ር.ሊ.ጳ ሊዮ በኮንጎ በደረሰው ጥቃት አሳዛኝ ሁኔታዎችን መከላከል ለተሰደዱ ክርስቲያኖች እጸልያለሁ አሉ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምሥራቃዊ ክፍል ኮማንዳ በሚባልበት ሥፍራ ሐምሌ 16 እና 17/2017 ዓ.ም ምሽት በደረሰው አሰቃቂ የሽብር ጥቃት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘኔታ በድጋሚ ልገልጽ እወዳለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው በጸሎት ጊዜ በቤታቸው እና በቤተክርስቲያን ውስጥ የነበሩ ከአርባ በላይ ክርስቲያኖች መገደላቸውን ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በሀገሪቱ ኢቱሪ ግዛት በኮማንዳ በሚገኘው የብፁዕ አቡነ አኑዋሪት ደብር ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ጥቃት በመግለጽ ከበጋ የዕረፍት ጊዜያቸው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ረቡዕ ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም ካደረጉት የጠቅላላ አስተምህሮ በመቀጠል ባስተላለፉት መልዕክት ይህንን ገልጸዋል ።
በምስራቅ ኮንጎ ኢቱሪ ግዛት እሁድ እለት አማፅያን የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ወረው በምእመናን ላይ ተኩስ ከከፈቱ በኋላ ከ40 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 38 ሰዎች መሞታቸው የተረጋገጠ ሲሆን ሌሎች በአቅራቢያው ባለ መንደር በርካቶች ተገድለዋል።
በዛሬው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተጎጂዎችን ለእግዚአብሔር አፍቃሪ ምሕረት አደራ እንደሚሰጡ ተናግረው፣ “ለቆሰሉት እና በዓለም ዙሪያ ላሉ ክርስቲያኖች ሁከትና ስደት እየደረሰባቸው ላሉ ሁሉ እጸልያለሁ” ሲሉ አረጋግጠዋል።
"ለቆሰሉት እና በአለም ዙሪያ ላሉ ክርስቲያኖች ሁከት እና ስደት እየደረሰባቸው ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ እጸልያለሁ" ያሉ ሲሆን ይህንንም መነሻ በማድረግ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ “በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች ይህን መሰል አደጋዎችን ለመከላከል እንዲተባበሩ አሳስባለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ቅዱስ አባታችን በላኩት የሐዘን መግለጫ ቴሌግራም “የእነዚህ ሰማዕታት ደም የሰላም፣ የእርቅ፣ የወንድማማችነት እና ለኮንጎ ሕዝብ ፍቅር ያድርግልን” በማለት ጸልየዋል።
"በሀገር ውስጥም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት ይህን መሰሉን አደጋ ለመከላከል በጋራ እንዲሰሩ አሳስባለሁ" ሲሉም አብክረው ተናግረዋል።
