ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ሊዮ 14ኛ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ሊዮ 14ኛ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት   (ANSA)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ የኮሙኒኬሽን መንገዶች ወደ ደህንነት እንጂ ወደ ጣፋት ሊመሩን አይገባም ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ረቡዕ እለት ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ የዲጂታል ሚሲዮናውያን እና የካቶሊክ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ወጣቶች የኢዩቤሊዩ ተሳታፊዎች ባደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የኮሙኒኬሽን ወይም የመገናኛ ዘዴዎች እና መንገዶች የሰው ልጆችን ወደ ድህንነት መንገድ መምራት እንጂ ወደ ጥፋት ሊመሩ እንደማይገባ ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በኢየሱስ ይፋዊ ህይወት ላይ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ዘወትር ረቡዕ እለት በተከታታይ  እያደረጉ የነበረውን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሲያጠናቅቁ ቅዱስነታቸው እንደ ተናገሩት የኢየሱስ ይፋዊ ሕይወት በግጭቶች፣ በምሳሌዎች እና በፈውሶች ተለይተው ይታወቃሉ ብለዋል።

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት የዲጂታል ሚሲዮናውያን እና የካቶሊክ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ወጣቶች የኢዩቤሊዩ ተሳታፊዎች እና ምእመናን ንግግር ያደረጉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሁሉንም ሰው ትኩረት በአሁናዊ ሁኔታ ላይ እንዲያተኩር ቅዱስነታቸው የተማጸኑ ሲሆን “አሁን እየኖርንበት ያለነው ዘመን ፈውስ ያስፈልገዋል” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በዛሬው ጊዜ ያለው ዓለም የሰውን ልጅ ክብር በእጅጉ የሚጎዳ “የዓመፅና የጥላቻ አየር” ያለበት እንደሆነ ገልጿል። ሕብረተሰባችን እየተባባሰ በመጣ ህመም ውስጥ ይገኛል፣ ከመነጠል የተነሳ ቢቻ ሳይሆን   ከመጠን በላይ በሆነ ሸክም ጭምር የመጣ  ነው ያሉ ሲሆን “ምንም እንኳን በበይነ መረብ አማካይነት ከመጠን በላይ የተገናኘን ቢመስለንም ቅሉ፣ ከመጥን በላይ በሆኑ ምስሎች፣ አንዳንዴ በውሸት ወይም በተዛቡ ዜናዎች የተነሳ ከፍተኛ የሆኑ ሸክሞች በአእምሮዋችን ውስጥ ተሸክመን እንገኛለን" ብሏል። ማህበራዊ ሚዲያዎች ብዙ ከመጠን በላይ በሆኑ ዜናዎች እና መልእክቶች የተነሳ ግራ እንድንጋባ በሚያደርግ ስሜታዊ ወደ ሆነ 'አግበስባሽነት" እንድናመራ ሊያደርግ ስለሚችል በዚህ ረገድ መጠንቀቅ ይኖርብናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በዚህ የተነሳ ብዙዎች ራሳቸውን ለመዝጋት ይፈተናሉ ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የተናገሩ ሲሆን “ምንም እንኳን ምንም ነገር እንዳይሰማን ሊያደርገን ይችል ይሆናል፣ ”ቃላቶቹ ራሳቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ ደካማ እየሆኑ መጥተዋል ብለዋል።

ከሰዎች ጋር አብራ የምትጓዝ ቤተ ክርስቲያን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ "ከዚያም ኢየሱስ ከጢሮስ አገር ተነሥቶ፥ በሲዶና በኩል አድርጎ ዐሥር ከተማ በተባለው አገር በማለፍ ወደ ገሊላ ባሕር መጣ። በዚያም ሰዎች ደንቆሮና ዲዳ የሆነ አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፤ እጁንም እንዲጭንበት ለመኑት። ኢየሱስም ሰውየውን ከሕዝቡ ለይቶ ከወሰደው በኋላ፥ ጣቶቹን በጆሮው አስገባ፤ ከዚያም እንትፍ ብሎ የሰውየውን ምላስ ዳሰሰ። ወደ ሰማይም ተመልክቶ ቃተተና፥ “ኤፋታህ” አለው፤ ይኸውም፥ “ተከፈት” ማለት ነው። ወዲያውም ጆሮዎቹ ተከፈቱ፤ ምላሱም ተፈቶ አጥርቶ መናገር ጀመረ። ኢየሱስ ይህን ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው፤ ሆኖም እርሱ እንዳይናገሩ ባዘዛቸውም መጠን፥ ነገሩን አስፍተው አወሩት። ሕዝቡም ከመጠን በላይ በመደነቅ፥ “ያደረገው ሁሉ ጥሩ ነው፤ ደንቆሮዎች እንዲሰሙ፥ ድዳዎች እንዲናገሩ እንኳን አድርጓል” (ማርቆስ 7፡31-37) በሚለው ኢየሱስ ደንቆሮና ዲዳ የነበረን ሰው መፈወሱን በሚገልጸው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ትኩረታቸውን ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ሰውየው ለራሱ ፈውስ አልጠየቀም ነበር፣ ሌሎች ሰዎች ናቸው ሰውዬውን ወደ ኢየሱስ ያመጡት ሲሉ ተናግረዋል። ነገር ግን ሌሎች ሰዎች ወደ ኢየሱስ ያመጡታል። እነዚህ ሁኔታዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደ ተናገሩት ከሆነ ከሌሎች ሰዎች ጋር አብረው የሚሄዱ፣ በተለይም ድምፃቸውን ወይም የማዳመጥ ችሎታቸውን ሲያጡ፣ ቤተ ክርስቲያን የምታደርገውን ተግባር እና የምታሳየውን አብነት ሊገልጹ ይችላሉ ማለታቸው ተገልጿል።

ከኢየሱስ ጋር ከተገናኘ በኋላ ሰውየው እንደገና መናገር ጀመረ፣ እናም ይህ ዝርዝር ጥልቅ እውነትን ያሳያል ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ። ምናልባት እንዴት እንደሚናገር ስለማያውቅ ወይም በቂ ሆኖ ስላልተሰማው ዝም ብሎ ሊሆን ይችላል ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ምን ያህል ጊዜ ሰዎች እኛን ጠየቁ፣ እኛ መናገር ያቆምነው በተሳሳተ መንገድ ስለተሰማን ነው ወይ? ብለን ራሳችንን ልንጠይቅ ይገባል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ይፋዊ ሕይወት ዙሪያ ላይ የጀመሩትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ስያጠቃልሉ እውነተኛ ግንኙነት ውጤታማ መሆን ብቻ ሳይሆን ስለ ፈውስ፣ በቃላችን ሌሎችን ላለመጉዳት መጠንቀቅ ጭምር እንደሆነ አስታውሰዋል። "በትክክል መናገር የጉዞ መጀመሪያ ነው" ብሏል። እናም ይህ ጉዞ በሕማማቱ እና በመስቀሉ በኩል ወደ ራሱ ኢየሱስ ይመራናል ያሉት ቅዱስነታቸው “የመገናኛ መንገዳችንን እንዲፈውስ እና ቤተክርስቲያን እያንዳንዱ ሰው ቃሉን የሚሰማበት፣ የሚፈወስበት እና የድኅነት መልእክተኛ የሆንበት ቦታ እንድትሆን ጌታን እንለምነው” ካሉ በኋላ አስተምህሮዋቸውን አጠናቀዋል።

30 Jul 2025, 16:30