ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ 'ጌታ እኛን ይቅር ለማለት በፍጹም አይታክትም' ማለታቸው ተገለጸ!
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮ የጌታ እራትን በእስር ቤት የማክበር ልማዳቸውን በመቀጠል በጸሎተ ሐሙስ በመጋቢት 19/2016 ዓ.ም ከሰአት በኋላ በሮም የሚገኘውን የረቢቢያ ማረሚያ ቤት የሴቶች ክፍል ጎብኝተዋል።
በእስር ቤቱ ውጭ በሚገኝ አካባቢ ለተሰበሰቡ በደርዘን የሚቆጠሩ እስረኞች፣ ጠባቂዎች፣ ቀሳውስት እና ባለስልጣናት መስዋዕተ ቅዳሴን እና እግር የማጠብ መንፈሳዊ ስነ ስርዓትን መርተዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሕማማቱ ዋዜማ ላይ በኢየሱስ የመጨረሻ እራት ላይ ባደረጉት አጭር ንግግር ላይ አተኩረው ነበር።
የአገልግሎት መንገድ
በመጨረሻው እራት ጊዜ ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ለማጠብ ራሱን አዋረደ። ይህን በማድረጉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንዳሉት ከሆነ “‘ለማገልገል እንጂ ልገለገል አልመጣሁም’ ሲል ኢየሱስ የተናገረው ምን ማለቱ እንደሆነ እንድንገነዘብ ያደርጉናል” ሲሉ አብራርተዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ “የአገልግሎትን መንገድ ያስተምረናል” ያሉት ይህ የትሕትና ምልክት ነው።
ኢየሱስ ሁል ጊዜ ይቅር ይላል።
ከዚያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በስግብግብነትና በራስ ወዳድነት ተነሳስተው ስለ ይሁዳ ክህደት ተናገሩ። የይሁዳ ታሪክ፣ ጳጳሱ እንዳሉት፣ ጌታ ሁል ጊዜ ኃጢአታችንን ይቅር እንደሚለን እና “ይቅርታን እንድንለምን ብቻ ነው የሚጠይቀን” ብሏል።
በእርግጥም “ኢየሱስ ይቅር ለማለት አይታክትም፤ ይቅርታን መጠየቅ የምንታክተው እና የምንደክመው እኛ ነን” ሲሉ አጥብቆ ተናግረዋል።
"ሁላችንም ትንሽም ሆነ ትልቅ ውድቀቶች አሉን - ሁሉም ሰው የራሱ ታሪክ አለው። ነገር ግን ጌታ ሁል ጊዜ ይጠብቀናል፣ እጆቹ ክፍት ሆነው እርሱ ይጠብቀናል፣ እና ይቅር ለማለት የማይታክት አምላክ ነው” ብለዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በማጠቃለያው ላይ ምእመናን ይቅርታውን መለመን እንዳንታክት እና በማገልገል ጥሪ እንድናድግ ጸጋውን እንዲሰጣቸው ጌታን እንዲጠይቁ አሳስበዋል።
የአስራ ሁለት እስረኞች እግር ማጠብ
ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከስብከታቸው በኋላ የ12 ሴት እስረኞችን እግር በማጠብ በቅዳሴው ማጠቃለያ ላይ ከማረሚያ ቤቱ እስረኞች እና ሰራተኞች ጋር በመገናኘት በተቋሙ ውስጥ የተመረቱ የእርሻ ምርቶች፣ የጎበኙ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለረቢቢያ ማረምያ ቤት ዳይሬክተር እና ሰራተኞች የቅድስት ማርያም ምስል በስጦታነት እንዳበረከቱም ተገልጿል።