ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በእስያ በታይፎን አውሎ ንፋስ ለተጎዱ ሰዎች ጸሎት ማድረጋቸው ተገለጸ!
የካታኪስቶች ኢዮቤልዩ ቅዳሴ ማብቂያ አካባቢ እና የቀትር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማድረጋቸው በፊት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምእመናን ንግግር አድርገዋል።
የቅዱስነታቸው ሐሳብ በተለይ በእስያ አህጉር ላይ ያተኮረ የነበረ ሲሆን እዚያም “በጣም ኃይለኛ አውሎ ንፋስ” በበርካታ ክልሎች፣ በተለይም ፊሊፒንስን፣ የታይዋን ደሴትን፣ የሆንግ ኮንግ ከተማን፣ የጓንግዶንግ ክልልን እና ቬትናምን መምታቱን" ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል፣ “በተለይም ድሆች፣ ለተጎጂዎች፣ ለጠፉት፣ ለተፈናቀሉ ቤተሰቦች፣ ለችግር የተዳረጉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች፣ እንዲሁም ለነፍስ አድን ሠራተኞችና የሲቪል ባለሥልጣናት ያለኝን ቀረቤታ እና ጸሎቴን አረጋግጣለሁ" ብለዋል።
"እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር እንዲያምን እና ለሌሎች አጋርነቱን እንዲያሳዩ እጋብዛለሁ ። ሁሉንም ችግሮች ለማሸነፍ ጌታ ብርታትን እና ድፍረትን ይስጠን" ማለታቸው ተገልጿል።
በያዝነው አመት ጠንካራው ነው የተባለው የታይፎን ራጋሳ የተሰኘው አውሎ ንፋስ በጓንግዶንግ ብቻ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ለቀው እንዲወጡ አድርጓል። ከደረሰው ከፍተኛ ጉዳት፣ ጎርፍ፣ የመብራት መቆራረጥ እና የመሬት መንሸራተት በተጨማሪ በፊሊፒንስ ቢያንስ 25 እና በታይዋን 14 ሰዎች ህይወታቸውን አጥቷል።
