ር.ሊ.ጳ ሊዮ በእግዚአብሔር ጊዜ እና ጸጋ እመኑ" ማለታቸው ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በእለቱ የተነበበው የቅዱስ ወንጌል ምንባብ
"በተሰቀለበትም ስፍራ የአትክልት ቦታ ነበረ፤ በአትክልቱም ቦታ ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ። መቃብሩም ቅርብ ስለ ነበረና የአይሁድ የዝግጅት ቀን ስለ ነበረ ኢየሱስን በዚያ አኖሩት" (ዩሐንስ 19፡41-42)።
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በወቅቱ ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ
ተስፋችን በሆነው በኢየሱስ ሕይወት ዙሪያ ላይ እያደረግን የምንገኘውን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል ዛሬ የቀዳም ሱር ወይም ቅዱስ ቅዳሜ (ቅዱስ ቅዳሜ ወይም ቀዳም ሱር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለበት ዐርብ እለት ቀጥሎ ያለው ቅዳሜ እለት ማለት ነው፣ በስቅለተ ዐርብ እና በትንሣኤ እሁድ መካከል ያለውን የቅዳሜ ቀን ያመለክታል) ተብሎ በሚጠራበት እለት ላይ ተከስቶ በነበረው ምስጢር ላይ እናሰላስላለን። በወቅቱ የእግዚአብሔር ልጅ በመቃብር ውስጥ ይገኛል። ነገር ግን ይህ የእሱ "አለመኖር" ባዶነት አይደለም፣ የመጠበቅ፣ የተገታ ወይም ሊፈጸም የተቃረበ ሙላት፣ በጨለማ ውስጥ የተቀመጠ ተስፋ ነው። ሰማዩ ድምጽ አልባ ዲዳ የሚመስልበት፣ ምድርም የማይንቀሳቀስበት ታላቅ የዝምታ ቀን ነው፣ ነገር ግን የክርስትና እምነት ጥልቅ ምስጢር የተፈጸመበት በትክክል በእዚያ እለት ነው። እንደ እናት በማኅፀን ውስጥ ያለ ያልተወለደውን፣ ነገር ግን በህይወት ያለ ልጇን እንደምትሸከም ትርጉም ያለው ዝምታ ነው።
ከመስቀል ላይ የወረደው የኢየሱስ አካል አንድ ሰው ውድ በሆነ ነገር እንደሚያደርገው በጥንቃቄ ተገንዟል። ወንጌላዊው ዮሐንስ “ማንም ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር” ውስጥ በአትክልት ስፍራ እንደ ተቀበረ ይነግረናል (ዮሐ. 19፡41)። በአጋጣሚ የሆነ ነገር አይደለም። ያ የአትክልት ስፍራ አምላክና ሰው የተዋሃዱበትን የጠፋውን ኤደን ያስታውሳል። እናም ያ መቃብር በጭራሽ ጥቅም ላይ ያልዋለ ፣ አሁንም ስለሚሆነው ነገር ይናገራል፡ እሱ መግቢያ በር እንጂ መጨረሻ አይደለም። በፍጥረት መጀመሪያ ላይ እግዚአብሔር የአትክልት ቦታን አዘጋጀ ተከለ፣ አሁን አዲስ ፍጥረት ደግሞ በገነት ይጀምራል፡ የተዘጋው መቃብር በቅርቡ ይከፈታል።
ቅዱስ ቅዳሜም (ቀዳም ሱር) የእረፍት ቀን ነው። በአይሁድ ሕግ በሰባተኛው ቀን ምንም ሥራ መሥራት የለበትም፣ አይፈቀድምም፣ በእርግጥም ከስድስቱ የፍጥረት ቀናት በኋላ እግዚአብሔር ያርፋል (ዘፍ. 2፡2)። አሁን ወልድም የማዳን ሥራውን ከጨረሰ በኋላ ዐርፏል። ስለደከመ ሳይሆን እስከ መጨረሻው ስለወደደ ነው። የሚጨመር ምንም ነገር የለም። ይህ እረፍት በተጠናቀቀው ተግባር ላይ ማህተም ማድረግ ማለት ነው፣ መደረግ የነበረበት በትክክል መፈጸሙን ማረጋገጫ ነው። በተሰወረው የጌታ መገኘት የተሞላ እረፍት ነው።
ቆም ብለን ለማረፍ እንታገላለን፣ እንቸገራለን። ሕይወት ፈጽሞ በቂ እንዳልሆነች አድርገን እንኖራለን። ለማምረት፣ ራሳችንን ለማረጋገጥ፣ ለመቀጠል እንቸኩላለን። ነገር ግን እንዴት መቆም ወይም ማረፍ እንዳለብን ማወቅ ልንፈጽመው የሚገባን የመተማመን ተግባር እንደሆነ ወንጌሉ ያስተምረናል። ቅዱስ ቅዳሜ (ቀዳም ሱር) ሕይወት ሁልጊዜ በምንሠራው ላይ የተመካ እንዳልሆነ፣ ነገር ግን ማድረግ የምንችለውን እንዴት ዕረፍት እንደምንወስድ፣ እንዴት እንደምናውቅ እንድንገነዘብ ይጋብዘናል።
በመቃብር ውስጥ፣ ኢየሱስ የአብ ህያው ቃል፣ ዝም አለ። ነገር ግን ልክ በዚያ ዝምታ ውስጥ ነው አዲሱ ህይወት መፍላት ወይም ኩፍ ማለት የምጀምረው። እንደ መሬት ዘር፣ ጎህ ሳይቀድ እንደ ጨለማ። እግዚአብሔር ጊዜ ማሳለፍ አይፈራም፤ ምክንያቱም እርሱ የሚጠባበቅ አምላክ ነው። ስለዚህም የእኛ “የማይጠቅም” ጊዜ፣ የእረፍት ጊዜ፣ ባዶነት፣ መካን ጊዜያት፣ የትንሣኤ ማኅፀን ሊሆን ይችላል። ተቀባይነት ያለው እያንዳንዱ ዝምታ የአዲስ ቃል መነሻ ሊሆን ይችላል። ለእግዚአብሔር ብናቀርበው እያንዳንዱ የእረፍት ጊዜ የጸጋ ጊዜ ሊሆን ይችላል።
በመሬት ውስጥ የተቀበረው ኢየሱስ ሁሉንም ቦታ የማይዝ የእግዚአብሔር የዋህ ፊት ነው። እሱ ነገሮች እንዲደረጉ የሚፈቅድ፣ የሚጠብቅ፣ የሚያፈገፍግ አምላክ ነው። ሁሉም ነገር ያለቀ ቢመስልም የሚታመን አምላክ ነው። እኛ ደግሞ በዚያ ለጊዜው በታገደው ቅዱስ ቅዳሜ (ቀዳም ሱር)፣ እንደገና ለመነሣት መቸኮል እንደሌለብን እንማራለን። በመጀመሪያ ዝምታን መቀበል አለብን ፣ እራሳችንን በገደብ መማር መቀበል አለብን። አንዳንድ ጊዜ ፈጣን መልሶችን፣ አፋጣኝ መፍትሄዎችን እንፈልጋለን። እግዚአብሔር ግን በጥልቅ ይሠራል፣የእግዚአብሔር መዘግየት የመታመን ጊዜ ነው። ስለዚህ ቅዱስ ቅዳሜ (ቀዳም ሱር) የመቃብር ሰንበት የማትበገር ብርሀኑ የትንሳኤ ብርሃን የሚፈልቅበት ማህፀን ይሆናል።
ውድ ጓደኞቼ፣ የክርስትና ተስፋ የሚወለደው በጫጫታ ሳይሆን በፍቅር በተሞላ የተስፋ ዝምታ ነው። የደስታ ልጅ አይደለም ፣ ግን የታመነ ተጥሎ መኖር ነው። ድንግል ማርያም ይህንን ትምክህት ፣ይህን አደራ ፣ይህን ተስፋ ታሳያለች። ሁሉም ነገር የቆመ፣ ህይወት የተዘጋ መንገድ እንደሆነ ሲመስለን፣ ቅዱስት ቅዳሜን (ቀዳም ሱር) እናስታውስ። በመቃብር ውስጥ እንኳን፣ እግዚአብሔር ከሁሉ የሚበልጠውን ድንቅ ነገር እያዘጋጀ ነበር። እናም የሆነውን ነገር በአመስጋኝነት እንዴት እንደምንቀበል ካወቅን ፣ በትክክል በትንሽነት እና በዝምታ ፣ እግዚአብሔር እውነታውን በመለወጥ ሁሉንም ነገር በፍቅሩ ታማኝነት አዲስ የሚያደርግ መሆኑን እንገነዘባለን። እውነተኛ ደስታ የሚወለደው በትዕግስት፣ በእምነት፣ በፍቅር የኖረው ነገር ወደ ዘላለማዊ ሕይወት እንደሚመጣ ካለው ተስፋ ነው።
