ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የጊኒ ቢሳው ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንትን በቫቲካን ተቀብለዋቸው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የጊኒ ቢሳው ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንትን በቫቲካን ተቀብለዋቸው  (@VATICAN MEDIA)

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የጊኒ ቢሳው ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንትን ተቀብለው አነጋገሩ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የጊኒ ቢሳው ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎን ሰኞ መስከረም 19/2018 ዓ. ም. በቫቲካን ተቀብለው አነጋግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ቅዱስነታቸው ከፕሬዚደንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ ጋር ባደረጉት ውይይት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለሀገሪቱ የጋራ ጥቅም የምታበረክተውን አስተዋፅኦ አስታውሰዋል።

የጊኒ ቢሳው ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ የቅድስት መንበር መግለጫ ክፍል፥ ፕሬዚደንቱ ከቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን እና በቫቲካን የመንግሥታት ግንኙነት ምክትል ዋና ጸሐፊ ሞንሲኞር ሚሮስላው ስታኒስላው ዋክሆውስኪ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን አስታውቋል።

መግለጫው በቅድስት መንበር እና በጊኒ ቢሳው ሪፐብሊክ መካከል ያለው መልካም የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በምዕራብ አፍሪቃ ሀገር ውስጥ በተለይም በትምህርት እና በጤና አጠባበቅ ዘርፍ የምታበረክተውን አስተዋፅዖ በማስመልከት በጎ ውይይቶችን ማድረጋቸውን አስታውቋል።

ለአንዳንድ የአገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ትኩረት በመስጠት እንዲሁም በአሁኑ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የሃሳብ ልውውጥ መደረጉን መግለጫው አክሎ ሳታውቋል።

 

29 Sep 2025, 16:37