ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ፥ ከሦስተኛ ዙር ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ወንድማማችነት ስብሰባ ተሳታፊዎች ጋር ር. ሊ. ጳ. ሊዮ፥ ከሦስተኛ ዙር ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ወንድማማችነት ስብሰባ ተሳታፊዎች ጋር   (@Vatican Media)

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ፥ “ወንድማማችነት ማለት የእግዚአብሔርን ፊት በሌሎች ላይ ማየት ነው” ሲሉ አስገነዘቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፥ ከሦስተኛ ዙር ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ወንድማማችነት ስብሰባ ተሳታፊዎች ጋር በቫቲካን ውስጥ ዓርብ መስከረም 2/2018 ዓ. ም. ተገናኝተዋል። ቅዱስነታቸው ለተሳታፊዎቹ ባደረጉት ንግግር፥ በስልጣን፣ በጥቅም እና በጥርጣሬ ላይ ሳይሆን በጥንቃቄ፣ በልግስና እና በመተማመን ላይ የተመሠረተ የሰው ልጆች ኅብረት እንዲፈጠር አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በሦስተኛ ዙር ዓለም የሰብዓዊ ወንድማማችነት ስብሰባ መጀመሪያ ላይ ከተሳታፊዎች ጋር በቫቲካን በሚገኘው የቀሌሜንጦስ አዳራሽ ውስጥ ተገናኝተው ሰላምታ አቅርበዋል። ግጭት እና መለያየት በበዛበት ዓለም ውስጥ ጦርነትን በድፍረት በመቃወም ለሰላም እና ለወንድማማችነት መቆማቸው ይበልጥ አስፈላጊ መሆኑን አበክረው ተናግረዋል።

ነፍስሔር ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ “ጦርነት ምን ጊዜም ቢሆን መልስ ሊሆን አይችልም” ባሉት ላይ በማስርተንተን እንደተናገሩት፥ “የአባላቱ በስብሰባው ላይ መገኘት የተለያዩ እምነቶችን እና ባህሎችን አንድ ሊያደርግ የሚችል መሆኑን ይመሰክራል” ብለው፥ “ይህም ከልዩነቶች ባሻገር ራሳችንን እንደ ወንድማማቾች እና እህትማማቾች አድርገን እንድንገነዘብ የሚረዳን ኃይል ነው” ሲል ገልጸዋል።

“ወንድምህ የት አለ?”

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ በዓይነቱ የመጀመሪያ በሆነው በቃየል እና በአቤል መካከል ያለውን ዝምድና በማስታወስ እንደተናገሩት፥ ምንም እንኳን ዝምድናቸው በግጭት ቢታወቅም ነገር ግን ይህ የመጀመርያው የኃይል እርምጃ ዘወትር እንደዚያው ነው ብለን ራሳችንን ማሳመን እንደማይገባ አስጠንቅቀዋል።

“ጥንታዊ እና በስፋት የሚነገር ቢሆንም የቃየን ጥቃት የተለመደ አድርጎ መቀበል ፈጽሞ የለበትም” ሲሉ አሳስበው፥ “ይልቅስ ልንከተለው የሚገባን መንገድ ‘ወንድምህ የት ነው?’ በሚለው ጥያቄ ውስጥ ይገኛል” ሲሉ አስረድተዋል።

በዚህ ጥያቄ ውስጥ ጥሪያችንን፣ ምሳሌያችንን፣ የፍትህ መለኪያ እና አስተዳደርን እናገኛለን” ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ እግዚአብሔር አምላክ ወንድሙን የገደለውን ቃየንን እንደማይበቀለው ተናግረው፥ በተቃራኒው በሰው ልጆች መካከል ለዘመናት የቆየውን ጥያቄ መልሶ ይጠይቃል” ብለዋል።

“ለእናንተ የቀረበ ጥያቄ ነው!”

“ጥያቄው ቀላል አይደለም” በማለት የገለጹት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፥ የማስታረቅ መርህ እንደሚሆን አጽንዖት ሰጥተው፥ “ጥያቄውን በልባችን ውስጥ መያዝን ስንማር በእያንዳንዱ የዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ራሳችንን ልንጠይቀው የሚገባን የግል ጥያቄ ይሆናል” ብለዋል።

ወንድሞች እና እህቶች ሆይ! የጦር መሣሪያን እንዲያነሱ የተገደዱ ወጣቶችን ሕይወት የሚያናጉ፣ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሰላማዊ ዜጎችን፣ ሕጻናትን፣ ሴቶችን እና አዛውንቶችን ዒላማ ያደረጉ እና ለራሳችንም እንግዳ የሚያደርግበት እጅግ በተቆራኘ ሕይወት ውስጥ ብቸኝነትን በማስፋፋት ማኅበራዊ ትስስርን የሚያበላሹ ጦርነቶች ሲካሄዱ የት ነበራችሁ?” ሲሉ ጠይቀዋል።

“ዝምታ መልስ ሊሆን አይችልም!” ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ በሰብዓዊ ወንድማማችነት ላይ የተካሄደ ዓለም አቀፍ ስብሰባን በቁርጠኝነት እና በድፍረት የተሳተፉት ለጥያቄው መልስ እንዲሆኑ አበረታተዋል። ከዕድገት እና ከብልጽግና መንገዶች መካከል አንዱ የሆነውን የተለየ ሕይወት ለመምራት ያደርጉት ምርጫ ዓለምን ሊለውጠው እንደሚችል አስረድተዋል።

እግዚአብሔርን በሌሎች ሰዎች ውስጥ መመልክት

“በዙሪያችን ያሉ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ማየት ከጀመርን፥ የተገለልን መሆናችንን ከማመን ወይም ከግል ጥቅም አንጻር ብቻ ግንኙነት ከመመሥረት አመክንዮ ነፃ እንሆናለን” ብለዋል። “የግል ፍላጎት ለእርስ በርስ ግንኙነት ብቸኛው መሠረት አይደለም” ያሉት ቅዱስነታቸው፥ “መንፈሳዊ ወጎች እና የዳበረ ሂሳዊ አስተሳሰብ ከቤተሰባችን ወይም ከጎሳ ትስስራችን ባለፈ ከሰዎች ጋር እንድንገናኝ በር ከፍተዋል” ብለዋል።

“ወንድማማችነት ትክክለኛ የመቀራረቢያ ስም ነው” ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፥ ትርጉሙ የሌላውን መልክ እንደገና ማግኘት ማለት እንደሆነ አስረድተው፥ “ለሚያምኑት በሙሉ የእግዚአብሔርን መልክ በሁሉም ሰዎች ማለትም በድሆች፣ በተገለሉት እና በጠላቶችም ጭምር ማየት ነው” ብለዋል።

በእንክብካቤ ላይ የተገነባ ኅብረት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፥ ሰብዓዊ ወንድማማችነትን በማስመልከት በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ ስብሰባ መሠረት፣ ሁሉንም የስብሰባው ተሳታፊዎች በተለያዩ የሥራ መስኮች፣ እውቀት እና ትውልዶች መካከል ትስስርን ለመፍጠር አዳዲስ መንገዶችን እንዲፈልጉ ጠይቀው፥ እነዚህ መንገዶች ድሆችን እንደ ዕርዳታ ተቀባይ ብቻ አድርገው የሚመለከቱ ሳይሆን በማስተዋል እና በጋራ ውይይት ንቁ ተሳታፊዎች አድርገው እንዲያካትቷቸው አሳስበዋል።

“ይህን መልካም ዘርን የመዝራት ሥራን እንድትቀጥሉበት” በማለት አሳስበው፥ ከዚህም በመነሳት ሰብዓዊነትን እና ወንድማማችነትን ያማከለ እውነተኛ አሳታፊ ሂደት ሊመጣ እንደሚችል ገልጸው፥ ከስልጣን፣ ከጥቅም እና ከጥርጣሬ ይልቅ በእንክብካቤ፣ በልግስና እና በመተማመን ላይ ለተመሠረተ ሰብዓዊ ኅብረት ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በመልዕክታቸው መደምደሚያ፥ እያንዳንዱ ሰው በዕለት ተዕለት ሕይወቱ እና ከዚያም አልፎ የወንድማማችነት መንፈስን ማሳደግ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

 

13 Sep 2025, 15:32