ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ   (AFP or licensors)

ር.ሊ.ጳ. ሊዮ በመከፋፈል ጊዜም ቢሆን የሰው ልጅ ሁል ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል ማለታቸው ተገለጸ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ለጣሊያን የበጎ አድራጎት ድርጅት በቪዲዮ መልእክት መላካቸው የተገለጸ ሲሆን በመከፋፈል የተነሳ በተጨነቀው ዓለም ውስጥ ውይይት እና ሰላምን ማስተዋወቅ አስፈላጊ መሆኑን አጥብቀው ተናግረዋል ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ለሰላም የመሰብሰብን አጣዳፊነት እና አንድነትን በስፖርት፣ በፖለቲካ፣ በሙዚቃ እና በሌሎችም ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት የገለጹ ሲሆን የቫቲካን ቅድስት መንበር የሕፃናት ሆስፒታል ባምቢኖ ጄዙ እና የጣሊያን ካሪታስ ባዘጋጁት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የጨዋታ ዝግጅት ላይ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "የእኛ ሰብአዊነት አደጋ ላይ ነው፥ ይህ ስለ ሰላም ከሚነገረው ነገር ጋር የተዛመደ አንድ ነጥብን የምያመለክት ነው" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመልእክታቸው “የሕፃናትን ዓይን አይተው ከእነሱ እንዲማሩ” ያላቸውን ተስፋ ገልፀው ሌሎችን እንዴት “ለመቀበል ድፍረት ማግኘት እንደሚችሉ፣ ሰዎች እንዴት መገናኘት እንደሚችሉ እና “እርቅ እንደሚመጣ ለማመን፣ ለመጠየቅ፣ ጥንካሬን ለማግኘት እና የጥላቻ ግንባታ የሚቆምበት ጊዜ” እንዲኖራቸው እንደምያደርግ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

"አሁንም ይቻላል፣ ሁልጊዜም ቢሆን መሰባሰብ ይቻላል፣ ቦምብ በሚወድቅበት እና በጦርነት ጊዜም ቢሆን፣ይህን እውን ለማድረግ ዕድሎችን መፍጠር አስፈላጊ ነው"ሲሉ አጽንኦት ሰጥው በመልእክታቸው የተናገሩ ሲሆን መከፋፈልን ፈትኑና ትልቁ ፈተና አንድ ላይ መሰባሰብ መሆኑን ተገንዘቡ" ማለታቸው ተገልጿል።

የታመሙ ህጻናትን እና ቤተሰቦቻቸውን የሚረዳ ዝግጅት

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክት በዚህ ዓመት በጣሊያነኛ ቋንቋ  "La Partita del Cuore" ("የልብ ግጥሚያ") የተሰኘው የበጎ አድራጎት እግር ኳስ ግጥሚያ እና ኮንሰርት ማክሰኞ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም. በማዕከላዊ ጣሊያን በምትገኘው በአኩይላ ከተማ ውስጥ በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ለተሳተፉ ሰዎች ነበር መልእክቱን ያስተላለፉት።

በቫቲካን የሕፃናት ሕክምና ሆስፒታል ባምቢኖ ጄዙ እና በጣሊያን ካሪታስ አስተባባሪነት የተዘጋጀው ዝግጅት ላይ የሚገኘው ገቢ በእነሱ ተነሳሽነት በጣሊያነኛ ቋንቋ “ፕሮጄቶ አኮልዬንሳ” (“የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮጄክት”) አካል መሆኑም ተገልጿል።

በኘሮጀክቱ የሚገኘው ገቢ በጣሊያን እና ከሀገር ውጭ ላሉ አቅመ ደካሞች ቤተሰቦች እና ልጆቻቸው በባምቢኖ ጄዙ ሆስፒታል ገብተው እንዲታከሙ የሕክምና ወጪያቸውን እና የማረፊያ ሥፍራ ለማዘጋጀት የሚውል እንደሆነም ተገልጿል።

የእግር ኳስ ጨዋታው የዚህ ተነሳሽነት 34ኛ ዝግጅት ሲሆን በሙዚቀኞች እና በፖለቲከኞች ቡድን መካከል የሚደረግ ይሆናል። ከተለያዩ የጣሊያናዊን አከባቢዎች የተውጣጡ አርቲስቶች የሙዚቃ ኮንሰርት ይቀርባል።

ጥፋትና ሞትን ሳይሆን ሕይወትን ይደግፉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በዚህ ክስተት ዙሪያ "ግጥሚያ" የሚለው ቃል "መገናኘት" እና አንድ ላይ መሰባሰብ ማለት ነው ሲሉ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት የገለጹ ሲሆን "ይህ ግጥሚያ አንድ ምክንያት ያለው ግጥሚያ ነው" ይህ "እርዳታ የሚሹ ልጆች፣ ከግጭት አካባቢዎች ወደ ጣሊያን የሚመጡ" እና "በእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮጀክት" የሚደገፉ ልጆችን ይጨምራል ሲሉ ተናግረዋል።

“በመሆኑም ግጥሚያ እና ልብ አንድ ላይ የሚጣመሩ ሁለት ቃላት ይሆናሉ” ሲሉ የተናገሩ ሲሆን አክሎም “ለሕይወት፣ መድኃኒቶችን ለመግዛት ገንዘብ ለማሰባሰብ እንጂ ለጥፋት እና ለሞት አይደለም” በማለት ተነሳሽነቱን አድንቀዋል።

ዛሬ ባለው ዓለም፣ ለእነዚህ ጉዳዮች "የማዳመጥ ቦታዎችን ለማግኘት በጣም አስቸጋሪ፣ ፈጽሞ የማይቻል ይመስላል" ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቤልጂየም ውስጥ ያፕሬስ በመባል በሚታወቀው ከተማ አቅራቢያ እ.አ.አ. በ1914 ዓ.ም በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በፈረንሣይ ፣ በእንግሊዝ እና በጀርመን ወታደሮች መካከል የተደረገውን የገና የእግር ኳስ ጨዋታ ምሳሌ አጉልተው በዋቢነት በመልእክታቸው ገልጸዋል።

እ.አ.አ በ1983 ዓ.ም በተለቀቀው በፖል ማካርትኒ “የሰላም ቧንቧዎች” በተሰኘው በፈረንሳይኛ ቋንቋ በተዘጋጀው  ፊልም ላይ ይህ ክስተት እንዴት እንደተዘገበ ጠቅሰዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በመልእክታቸው ሰዎች “ለበጎ ተግባር አንድ ላይ በጎ አስተዋጾ እንዲያበረክቱ” እና “የተሰበረ ልብን ወደ አንድነት እንዲመልሱ” አበረታተዋል።

"በእግዚአብሔር ልብ አንድ እንደሆንን፣ ልብም እግዚአብሔርን እና ሌሎችን የምንገናኝበት ቦታ መሆኑን እንወቅ" ሲሉ አስምረው ተናግረዋል።

ሙዚቃ፣ ስፖርት፣ ቴሌቪዥን እና ፖለቲካ የሚጫወቱት ሚና

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል ስፖርት፣ ሙዚቃ፣ ቴሌቪዥን እና ፖለቲካ አንድነትን በማጎልበት እና መከፋፈልን ለማስወገድ የሚያደርጉትን ትልቅ ሚና አስምረው የተናገሩ ሲሆን "ስፖርት - በተግባር በሚለማመዱ እና በሚደሰቱ ሰዎች ሲዘወተር - ይህ ትልቅ ነገር ስለእነርሱ እንድናስብ ያደርገናል፣ ግጭትን ወደ ሰላማዊ ግንኙነት፣ መለያየትን ወደ አንድነት እና ብቸኝነትን ወደ ሕብረት የሚቀይሩ ናቸው" ሲሉ ገልጿል።

አክለውም ቴሌቪዥን ሰዎችን ከማገናኘት የበለጠ ትልቅ ሚና ሊጫወት ይችላል፣ ምክንያቱም ለሁሉም "ከጥላቻ ይልቅ በፍቅር መካከል መግባባትን ለማስተዋወቅ ይረዳል" ብለዋል።

በተመሳሳይም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ፖለቲካ “ጠላቶችን በመገንባት ላይ ባለው ፕሮፓጋንዳ ካልተመሰረተ ከመከፋፈል ይልቅ አንድነትን ሊፈጥር ይችላል” ሲሉ አጥብቀው ተናግረዋል ።

ፖለቲካው “የጋራ ጥቅም ወደሚያስፈልገው ገንቢ የውይይት አስቸጋሪ እና አስፈላጊ ጥበብ” መገንባት አለበት ያሉት ቅዱስነታቸው በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "በልጅነት ጊዜ መናገር እና ማስታወስ ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ ቃላቶቻችንን እና ትውስታዎቻችንን የሚያበለጽግ ሙዚቃን አስፈላጊነት" አስምረውበታል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ይህ ዝግጅት የተዘጋጀላቸው ልጆች እነዚህን ነገሮች ያውቃሉ። እግዚአብሔርን ለማየት የሚያስችላቸው የልብ ንጽህና አላቸው" ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው የቪዲዮ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

16 Jul 2025, 16:41