ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የፔሩ ወጣቶች  በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የፔሩ ወጣቶች በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (@Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ ለወጣቶች በሰጡት የቤት ሥራ፡ 'የክርስቶስን የምሥራች ቃል ለሁሉም አዳርሱ' የሚለው ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የፔሩ ወጣቶች "በወጣቶች ኢዮቤልዩ" ላይ ለሚሳተፉት የቤት ሥራ የሰጧቸው ሲሆን፣ ኢዮቤልዩ በፎቶዎች ውስጥ የተቀመጡ ትውስታዎችን ለማድረግ ሳይሆን የክርስቶስን ወንጌል ወደ ቤታችሁ መልሳችሁ ለመውሰድ እና  ለምታገኟቸው ሰዎች ሁሉ የክርስቶስን ፊት እንዲያዩ ለማድረግ ስለሆነ በዚህ ረገድ የቤት ሥራችውን ማከናወን ይኖርባችኋል ማለታቸው ተግልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"ወደ ፔሩ ስትመለሱ፣ ያንን ሀገር በወንጌል ደስታ እና ጥንካሬ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንድታጥለቀለቁ እወዳለሁ" ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ሰኞ ዕለት ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም ከፔሩ በሮም ከተማ በሚከናወነው የወጣቶች ኢዮቤልዩ ላይ ለመሳተፍ ከመጡ ወጣቶች ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የቅዱስ ዓመት በዓልን በጋራ ለማክበር በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ወጣቶችን ለመገናኘት እንደተዘጋጁ "እንደ የተስፋ መንፈሳዊ ነጋዲያን ወይም ተጓዦች" እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት አቀባበል ያደረጉ ሲሆን “እዚህ  እናንተን በማየቴ” እጅግ ደስ ብሎኛል፣ በማለት “በታላቅ መስዋዕትነት እና በትጋት” የረዷቸውን ቤተሰቦቻቸውን እና ብዙ ሰዎችን በማሰብ ይህንን በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ጉዞ እንዲሳካ እንዳደረጋቸው ጳጳሱ ተናግረዋል።

የቤተክርስቲያኗ ቤተሰብ

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በእለቱ ንባብ ላይ ሲያሰላስሉ “እኛም ትንሽ ነን ብቻችንን ግን አይደለንም” ሲሉ የተናገሩ ሲሆን “ጌታ፣” ሁሌም ከእኛ ጋር ነው ሲሉ አረጋግጠዋል፣ የታላቅ ቤተሰብ፣ የቤተክርስቲያን ቤተሰብ እንድንሆን ፈቅዷል። በእሱ ውስጥ በክርስቶስ ተካተው፣ እንደ ወይን ዘለላዎች፣ በጌታ ፀጋ በመታገዝ ማደግ እና ፍሬ ማፍራት እንችላለን" ብለዋል።

ሊቀ ጳጳሱ ቅዱስ አውግስጢኖስ በመዝሙረ ዳዊት 68 ላይ ያደረገውን አስተንትኖ በተመለከተ አስተያየቱን ሲሰጡ በዚህ መልኩ የትናንሽ ነገርን ጥንካሬ እንዳጎላው አስታውሰው ሲያድግ በአንድ ሕዝብ ውስጥ ማለትም "በምድር ሁሉ የሚስፋፋ የእግዚአብሔር ሕዝብ" መሆኑን አበክሮ ገልጿል።

ምሥራቹን ወደ ቤት አምጡ እና የክርስቶስን ፊት ለምታገኛቸው ሰዎች አስተላልፉ ብለዋል።

ከዚህ አንጻር ቅዱስ አባታችን ወጣቶቹ በእነዚህ ቀናት ያጋጠሟቸውን ነገሮች ሁሉ፣ ያሳለፉትን ጊዜ የምያስታውሱበት የመታሰቢያ ጊዜ ብቻ እንዳይሆን አሳስበዋል። "እባካችሁ ይህ ሁሉ በሚያማምሩ ፎቶዎች ላይ እንደ ትውስታ ብቻ ሆኖ እንዲቀር አትፍቀዱ" ይልቁንስ ወደ ቤት ከተመለሳችሁ በኋላ ክርስቶስን ለሁሉም አስተላልፉ ብለዋል።

“የምትገናኙትን ሁሉ፣ እኛን የሚወድና ራሱን የሚሰጥ፣ በእያንዳንዱ የተጠመቀ ሰው ውስጥ የሚኖረውን የክርስቶስን ፊት በእናንተ ላይ ይዩ” በማለት ቅዱስ አባታችን አበረታተዋል።

የተወደዳችሁ የፔሩ ቅዱሳን

ስለዚህም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ፣ በጥቃቅንና በተሰወረው ነገር በነፃ ውደዱና አገልግሉ፣ ምክንያቱም በመጀመሪያ የመወደድ ደስታን ስላሳያችሁ እና ሁሉንም ነገር በነፃ ከእግዚአብሔር አብ ስለተቀበላችሁ ነው።

“በእነዚህ ቀናት ውስጥ በምትሸከሟቸው ቦርሳዎች ውስጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ብቻ ያዙ፣” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የገለጹ ሲሆን “ጳጳሱ ዛሬ ለእናንተ በአደራ የተሰጡትን ተልእኮ የሚያሳይ ምልክት ነው፣ ይህም በሄዳችሁበት ቦታ ሁሉ ሚስዮናውያን ሁኑ፤ ልክ እንደ ተወዳጅ የፔሩ ቅዱሳን ለጌታ ፊት ግልጽ ሁኑ" ማለታቸው ተገልጿል።

29 Jul 2025, 08:06