ፈልግ

የእስራኤል እና የኢራን ግጭት የእስራኤል እና የኢራን ግጭት   (AFP or licensors)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፡- ‘የሰው ልጅ ይጮኻል፣ ስለ ሰላም ይለምናል’ ማለታቸው ተገለ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በጦርነት በተለይም በመካከለኛው ምሥራቅ እየደረሰ ያለው አሳዛኝ ሁኔታ እንዲያበቃ ተማጽነዋል፣ ጦርነት ዘላቂ መፍትሄ ሳይሰጥ ችግሮችን በማባባስ እና ጥልቅ ቁስሎችን እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እሁድ እለት ሰኔ 15/2017 ዓ.ም የመልአከ ሰላም ጸሎት ካደረጉ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት  "ከመካከለኛው ምስራቅ በተለይም ከኢራን አስደንጋጭ ዜና መምጣቱን ቀጥሏል" ብለዋል።

የቅዱስ አባታችን ቃል ትኩረቱን ያደርገው እስራኤል እና ኢራን እርስበርስ በግዛታቸው ላይ ጥቃት ሲሰነዛዘሩ የአሜሪካ ቦምቦች በኢራን የኒውክሌር ቦታዎችን ከመቱ ከጥቂት ሰአታት በኋላ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል “እስራኤልንና ፍልስጤምን በሚያካትት በዚህ አስደናቂ ሁኔታ በሕዝቡ በተለይም በጋዛ እና በሌሎች ግዛቶች ላይ የሚደርሰው የዕለት ተዕለት ስቃይ በቂ የሆነ ሰብዓዊ ዕርዳታ የሚያስፈልገው አጣዳፊ እየሆነ ቢመጣም የመዘንጋት አደጋ አለው ብለዋል።

"ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የሰው ልጅ ይጮኻል እናም ስለ ሰላም ይለምናል" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሰላም ጩኸት ኃላፊነትን እና ምክንያታዊነትን የሚጠይቅ በመሆኑ በጦር መሣሪያ ጩኸት ወይም ግጭት በሚቀሰቅሱ የአጻጻፍ ቃላቶች መስጠም የለበትም ብለዋል ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እያንዳንዱ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አባል “ጦርነቱ ወደማይጠገን ጥልቅ ገደል ከመግባቱ በፊት ለማስቆም የሞራል ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

የሰው ልጅ ክብር አደጋ ላይ ሲወድቅ ከምንም ዓይነት ግጭት የራቀ አይደለም ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ጦርነት ችግሮችን አይፈታም" ብለዋል። "በተቃራኒው እነርሱን ማለትም ችግሮችን ያጠናክራል፣ እንዲሁም በሰዎች ታሪክ ውስጥ ጥልቅ ቁስሎችን ያስከትላል - ትውልዶችን ለመፈወስ የሚፈጅ ቁስሎች። የትኛውም ወታደራዊ ድል የእናትን ህመም፣ የሕፃን ፍርሃት ወይም የተሰረቀ የወደፊት ሕይወት ማካካሻ ሊሆን አይችልም ብለዋል።

በማጠቃለያውም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የጦር መሣሪያ አፈሙዝ ዝም እንደሚል ያላቸውን ተስፋ ገለጸዋል።

“ዲፕሎማሲ የጦር መሳሪያዎቹን ጸጥ ያድርግ!” በማለት ተናግሯል። “ሀገሮች የወደፊት ህይወታቸውን በሰላም ግንባታ እንጂ በአመፅና በደም አፋሳሽ ግጭቶች እንዲቀርጹ አያድርጉ!” ብለው ከተናገሩ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእልክታቸውን አጠናቀዋል።

23 Jun 2025, 13:13