ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ በቆጵሮስ እና በግሪክ የሚገኙ ስደተኞችን በጎበኟቸው ወቅት ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ በቆጵሮስ እና በግሪክ የሚገኙ ስደተኞችን በጎበኟቸው ወቅት  (Vatican Media)

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ የመሰደድ ወይም በአገር የመቆየት ምርጫ የሰዎች መሠረታዊ መብት ነው!” አሉ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ እሑድ መስከረም 13/2016 ዓ. ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡት ምዕመናን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ካቀረቡ በኋላ ንግግር አድርገዋል። ቅዱስነታቸው ከጸሎት ሥነ ሥርዓቱ ቀጥለው ባደረጉት ንግግር፥ ሰዎች በተወለዱበት አገር የመቆየት ሆነ ለቅቀው የመውጣት ነፃነት እንዲጠበቅላቸው እንዲሁም በሄዱበት አገርም መልካም አቀባበልን ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን ደግመው ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትናንት እሑድ መስከረም 13/2016 ዓ. ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተገኙት ምመናን ጋር በኅብረት የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ካቀረቡ በኋላ ዕለቱ ዓለም አቀፍ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ቀን እንደ ነበር በማስታወስ አክብረው ውለዋል። ዕለቱን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክታቸው፥ ሰዎች በተወለዱበት አገር የመቆየትም ሆነ ለቅቆ የመውጣት ነፃነት እንዲሁም በሚሄዱበት አገርም መልካም አቀባበልን የማግኘት መሠረታዊ አስፈላጊነትን አስገንዝበዋል።

የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ቀን መሪ ርዕሥ፥ “የመሰደድ ወይም በአገር የመቆየት ነጻነት” የሚል ሲሆን፥ ዓላማውም ስደት ተስፋን በመቁረጥ የሚወሰድ እርምጃ ሳይሆን፥ በፈቃደኝነት በምርጫ የሚደረግ መሆኑን ለማሳየ እንደሆነ ታውቋል።

የመሰደድ መሠረታዊ ሰብአዊ መብት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትናንት እሑድ መስከረም 13/2016 ዓ. ም. ባደረጉት ንግግር፥ መሰደድ የሰው ልጅ መሠረታዊ መብት እንደሆነ አስገንዝበው፥ ለብዙዎች ግን በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ምንያት ተገድደው የሚፈጽሙት ድርጊት ሆኗል” በማለት አስረድተዋል። ቅዱስነታቸው ከዚህ ጋር አያይዘው፥ ሰዎች በትውልድ አገራቸው ውስጥ የተከበረ እና የተሟላ ሕይወት እንዲኖሩ የሚያደርግ እኩል መብት መኖር አስፈላጊነትንም ተናግረዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በንግግራቸው፥ “አሁን ያለው ዓለም አቀፋዊ ገጽታ በስቃይ፣ በግጭት እና በአየር ንብረት ቀውስ አስከፊ ተፅዕኖዎች የተጠቃ በመሆኑ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች መኖሪያቸውን ጥለው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲሰደዱ አስገድዷቸዋል” ብለዋል። ይህንን አስከፊ እውነታ አምነው ግለሰቦች እና አገራት በሙሉ በአንድነት እና በመተሳሰብ እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል። በመደጋገፍ እና በማጽናናት ወደ ደጃቸው የሚመጡ ስደተኞችን ለመቀበል፣ ለመደገፍ፣ ለመምራት እና ከሌላው የማኅበረሰ ክፍል ጋር ለማዋሃድ የተዘጋጁ ብቻ ሳይሆን፥ ጉጉት ያላቸው ማኅበረሰቦችን ለመፍጠር ጥረት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ከማርሴ ከተማ የሚስተጋቡ መልዕክቶች

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የደቡብ ፈረንሳይ ከተማ ማርሴ ውስጥ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት የሜዲቴራኒያን አካባቢ አገራት ከመስከረም 6-12/2016 ዓ. ም. ድረስ ያካሄዱትን ስብሰባ በማስታወስ፥ ስብሰባው ግለሰቦች እና አገራት በሰው ልጆች ላይ የሚደርሰውን አስከፊ የስደት ቀውስ በመገንዘብ ሁሉም እርስ በርስ በመተሳሰብ እንዲተባበሩ ጥሪ መቅረቡን ገልጸዋል።

የደቡብ ፈረንሳይ ከተማ በሆነች ማርሴ መስከረም 11 እና 12/ 2016 ዓ. ም. ባደረጉት የሁለት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት ቅዱስነታቸው፥ ስደትን በተመለከተ በተለይም በሜዲትራኒያን አገራት አካባቢ ባሉት ተግዳሮቶች እና ዕድሎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። በጉባዔው ወቅትም፥ የሜዲትራኒያ አካባቢ በታሪክ የባህልና የሥልጣኔ መፍለቂያ ነበር" ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በማርሴ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት፥ "በእነዚህ ፈታኝ ጊዜያት እርስ በርስ በመተሳሰብ የአንድነት መንፈስን በመቀበል፣ ጥገኝነት የሚጠይቁትን ለመቀበል ልባችንን እና አእምሮአችንን እንክፈት" ብለዋል። በጦርነት አደጋ ለሚሰቃዩ የዩክሬይን ሕዝቦች ሰላም እንዲወርድ ተማጽነዋል። ቅዱስነታቸው ከዚህም በተጨማሪ የሜዲትራኒያን አካባቢ አገራት የፈረንሳይ ከተማ በሆነች ማርሴይ ውስጥ በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ ለመገኝት ወደ ሥፍራው ለሚያደርጉት የሁለት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት የምዕመናንን የጸሎት ዕርዳታ ጠይቀዋል።

 

 

25 September 2023, 17:04