቫ ማርቲንስ፣ ሪማንታስ ኖርቪላ እና ቸስላው ኮዞን በምክትል ፕሬዚዳንትነት ተመርጠዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በአውሮፓ ህብረት ቀጠና ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት በአውሮፓ ፕሮጀክት አነሳሽ እሴቶች ማለትም አንድነት እና ሰላም በተገለፀው አድማስ ላይ ዓይኖቻቸውን እንዲተክሉ ጋብዘዋል።

በልዩነት ውስጥ አንድነት

በመጀመሪያው ነጥብ ላይ ቅዱስ አባታችን እንደተናገሩት ከሆነ የአውሮፓ አንድነት “አንድ ወጥ የሆነ አንድነት ሊሆን እንደማይችል፣ ነገር ግን “በግለሰብ ደረጃ፣ የሕዝቦችን እና ባህሎችን ልዩ ባህሪያትን የሚያከብር እና የሚያስከብር ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችን እና ባህሎቻቸውን በማስታወስ የአውሮፓን ብልጽግና “ከተለያዩ የአስተሳሰብ ምንጮችና የታሪክ ተሞክሮዎች ውህደት” ጋር አመሳስሎታል።

“እንደ ወንዝ በወንዙ ውስጥ ይኖራል። ገባር ወንዞች ከተዳከሙ ወይም ከተዘጉ ወንዙ በሙሉ ይሠቃያል እናም ጥንካሬውን ያጣል” ብለዋል።

አውሮፓ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በንግግራቸው ወቅት እንዳሉት ከሆነ "በእውነቱ ህብረት ካላት ብቻ ነው የወደፊት ሕልሟ እውን የሚሆነው" በማለት የየራሳቸው ባህሪያት ያላቸው አገሮች ውህደት ብቻ አይደለም ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

ፈተናው በልዩነት ውስጥ ያለ አንድነት ነው ሲሉም አክለዋል። እናም የሰለጠኑ ባለሞያዎች ስብስብ አሠራር የዘለለ ጠንካራ ተነሳሽነት ካለ እና ሰዎችን ማበረታታት እና አዲስ ትውልድን በጋራ ፕሮጀክት ግንባታ ውስጥ መሳብ የሚችል ከሆነ ሕብረቱን አስጠብቆ መጓዝ ይቻላል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የአውሮፓ ኅብረት ከተመሠረተ በኋላ ምን ያህል ለውጥ እንዳለ በማሰላሰል፣ ቤተ ክርስቲያን “የዘመኑን ምልክቶች እያነበበች፣ የአውሮፓን ፕሮጀክት በዛሬው ታሪክ እንዴት እንደሚተረጉሙ የሚያውቁ ሰዎችን የማሰልጠን ኃላፊነት አለባት” ብለዋል።

ለሰላም የጋራ ቁርጠኝነት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሰላም ህልምን በሚመለከት “በዛሬው ታሪክ ውስጥ ለሰላም አገልግሎት አውሮፓ ህብረት የመፍጠር ህልም ያልቸው ወንዶች እና ሴቶች ያስፈልጉናል” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ አህጉሪቱ በታሪኳ ረጅሙን የሰላም ጊዜ ያሳለፈችበትን ሁኔታ አስታውሰዋል። በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተከሰቱትን በርካታ ጦርነቶች አንዳንዶቹን “ለዓመታት የቆዩ” በመሆናቸው እነዚህን ጦርነቶችን እስከ አሁን ድረስ ማስቆም ባለመቻላችን “አንድ ሰው ስለ ሦስተኛው የዓለም ጦርነት ሊናገር ይችላል” ሲል ነቅፏል። ይህንን ሐሳባቸውን ቅዱስነታቸው ሲያጠናክሩ "የዩክሬን ጦርነት ቀርቧል፣ እናም የአውሮፓን ሰላም አንቀጥቅጧል" በማለት በዋቢነት በአሁኑ ወቅት በዩክሬይን እና በራሻ መካከል እየተካሄደ ስላለው ጦርነት የገለጹ ሲሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አጎራባች ሀገራት ስደተኞችን ለመቀበል የተቻላቸውን ሁሉ እንዳደረጉ እና ሁሉም የአውሮፓ ህዝቦች ከዩክሬን ህዝብ ጋር በመተባበር መሳተፋቸውን አረጋግጠዋል ።

የተለያዩ የአውሮፓ ኅብረት አገሮች “በተለያዩ ጥምረቶች፣ ፍላጎቶች፣ ስላታዊ በሆነ መንገድ ፣ ወደ አንድ ፕሮጀክት ለማሰባሰብ አስቸጋሪ በሆኑ የተለያዩ ኃይሎች ውስጥ መሣተፋቸውን” ከሚያመልክተው እውነታ የመነጨውን ውስብስብነት በመገንዘብ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት “ጦርነት ለግጭቶች መፍትሄ ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም” የሚለውን አንድ መርህ በግልፅ እና በቆራጥነት ሁሉም ሊጋራው ይገባል ብሏል።

"ጦርነት ለግጭቶች መፍትሄ ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም እናም ከእንግዲህ እንዲህ መሆን የለበትም" በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “የዛሬው አውሮፓ አገሮች ይህንን ሥነ-ምግባራዊ-ፖለቲካዊ መርህ የማይጋሩ ከሆነ፣ ከዋናው ህልም ወጥተዋል ማለት ነው። በአንፃሩ የሚካፈሉት ከሆነ ታሪካዊ ሁኔታው ​​በሚጠይቀው ጥረትና ውስብስብነት ተግባራዊ ለማድረግ ራሳቸውን መስጠት አለባቸው” ብለዋል።

ጦርነት የፖለቲካ እና የሰብአዊነት ውድቀት ነው ።

በአብያተ ክርስቲያናት እና በተቋማት መካከል ድልድይ ሆኖ ማገልገል እንደ ሚገባ የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “በአውሮፓ ውስጥ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት እና በኅብረቱ ተቋማት መካከል ድልድይ” የመሆን ኃላፊነታቸውን ለተሰብሳቢዎቹ በማሳሰብ ደምድመዋል።

“እናንተ በሚስዮናዊ ፍቅር የግንኙነቶች፣ የመገናኘት፣ የውይይት ገንቢዎች ናችሁ። ይህ ደግሞ አስቀድሞ ለሰላም አገልግሎት እየሰራ ነው። ግን በቂ አይደለም” ብሏል።

“ትንቢትን ይጠይቃል፣ አርቆ ማሰብን ይጠይቃል፣ የሰላምን ጉዳይ ለማራመድ ፈጠራን ይጠይቃል። በዚህ የሰላም የግንባታ ቦታ ውስጥ ሁለቱም የመልካም ሐሳብ ነዳፊዎች እና የስነ ጥበብ ባለሙያዎች ያስፈልጋሉ፤ እኔ ግን እላለሁ እውነተኛ ሰላም ለማስፈን ሁለቱም መሐንዲስ እና የእጅ ጥበብ ባለሙያ መሆን አለባቸው” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

24 March 2023, 10:37