ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ሊዮ 14ኛ በሮም ከተማ አቅራቢ በሚገኘው በካስተል ጋንዳልፎ ር.ሊ.ጳ ሊዮ 14ኛ በሮም ከተማ አቅራቢ በሚገኘው በካስተል ጋንዳልፎ  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለዩክሬን ተስፋ አለ፣ ነገር ግን ሥራ እና ጸሎት ያስፈልጋል ማለታቸው ተገለጸ

በነሐሴ 6/2017 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ ለእረፍት ከሄዱበት ከካስቴል ጋንዶልፎ ወደ ቫቲካን ከመመለሳቸው በፊት ጳጳሱ ማክሰኞ ምሽት ነሐሴ 13/2017 ዓ.ም ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "ሰላምን ለማግኘት ወደፊት መንገዱን በእውነት መፈለግ አለብን" ብለዋል ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"ተስፋ አለ፣ ነገር ግን አሁንም ጠንክረን መስራት፣ ጠንክረን መጸለይ እና ሰላም ለማግኘት ወደ ፊት መንገዱን በእውነት መፈለግ አለብን" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ማክሰኞ አመሻሽ ነሐሴ 13/2017 ዓ.ም ላይ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማቆም ታስቦ የተደርገውን ድርድር አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ከተወሰኑ መሪዎች ጋር ስለሚደረጉ ንግግሮች፣ “አንድ ሰው” ያለማቋረጥ የሰላም አሰፈላጊነት እንደሚሰማው ተናግሯል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በነሐሴ 13/2017 ዓ.ም ወደ ቫቲካን ለመመለስ በካስቴል ጋንዶልፎ የሚገኘውን የበጋ መኖሪያ ቤት ለቀው ሲወጡ ከአንድ ሰዓት በፊት ቅዱስ አባታችን እሳቸውን ለማየት ለተሰበሰቡት ብዙ ሰዎች ሰላምታ አቅርበዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በካስቴል ጋንዶልፎ ስለነበራቸው ቆይታም በቅርቡ እንደሚመለሱ ተስፋ እንዳላቸው ተናግረው ነበር። “እዚህ መሆን መታደል ነው” ብሏል። "ከህዝቡ ለተደረገልኝ አቀባበል በጣም ደስተኛ ነኝ" ብለዋል።

በዕለቱ ቀደም ብሎ “ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የጎበኟቸውን የእመቤታችንን ቤተ መቅደስ” መጎብኘታቸውን አስታውሰዋል።

በመጨረሻም በርዕሰ ሊቀ ጳጳስነት ስላሳለፉት የመጀመሪያዎቹ መቶ ቀናት ሲጠየቁ “የእግዚአብሔር በረከት” የነበሩባቸው ቀኖች እንደነበሩ አበክሮ ገልጿል። ወደ ቫቲካን የሚወስደውን መኪና ከመሳፈራቸው በፊት በመጨረሻ ባደረገው ንግግር፣ “በጣም ተቀብላችሁኛል፣ በጌታ ፀጋ አምናለሁ፣ እና ለተደረገልኝ አቀባበል በጣም አመስጋኝ ነኝ። ሁላችሁንም አመሰግናለሁ" በማለት ከልብ የመነጨ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሁለተኛው ቆይታ በካስቴል ጋንዶልፎ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በሐምሌ ወር ከሁለት ሳምንታት በላይ ካሳለፉ በኋላ በነሐሴ 06/2017 ለሁለተኛ ጊዜ ለእረፍት ወደ ካስቴል ጋንዶልፎ ተመለሱ። በእነዚህ ሰባት ቀናት ውስጥ ከምእመናን ጋር አራት ቀጠሮዎች ነበሯቸው። የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ ምዕመናን ዘንድ በነሐሴ 15/2025 ዓ.ም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሰታ ማርያም ክብረ በዓል፣ ጳጳሱ ከቪላ ባርበሪኒ ብዙም በማይርቅ በቅዱስ ቶማስ የቪላኖቫ ጳጳሳዊ ደብር ውስጥ ቅዳሴ በማሳረግ አክብረዋል።  በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባደርጉት ስብከት የማርያም “እነሆኝ” የሚለው ቃል “በዘመናችን ባሉ ሰማዕታት፣ በእምነትና በፍትህ፣ በየዋህነት እና በሰላም ምስክሮች ሞትን እንደሚቃወመው” አጽንዖት ሰጥተው ገልጸው የነበረ ሲሆን ከእዚያን በኋላ ግን ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በመቀጠል ባስተላለፉት መልእክት ወደ ወቅታዊው የዓለም ክስተቶች ዘወር በማለት ፣ ሰዎች “የግጭት እና የጦር መሣሪያ አመክንዮ መስፋፋት” ራሳቸው ፈቃደኛ እንዳይሆኑ አሳስቧቸው ነበር።

ቀኑ ከአልባኖ ድሆች እና ቤት አልባዎች ጋር

ያለፈው እሑድ፣ ነሐሴ 11/2017 ዓ.ም እንዲሁ የመገናኘት ቀን ነበር። ጠዋት ላይ ጳጳሱ በአልባኖ በሚገኘው የቅድስት ማርያም  ዴላ ሮቶንዳ ቤተ መቅደስ ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የሚታወስ ሲሆን- ለአካባቢው ድሆች - ቤት ለሌላቸው እና በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ያሉ የመጠለያ እና የቡድን ቤቶች ነዋሪዎች - እንዲሁም የካሪታስ ሠራተኞች እና የምክር ማዕከላት ተጠቃሚዎች ጋር የምሣ ግብዣ መቋደሳቸው ይታወሳል።በወቅቱም “የጦርን ወይም ሌሎችን የሚያቃጥል የቃላት እሳትን ሳይሆን፣ ራሱን የሚያዋርድና የሚያገለግል፣ ግድየለሽነትን በጥንቃቄ እና በትዕቢት በየዋህነት የሚቃወም የፍቅር እሳት፣ የጦር መሣሪያን ያህል የማይከፋፍል፣ ነገር ግን ዓለምን በነጻነት የሚያድስ የደግነት እሳት” እንዲያመጡ አሳስበዋል።

ከእሁድ የአምልኮ ሥርዓት በፊት በአልባኖ ጎዳናዎች ላይ በብዙ ሰዎች አቀባበል የተደረገላቸው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በሀገረ ስብከቱ ካሪታስ የተዘጋጀውን “የተስፋ ምልክቶች” የተሰኘውን ዐውደ ርዕይ ጎብኝተዋል።

ከቅዳሴ በኋላ ቅዱስ አባታችን ወደ ካስቴል ጋንዶልፎ ለሳምንታዊው የመልአክ እግዚአብሔር ጸሎት ለማድረግ ተመለሱ። የማሪያም ጸሎት ሲያበቃ ምእመናን አብረዋቸው እንዲጸልዩ በመጋበዝ “ጦርነት እንዲቆምና ሰላምን ለማስፈን የሚደረጉ ጥረቶች ፍሬ እንዲያፈሩ፣ እና በድርድር የህዝቦች የጋራ ጥቅም ምንጊዜም ቅድሚያ እንዲሰጠው” እንዲጸልዩ ጋብዟል።

20 Aug 2025, 10:13