ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ   (AFP or licensors)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ዋልታ ረገጥነትን ማስወገድ እንደ አንዱ የድልድይ ግንባታ ሂደት ይመለከቱታል።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አዲስ የሕይወት ታሪክ፣ “ሊዮ አሥራ አራተኛ፡ የዓለም ዜጋ፣ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሚስዮናዊ” በሚል አርእስት ቅዱስ አባታችን ለጋዜጠኛ ኤሊዝ አን አለን የሰጡት ቃለ ምልልስ ሙሉ ቃል አካቶ የታተመ መጽሐፍ ሲሆን የጋዛን አሳዛኝ ሁኔታ ጨምሮ፣ በቻይና ላይ የቤተ ክርስቲያን ፖሊሲ፣ የሴቶች ሚና፣ የቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች፣ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አብርኾት) በደል እና የተመሳሳይ ጾታ እና የስነ-ጾታ ለውጥ ሁኔታን፣ የሐሰት ዜናዎችን ጭምሮ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ያካተተ ነው።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እ.አ.አ በግንቦት 05/2025 ዓ.ም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን 267ኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡት በኋላ ባደረጉት የመጀመሪያ ሙሉ ቃለ ምልልስ በዩክሬን ሰላም እንዲሰፍን እና "በጋዛ ውስጥ ስላለው አስከፊ ሁኔታ" በሚመለከቱ ርዕስ ጉዳዮች ላይ ለቀረቡ የተለያዩ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል፥ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የሴቶች ሚና እና ቤተክርስቲያኗ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ እና ስነ-ጾታን የቀየሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ያላትን ግንኙነት፣ የቤተክርስቲያን አባቶች የምያደርሱትን ጾታዊ ጥቃት እና  የሮማን ኩሪያ ማሻሻያ በተመለከቱ ጭብጦች ላይ መለስ ሰጥተዋል።

ቃለ ምልልሱ ለጋዜጠኛ ኤሊዝ አን አለን ለቅዱስ አባታችን ሊዮ አሥራ አራተኛ “ሊዮ አሥራ አራተኛ፡ የዓለም ዜጋ፣ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሚስዮናዊ” በሚል አርዕስት ሐሙስ ዕለት መስከረም 08/2018 ዓ.ም ከፔንግዊን ፔሩ አሳታሚ ድርጅት ጋር በመተባበር አዲስ መጽሐፍ ታትሟል። አለን የ"CruxNow.com" ነፃ የኦንላይን ካቶሊካዊ የዜና ጣቢያ ከፍተኛ ዘጋቢ ሲሆን ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ሙሉ ቃል ሐሙስ ዕለት በተለቀቀው ተከታታይ መጣጥፎች ላይ ያሳተመ ነው።

የጵጵስና ሚና

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የጵጵስና ኃላፊነታቸውን እንዴት እንደሚመለከቱ ሲጠየቁ የአዲሱን ኃላፊነት ሚና በተለይም “በሁሉም ዕድሜ ላሉ ሰዎች የሚሰጡትን አገልግሎት” “የእረኝነት ሚና” አጉልተው የተናገሩ ሲሆን "ሁሉንም ሰው አደንቃለሁ፣ ማንም ይሁኑ ምን፣ ምን ይዘው ይመጣሉ... እናም አዳምጣቸዋለሁ… ስለዚህ፣ የአለም አቀፋዊ ቤተክርስቲያን እረኛ የመሆን አንድ ገጽታ በጣም አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፣ እናም ሰዎች ከሚያደንቁት ነገሮች አንዱ ያንን ነው ብዬ አስባለሁ" ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።

በሚቀጥሉት ወራት እና ዓመታት ውስጥ መወሰድ በሚገባቸው ውሳኔዎች ምንም ዓይነት ጭንቀት እንደማይሰማቸው ገልጸው፣ የቤተ ክርስቲያን የውስጥ አስተዳደር የጳጳስነት ሚናቸው ትልቅ አካል መሆኑን አምነዋል።

አዲስ ነገር የዓለም መሪ የመሆን ሚናው ነው ብሏል። "ቅድስት መንበር ለብዙ ዓመታት በዲፕሎማሲው ዓለም ውስጥ እንዴት ሚና እንደነበራ ብዙ እየተማርኩ ነው" ብለዋል። "ሁልጊዜ ዜናውን ለመከታተል እጥር ነበር፣ ነገር ግን የጳጳሱ ሚና ለእኔ አዲስ ነው።" እዚህም እንዲሁ፣ “ብዙ እየተማርኩ ነው እና በጣም እየተፈታተነኝ ነው፣ ነገር ግን አልተቸገርኩም" በማለት ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

የጋዛ አሳዛኝ ሁኔታ

ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከቀረቡት የመጀመሪያ ጥያቄዎች አንዱ የጋዛን ሁኔታ ይመለከታል። ምንም እንኳን ከአሜሪካ በእስራኤል ላይ አንዳንድ ጫናዎች ቢደረጉም እና በቅርቡ ከፕሬዚዳንት ትራምፕ አንዳንድ "በጣም ግልጽ መግለጫዎች" ቢኖሩም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "በጋዛ ውስጥ ያሉ የንጹሃን ዜጎችን ስቃይ ለማስታገስ ውጤታማ መንገዶችን ከማፈላለግ አንጻር ግልጽ ምላሽ አልተገኘም፣ እናም ይህ በጣም አሳሳቢ እንደሆነ ግልጽ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የጋዛውያንን እና በተለይም የአከባቢን ልጆች ፍላጎቶች ጎላ አድርገው አሳይተዋል። "ይህን ሁኔታ በእውነት ለመለወጥ ብዙ እርዳታ፣ የህክምና እርዳታ እና ሰብአዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፣ እና አሁንም ሁኔታው በጣም እና በጣም አሳሳቢ ይመስላል" ብሏል። በቴሌቭዥን ላይ የምናያቸው ምስሎችን ማየት በጣም አሰቃቂ ነገር ነው፤ ተስፋ እናደርጋለን፣ ሁኔታው እንደሚለወጥ ተስፋ እንዳደርጋለን ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ህመሙ እየደነዘዘ ስለመምጣቱ ጮክ ብሎ ገልጸው ነበር። "ይህ የሰው ምላሽ ነው፣ ምክንያቱም በጣም ብዙ ህመም ሲሰማህ ልትቆም አትችልም" ሲል ተናግሯል። የሰው ልጆች በተለይም ክርስቲያኖች ደንዝዘው ማደግ እና ሁኔታውን ችላ ማለት የለባቸውም ሲሉ ተናግሯል። ይልቁንስ “በሆነ መንገድ እዚህ ለውጥ ለማድረግ መግፋታችንን መቀጠል አለብን” ብለዋል።

“ዘር ማጥፋት” የሚለው ቃል

በጋዛ ላይ እየደረሰ ያለውን አሳዛኝ ክስተት በተመለከተ “የዘር ማጥፋት” የሚለውን ቃል መጠቀሙን በተመለከተ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ “በዚህ ጉዳይ ላይ በአሁኑ ጊዜ ምንም ዓይነት መግለጫ መስጠት እንደሌለብን የቅድስት መንበር በይፋ ታምናለች" ሲሉ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

“የዘር ማጥፋት ምን ሊሆን እንደሚችል በጣም ቴክኒካል ፍቺ አለ፣ ነገር ግን ጉዳዩን የሚያነሱት ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው፣ በእስራኤል የሚገኙ ሁለት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ይህንን መግለጫ የሰጡ ናቸው” ሲሉ አብራርቷል።

ከቻይና ጋር ግንኙነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በጂኦፖለቲካ ውስጥ በመቆየታቸው ስለ ቻይና "ሌላ ዓለም አቀፍ ተዋናይ" ተጠይቀው ነበር። “ከተወሰኑ አመታት ወዲህ ቅድስት መንበር ስትከተል የቆየችውን ፖሊሲ በአጭር ጊዜ ውስጥ እቀጥላለሁ” በማለት ከቀደሙት መሪዎች ይልቅ “በምንም መንገድ” “ጥበበኛ ወይም የበለጠ ልምድ ያላቸው” እንደ ሆነ እርግጠኛ አይደሉም።

ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ፣ የተለያዩ አመለካከቶች ያሏቸው በርካታ ቻይናውያን “በቀጣይ ውይይት ላይ መሆናቸውን” ገልፀው “ቤተክርስቲያኗ ባህልን እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በማክበር የቤተክርስቲያኗን ተልእኮ እንዴት መቀጠል እንደምትችል የበለጠ ግንዛቤ ለማግኘት እየሞከረች ነው” በተጨማሪም “ለብዙ ዓመታት የኖሩትን የቻይና ካቶሊኮች ትልቅ ቡድን በማክበር እምነታቸውን በነፃነት በመምራት ላይ ይገኛሉ ብለዋል። በተመሳሳይ ጊዜ "በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ በቻይና አለ " ብሎ እንደምያምኑ ገልጸዋል።

“ሊዮ አሥራ አራተኛ፡ የዓለም ዜጋ፣ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሚስዮናዊ” በሚል  አርእስት የታተመ መጽሐፍ
“ሊዮ አሥራ አራተኛ፡ የዓለም ዜጋ፣ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሚስዮናዊ” በሚል አርእስት የታተመ መጽሐፍ

የአሜሪካ ፖለቲካ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ከአሜሪካ የተገኙ የመጀመሪያው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ስለመሆናቸው አስፈላጊነት “በጂኦፖለቲካል ደረጃ” ተጠይቀው “በመጀመሪያ በአሜሪካ ከሚገኙት ጳጳሳት ጋር ሆነው ለውጥ እንደሚመጣ ተስፋ አደርጋለሁ” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ስለ አሜሪካ ኤጲስ ቆጶስነት እና በቤተክርስቲያን እና በፖለቲካ መካከል ስላለው ግንኙነት "የተነገሩትን አንዳንድ ነገሮች" በተመለከተ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "እኔ አሜሪካዊ መሆኔ ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ ሰዎች ከቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ላይ እንዳደረጉት፣ በእኔ ላይም ሊናገሩ አይችሉም ማለት አይደለም፣ "እርሳቸው አሜሪካን በሚገባ አይረዱም ነበር፣ በቀላሉ እየሆነ ያለውን ነገር አይመለከቱም ነበር" ብለዋል።

ሆኖም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በግልጽ “በፓርቲያዊ ፖለቲካ ውስጥ ለመሳተፍ አላሰብኩም” ብለዋል ።ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሃሳባቸውን ሲገልጹ “በአሜሪካ ውስጥ ያሉት የቤተ ክርስቲያን አመራር እሱን በቁም ነገር ቢያደርጉት የበለጠ ተገቢ ነው” ብለዋል። ሆኖም ከትራምፕ ጋር መነጋገር የሚቻልበት “የተለዩ ጉዳዮች ካሉ ወይም ሲኖሩ” “እንዲህ ለማድረግ ምንም ችግር የለብኝም” ብለዋል ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ የቀደሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው መጨረሻ አካባቢ ስለ ስደተኞች አያያዝ የሰጡትን መግለጫ እና መልእክት እንደ ምሳሌ ጠቅሰው፣ “የአሜሪካ ጳጳሳት እንዴት እንዳነሱት በማየቴ በጣም ተደስቻለሁ፣ አንዳንዶቹም ይህን ለማድረግ ደፋር ነበሩ” ብለዋል። አክለውም “እኔ እንደማስበው ያ አካሄድ፣ በአጠቃላይ፣ ከሁሉ የተሻለ አካሄድ ነው፣ ይህም በዋናነት ከጳጳሳት ጋር ልገናኝ ነው።

በኋላ ላይ "አሜሪካ በዓለም ደረጃ የኃያልነት ሚናዋን አምነን መቀበል አለብን፣ እናም አንዳንድ ጊዜ ውሳኔዎች ከሰብአዊ ክብር እና ከሰብአዊ ድጋፍ ይልቅ በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የተመሰረቱ ናቸው፣ ነገር ግን ምላሽ ለመስጠት "ምርጡን መንገድ" ለመወሰን መቃወም እና አንዳንድ ጥያቄዎችን ማንሳት መቀጠል አለብን" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ትራምፕ ራሱ በቅርቡ በሁለቱ መካከል የተደረገው ስብሰባ በአጀንዳ ላይ እንዳልሆነ ተናግሯል።

በቃለ መጠይቁ ውስጥ ከቤተሰባቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ሲገልጹ ስለ ወንድማቸው እንደገና ይናገራሉ። እርሳቸው እና ወንድማቸው ሉዊስ እና ጆን “አሁንም በጣም ቅርብ ናቸው፣ ምንም እንኳን አንዱ በፖለቲካው አንድ ጫፍ ላይ ቢሆንም እኛ ግን በተለያዩ ቦታዎች ነን ብለዋል።

በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚፈጸመው ጥቃት

አብዛኛው የውይይቱ ክፍል በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ላለው የካህናት ጾታዊ ጥቃት “ቀውስ” የተሰጠ ነው። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ይህ “እውነተኛ ቀውስ” መሆኑን አምነዋል፣ “ተጎጂዎች በታላቅ አክብሮት ሊታከሙ ይገባል እናም በደል ምክንያት በጣም ጥልቅ የሆነ ቁስል ያጋጠማቸው አንዳንድ ጊዜ እነዚያን ቁስሎች በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ እንደሚሸከሙ እንደሚረዱ ገልጸዋል።  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት የሚከሱት ሰዎች” “ተጨባጭ ተጠቂዎች” መሆናቸውን የሚያሳዩ አኃዛዊ መረጃዎችን ጠቅሰዋል። በሌላ አነጋገር እነሱ ክሶችን አይፈጥሩም፣ በሕይወታቸው ውስጥ የተፈጸሙ ጥቃቶች ናቸው።

ሆኖም “እንዲሁም አንዳንድ ዓይነት የሐሰት ክሶች የተረጋገጡ ጉዳዮች አሉ” እና አንዳንድ ካህናት ሕይወታቸውን “በዚያም ምክንያት ወድመዋል” ብሏል። አንድ ክስ “ንጹሕ የመሆንን ግምት አያስወግድም” ሲሉ ጳጳሱ አጥብቀው ገልጸው፣ “ስለዚህ ካህናት ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል፣ ወይም የተከሰሰው ሰው ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል፣ መብቱ ይከበር። ያም ሆኖ “አንዳንድ ጊዜ በተጠቂዎች ላይ ከፍተኛ ሥቃይ እንደሚያስከትል መናገሩ” ተገቢ እንደሆነ ተገንዝቧል።

ያም ሆነ ይህ፣ የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን “በጣም ጥሩ ግንዛቤ” በመጥቀስ “የፆታዊ ጥቃት ጉዳይ የቤተክርስቲያኗ ዋና ትኩረት ሊሆን አይችልም” በማለት ገልጸዋል። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የተሰማሩ “አብዛኞቹ” ሰዎች ምንም ጾታዊ ጥቃት እንዳልፈጸሙ ከገለጹ በኋላ፣ “መላው ቤተክርስቲያን በዚህ ጉዳይ ላይ ብቻ እንዲያተኩር ማድረግ አንችልም፣ ምክንያቱም ይህ ዓለም ከቤተክርስቲያን ተልእኮ ፍላጎት አንፃር ለሚፈልገው ትክክለኛ ምላሽ አይሆንም" ሲሉ ተናግረዋል።

ያልተለመደ ጾታዊ ግንኙነትን በተመለከተ የቤተክርስቲያኗ አቀራረብ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱም ከአመት በፊት በሲኖዶስ ውስጥ በተነሱት የሲኖዶስ ጉዳዮች ላይ ስለ ሁለቱ "ትኩስ ቁልፍ" ጉዳዮች ተጠይቀዋል-የሴቶች ሚና በቤተክርስቲያን ውስጥ እና ያልተለመደ ጾታዊ ግንኙነትን በተመለከተ የቤተክርስቲያን አቋም ምንድነው የሚለውን ማለት ነው።

የኋለኛውን በተመለከተ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በዚህ ጉዳይ ላይ መናገር “በአሁኑ ጊዜ ዕቅድ” እንደሌላቸው ገልጸው፣ ነገር ግን “በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዋልታ ረገጥነትን መቀጠል ወይም ማስተዋወቅ እንደማይፈልጉ” አክለው ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለሁሉም፣ በእስፓኒሽ ቋንቋ “ቶዶስ፣ ቶዶስ፣ ቶዶስ” የእንኳን ደህና መጣችሁ የሚለውን መልእክት እንደሚቀበሉ ተናግሯል። "ሁሉም ሰው ተጋብዟል" ሲሉ ተናግሯል፣ "ነገር ግን አንድን ሰው ወደ ውስጥ የጋበዝነው የተለየ ማንነት ስላለው ወይም ስለሌለው አይደለም። አንድን ሰው እጋብዛለሁ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ወንድ ወይም ሴት ልጆች ስለሆኑ ነው። ሁላችሁም እንኳን ደህና መጣችሁ፣ እናም እርስ በርሳችን እንተዋወቅ እና እንከባበር" ለማለት እፈልጋለሁ ሲሉ ተናግረዋል።

በላቲን ቋንቋ "Fiducia supplicans" (በልበ ሙሉነት መጸለይ) በሚል አርዕስት ይፋ የሆነው መልእክት በመጥቀስ፡- የሐዋርያዊ ቡራኬን በተመለከተ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሰነዱ “በመሠረቱ እንደሚለው፣ በእርግጥ ሁሉንም ሰው መባረክ እንደምንችል ይናገራል፣ ነገር ግን ቤተክርስቲያን የምታስተምረው ይህን ስላልሆነ የዚህን ዓይነት ቡራኬ የሥርዓተ አምልኮ አካል አድርጎ መቀበል እና የማስመሰል ዘዴን እንደማይቀበሉ" ገልጸዋል።

አንዳንድ ሰዎች “የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እንዲለወጥ፣ አመለካከቶች እንዲለወጡ ይፈልጋሉ” ሲሉ አምኗል። ይሁን እንጂ፣ “በእርግጠኝነት በቅርብ ጊዜ ውስጥ፣ ቤተ ክርስቲያን ስለ ጾታዊ ግንኙነት የምትሰጠው አስተምህሮ፣ ቤተ ክርስቲያን ስለ ጋብቻ የምታስተምረው ትምህርት የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮት ይለውጣል የሚል እምነት የለኝም ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ቀደም ሲል ስለ ጋብቻ እንደተናገሩት “ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩበት ጊዜ እንዳደረጉት ሁሉ፣ ቤተሰብ ወንድና ሴት በቁርጠኝነት፣ በጋብቻ ሥርዓተ ሕብረት የተባረከ ነው” በማለት ተናግሯል።

በቤተክርስቲያን ውስጥ የሴቶች ሚና

እንዲሁም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ የሴቶችን የክህነት ሹመት በተመለከተ የቤተክርስቲያኗን አቋም ይለወጣል ብለው እንደ ማያስቡ ተናግረዋል።  በተለይም ሴቶችን በድቁና ማዕረግ ሹመት እድልን በተመለከተ፣ “እኔ፣ በአሁኑ ጊዜ፣ በርዕሱ ላይ የቤተክርስቲያንን ትምህርት የመቀየር ሃሳብ የለኝም" ብለዋል።

በተመሳሳይ ጊዜ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ “ሴቶች በቤተክርስቲያኗ ሕይወት ውስጥ በብዙ መልኩ የሚያበረክቱትን ስጦታዎች በመገንዘብ፣ በቤተክርስቲያኗ ሕይወት ውስጥ በተለያዩ ደረጃዎች ላይ ለሚገኙ አንዳንድ የመሪነት ሚናዎች ሴቶችን በመሾም የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ፈለግ ለመቀጠል ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።

ር.ሊ.ጳ. ሊዮ አሥራ አራተኛ ከጋዜጠኛ ኤሊዝ አን አለን ጋር የነበራቸው ቆይታ
ር.ሊ.ጳ. ሊዮ አሥራ አራተኛ ከጋዜጠኛ ኤሊዝ አን አለን ጋር የነበራቸው ቆይታ   (CRUX)

የቅድስት መንበር የገንዘብ ነክ ሁኔታ

የቅድስት መንበር የፋይናንስ ሁኔታን በተመለከተ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ “እስካሁን እንዴት ጉዳዩን መያዝ እንዳለብኝ አላውቅም፣ ነገር ግን አንዳንድ ግልጽ ሐሳቦችን እያገኘሁ ነው” ብለዋል።

እ.አ.አ በ2024 ዓ.ም የሒሳብ ሪፖርታቸው ላይ የቅድስት መንበር የፋይናንስ አስተዳደር (APSA) የተዘገበው የ60 ሚሊዮን ዩሮ ትርፍን ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮችን ገልጸዋል። በተመሳሳይ ጊዜ፣ ለቫቲካን ሠራተኞች የጡረታ ፈንድ (“መታየት ያለበት”) እና የኮቪድ ቀውስ “ለቫቲካን ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ከሆኑት መካከል አንዱ በሆነው በቫቲካን ሙዚየሞች ላይ ምን ተጽዕኖ እንዳሳደረ” ማወቅ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ግን “በቅርብ ዓመታት ከተደረጉት የተሳሳቱ ምርጫዎች መራቅ አለብን” ሲሉ በለንደን የተካሄደውን የአንድ የሕንፃ ግዢ በመጥቀስ የፍርድ ቤት ክርክር “ታላቅ ትኩረት” የሳበ መሆኑን ጠቅሰዋል። "በዚያ ምክንያት ስንት ሚሊዮን ጠፋ!" ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በጉዳዩ እጅግ በጣም አዝነዋል።

በተመሳሳይ ጊዜ፣ በቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አዲስ የፋይናንስ ቁጥጥር ስርዓት ለመዘርጋት ቀደም ሲል የተወሰዱትን “ጉልህ እርምጃዎች” ጠቁመዋል። አክለውም  "እኔ ዘና ማለት እንችላለን እያልኩ አይደለም ቀውሱ አብቅቷል ማለት አይቻልም ብለዋል። ቀውሱ ያበቃ አይመስለኝም ፣ በዚህ ላይ መስራታችንን መቀጠል አለብን ብዬ አስባለሁ ፣ ግን በዚህ ምክንያት እንቅልፍ አላጣሁም ፣ እና የተለየ መልእክት ማስተላለፍ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።

የኩሪያ ተሐድሶዎች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የሮማን ኩሪያ (ሮማን ኩሪያ፣ ኩሪያ ሮማና በመባል ይታወቃል፣ የተለያዩ የቫቲካን ቢሮዎች ቡድን፣ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣን ላይ የሚገኙት የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን ዕለት ተዕለት ተግባር የሚያጉዙ እና የሚረዱ የተለያዩ ጳጳሳዊ ጽ/ቤቶችን እና ምክር ቤቶችን አቅፎ የያዘ መንበር ነው) ማሻሻያ በሚለው ርዕስ ላይ እንዳሉት “እንደማንኛውም ሰብዓዊ ድርጅት አዎንታዊ ነገሮች እንዳሉ እና መሻሻል ያለባቸው ነገሮች አሉ” በማለት በተለይ “እያንዳንዱ በቫቲካን የቅድስት መንበር ጽ/ቤት የሚሰራበትን ገለልተኛ አሠራር ማፍረስ ወይም መለወጥ” የሚለውን አስፈላጊነት አጉልተዋል። አንዳንድ ጊዜ የውይይት እና የመግባቢያ እጦት እንዲፈጠር ስለሚያደርግ እና አንዳንድ ጊዜ “በቤተክርስቲያኗ አስተዳደር ላይ ትልቅ ውስንነት እና ጉዳት” ስለምያስከትለው “የተናጥል አስተሳሰብ” ዓይነት ስጋት እንዳላቸው ገልጿል።

የላቲን ቅዳሴ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በተጨማሪም "የዚህ ጉዳይ አካል እንደ አለመታደል ሆኖ የዋልታ ረገጥነት ሂደት አካል ሆኗል - ሰዎች የአምልኮ ሥርዓቱን ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮችን ለማራመድ ሰበብ አድርገው ተጠቅመዋል" በማለት ለ "ባህላዊ የላቲን ቅዳሴ" ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

እርሳቸው ገና ከ“የትሪደንቲን ሥርዓተ አምልኮ ተከታይ ተሟጋች የሰዎች ቡድን ጋር ቁጭ ብለው መነጋገር እንዳልቻሉ አምኗል” ነገር ግን “በቅርቡ አንድ እድል ይመጣል ፣ እናም ለዚያም አጋጣሚዎች እንደሚኖሩ እርግጠኛ ነኝ” ብለዋል ። አክለውም “ነገር ግን እኔ የማስበው ጉዳይ ነው፣ ምናልባት ከሲኖዶስ ጋር ተቀምጠን መነጋገር አለብን” ብለዋል።

የውሸት ዜና እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ

ከቤተክርስቲያን ጉዳይ ባሻገር፣ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ጋር የተደረገው ቃለ ምልልስ “አጥፊ” በማለት የገለጹትን “የውሸት ዜና” መስፋፋትን ጨምሮ ጉዳዮችን ተመልክቷል። እናም የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ ጉዳይ በተመለከተ፣ ቅዱስ አባታችን “የሰውንና የሰውን ልጅ ዋጋ ፈጽሞ ወደ ጎን በመተው በሰው ሰራሽ አብርኾት ውስጥ ኢንቨስት ስለሚያደርጉ ብዙ ባለጸጎች” አሳስቧቸዋል።

“የሰው ልጅን ዋጋ” ሙሉ በሙሉ ችላ እያለ “እጅግ ባለጸጎች” ኢንቨስት እያደረጉ ባሉበት ቤተክርስቲያን እዚያ መናገር አለባት ብዬ አስባለሁ። "ቤተክርስቲያኗ ካልተናገረች ወይም አንድ ሰው ስለዚህ ጉዳይ የማይናገር ከሆነ - ነገር ግን ቤተክርስቲያን በእርግጠኝነት እዚህ ካሉት ድምፆች አንዷ መሆን አለባት - አደጋው ዲጂታል አለም በራሱ መንገድ ይሄዳል እና እኛ አሻንጉሊቶች እንሆናለን ወይም በመንገድ ዳር እንቀራለን" የሚለው እንደ ሆነ አክለው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ስለ "ጥልቅ ሐሰተኛ" ዜና ችግሮች ተጠይቀው ማንኛውም ሰው ከሊቀ ጳጳሱ ጋር የግል ግንኙነት እንዲኖረው "አርቴፊሻል ጳጳስ" ለመፍጠር ፈቃድ መጠየቃቸውን አስታውሰዋል። “ ‘ያንን አልፈቅድም’ አልኩ፣” እናም አክለውም፣ “በአቫታር መወከል የሌለበት ሰው ካለ፣ ጳጳሱ በዝርዝሩ ውስጥ ይገኛሉ" ብዬ መልሼ ነበር ሲሉ መናገራቸውም ተገልጿል።

19 Sep 2025, 14:37