ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የሚታከሙበት የጂሜል ሆስፒታል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የሚታከሙበት የጂሜል ሆስፒታል  (ANSA)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከአሁን በኋላ የአየር መተንፈሻ መሣርያ እንደ ማያስፈልጋቸው ተገልጿል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በምሽት የመተንፈሻ ድጋፍ የምያደርግ መሣርያ አላስፈላጋቸውም፣ በተጨማሪም በቀን ውስጥ ከፍተኛ ፍሰት ያለው የኦክስጂን ሕክምና እንደማያስፈልጋቸው የቅድስት መንበር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ረቡዕ አመሻሽ ላይ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም የቅድስት መንበር የዜና አውታር ጽ/ቤት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮን የጤና ሁኔታ አስመልክቶ የሚከተለውን መረጃ አውጥቷል።

"የቅዱስ አባታችን የጤና ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱ ተረጋግጧል። ቅዱስ አባታችን አጋዥ የመተንፈሻ መሣርያ መጠቀም አቁመዋል፣ እንዲሁም ከፍተኛ ፍሰት ያለው የኦክስጂን ሕክምና የሚያስፈልጋቸው አይደለም" ሲል የቅዱስነታቸውን የጤና ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ ያወጣ ሲሆን "ዛሬ ጠዋት፣ በቅዱስ ዮሴፍ ክብረ በዓል ላይ ቅዱስነታቸው መስዋዕተ ቅዳሴ ተሳትፈዋል" ሲል መገለጫው አክሎ ገልጿል።

የጳጳሱ ሐኪሞች የሳንባ ምች በሽታ ምንም እንኳን ሙሉ በሙሉ ባይወገድም ቁጥጥር እየተደረገበት ነው ብለዋል። የእርሳቸው የጤና ሁኔታ  ትንታኔ ውጤቶች በተለመደው ክልል ውስጥ ናቸው፣ እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከትኩሳት በሽታ ነጻ ሆነዋል ብለዋል።

ቀኑን በህክምና፣ በጸሎት እና አንዳንድ ስራዎችን በመሥራት አሳልፏል። በዐብይ ጾም የመጨረሻው ሳምንት ላይ ማለትም በቅዱስ ሳምንት የአምልኮ ሥርዓቶችን ማን እንደሚመራ እስካሁን ውሳኔ አልተደረገም።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሁኔታ የተረጋጋ በመሆኑ የሚቀጥለው የሕክምና ውጤት ከሚቀጥለው ሳምንት ቀደም ብሎ ይጠበቃል። የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት አርብ ለጋዜጠኞች አንዳንድ አጠቃላይ መረጃዎችን ይሰጣል፣  በመጪው ሰኞ ደግሞ በድጋሚ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከየካቲት 07/2017 ዓ.ም ጀምሮ በሁለትዮሽ የሳምባ ምች በሽታ ተጠቅተው በሮም ጂሜሊ በመባል በሚታወቀው ሆስፒታል ሲታከሙ ቆይተዋል።

 

20 Mar 2025, 13:53