ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮበቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮበቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  (@Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ 'በንግግር ለመጽናት 'የሄልሲንኪን መንፈስ' መጠበቅ አለብን' ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ረቡዕ ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምመናን ያደረጉትን የጠቅላላ በጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካጠናቀቁ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት የሄልሲንኪ ስምምነት የተፈረመበትን 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በማስታወስ፣ ‘ከመቼውም ጊዜ በላይ ዛሬ የሄልሲንኪን መንፈስ በመጠበቅ በውይይት መጽናት፣ ትብብርን ማጠናከር እና ዲፕሎማሲያዊ ዕድል ያለው መንገድ ማድረግ አስፈላጊ ነው’ ሲሉ አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

እ.አ.አ "በነሐሴ 1 ላይ የሄልሲንኪ (በፊንላንድ ዋና ከተማ) የመጨረሻ ህግ የተፈረመበት ሃምሳኛ አመት እናከብራለን። በቀዝቃዛው ጦርነት አውድ ውስጥ ደህንነትን ለማረጋገጥ ባለው ፍላጎት የተነሳ ሠላሳ አምስት አገሮች በምስራቅ እና በምዕራብ መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር አዲስ የጂኦፖሊቲካል ዘመን ውስጥ እንድንገባ አደረጉን" በማለት የተናገሩት ቅዱስነታቸው በዚህ ስምምነት መንፈስ አሁንም ቢሆን መኖር አለብን ሲሉ አሳስበዋል።

የሄልሲንኪ ስምምነት፣ የሄልሲንኪ የመጨረሻ ህግ ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን እ.ኤ.አ. ነሐሴ 1 ቀን 1975 ዓ.ም ሰነዱ ተፈርሞ ተግባራዊ መሆን ጀመረ። ሰነዱ በምዕራባውያን ኃያላን አገራት እና የሶቪየት ኅብረት በአውሮፓ የደህንነት እና የትብብር ኮንፈረንስ የተፈረመበት ታሪካዊ ስምምነት ሲሆን ዓላማውም የምስራቅ-ምዕራብ ግንኙነቶችን ማሻሻል ነው።

ዲፕሎማሲ ልዩ መንገድ መሆን አለበት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ዛሬ ማለዳ እንዳስታወቁት ሰነዱ በሰብአዊ መብቶች ላይ የታደሰ ትኩረት እንዲደረግ፣ በተለይም ለሃይማኖት ነፃነት ፣ ከቫንኮቨር እስከ ቭላዲቮስቶክ ድረስ ለተዘረጋው የትብብር ሥር መሠረት ከሆኑት መካከል አንዱ ተደርጎ ይወሰዳል ፣ እናም የቅድስት መንበር ንቁ ተሳትፎ በሄልሲንኪ ኮንፈረንስ  ላይ በወቅቱ የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የነበሩት ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ካዛሮሊ ተሳትፎ መገለጹ ይታወሳል፣ ሰላምን ለማበረታታት እና ለፖለቲካዊ ቁርጠኝነት የሚረዳ ሰነድ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ “የሄልሲንኪን መንፈስ መጠበቅ፣ በውይይት መጽናት፣ ትብብርን ማጠናከር እና ዲፕሎማሲያዊ ዕድል ያለው መንገድ ማድረግ አስፈላጊ ነው” ሲሉ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

“የሄልሲንኪን መንፈስ መጠበቅ፣ በውይይት መጽናት፣ ትብብርን ማጠናከር እና ዲፕሎማሲውን የድል ጎዳና ማድረግ ከምንጊዜውም በላይ ዛሬ በጣም አስፈላጊ ነው" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አክለው ገልጸዋል።

30 Jul 2025, 16:40