ፈልግ

የዓለም አቀፉ ጋኔን አስወጪዎች ማኅበር ስብሰባ የዓለም አቀፉ ጋኔን አስወጪዎች ማኅበር ስብሰባ  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለጋኔን አስወጪዎች 'አገልግሎታችሁ አስፈላጊ እና ረቂቅ ነው' ማለታቸው ተገለ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከሮም ከተማ ወጣ ብሎ በተካሄደው የዓለም አቀፉ ጋኔን አስወጪዎች ማኅበር ስብሰባ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ተሳታፊዎች በክፉ መንፈስ የሚሠቃዩትን ምእመናን የነፃነት እና የመጽናኛ ጸሎት በማድረግ እንዲሸኟቸው አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ማክሰኞ ዕለት መስከረም 13/2018 ዓ.ም በሮም አቅራቢያ በሚገኘው ሳክሮፋኖ በሚገኘው “Fraterna Domus” መንፈሳዊ ማእከል ውስጥ በ15ኛው ዓለም አቀፍ የጋኔን አስወጪዎች ማኅበር በተካሄደው 15ኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ለተሰበሰቡ ካህናት የምስጋና መልእክት መላካቸው የተገለጸ ሲሆን ስብሰባው ወደ 300 የሚጠጉ ካህናት እና ከሁሉም አህጉራት የተውጣጡ ረዳቶቻቸው ጭምር ተሳታፊ እንደ ነበሩ ተገልጿል።

በክፉ መንፈስ ላይ ድል ማድረግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የጋኔን ማስዋወጣት አገልግሎት “ረቂቅ” ቢሆንም “በጣም አስፈላጊ ነው” በማለት ካህናትን በማበረታታት “እንደ የነጻነት እና የመጽናናት አገልግሎት ሆነው እንዲኖሩት፣ በክፉ መንፈስ የተያዙትን ሰዎች፣ እና ምእመናን በጸሎትና የክርስቶስን ውጤታማ መገኘት በመማጸን እንዲኖሩት በማበረታታት (...) ጌታ በሰይጣን ላይ ድልን እንዲያገኙ እንዲረዳቸው ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አበረታተዋል።

ጉባኤው የመደማመጥ እና የማሰላሰል ጊዜያትን ያካተተ ሲሆን የጋኔን ማስወጣት አገልግሎት አስፈላጊነት እንደ "ቤተክርስቲያኗ ለሚሰቃዩ ወንድሞች እና እህቶች ያላትን ፍቅር የሚያሳይ ተጨባጭ ምልክት" እንደሆነ የተረጋገጠበት አገልግሎት ነው ያሉት የዓለም አቀፉ ጋኔን አስወጪዎች ማኅበር ፕሬዘደንት አባ ካሬል ኦርሊታ፣ አብራርተዋል።

በወቅቱ በተካሄደው መስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት በሣክሮፋኖ በተከበረበት ወቅት በቫቲካን የመለኮታዊ ሥርዓተ አምልኮና የቅዱሳን ምስጢራትን ጉዳይ የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አርተር ሮቼ፣ በዲያብሎስ ምክንያት የሚሠቃዩትን ሰዎች መፈወስ እንደሚገባ እና ከዚህ በሽታ የተፈወሱትን እያጽናናን አብሮ የመጓዝ አስፈላጊነት ላይ ያተኮሩ ሲሆን በሥቃያቸውም በክርስቶስ መከራ ውስጥ እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል።

24 Sep 2025, 13:22