የስልሳ ዓመታት የ'ኖስትራ አኤታቴ' የውይይት ምዕራፍ
"ኖስትራ አኤታቴ" የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ አንዱ ሰነድ ሲሆን ትርጉሙም "በእኛ ዘመን" ማለት ነው። ዋናው ዓላማው በካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና ክርስቲያን ባልሆኑ የሃይማኖት ተቋማት፣ በተለይም በአይሁድ እምነት መካከል ያለውን ግንኙነት በአክብሮት፣ በመተማመን እና በውይይት አቀራረብ እንደገና መግለጽ ነው። ይህ ሰነድ እ.አ.አ በ1965 ዓ.ም የጸደቀው ፀረ-ሴማዊነትን በማውገዝ እና ሁለንተናዊ ወንድማማችነትን በማስፋፋት ታሪካዊ የለውጥ ምዕራፍን የከፈተ ሂደት ነበር።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
እ.አ.አ ጥቅምት 28/1965 ዓ.ም በወቅቱ በነበሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛ የተፈረመው "ኖስትራ አኤታቴ" (በእኛ ዘመን) የተሰኘው የስምምነት ሰነድ መግለጫ ለሁሉም ሕዝቦች በሰላም ስም የመገናኘት እና የመወያየት ባህል መሠረት ጥሏል።
ለ60 ዓመታት የዘለቀ ጉዞ፡- የስምምነት ሰነድ "ኖስትራ አኤታቴ" ታሪክ ይህም፣ በሰነዱ ቃላት፣ በንግግሮች እና በተከታታይ ሊቃነ ጳጳሳት በሚፈጽሟቸው ተግባሮች እና በሚገልጿቸው ምልክቶች ለምሳሌ- ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በሮም ከተማ የሚገኘውን የአይሁዳዊያን ምኩራብ እና በደማስቆ ወደሚገኘው የኡማያድ መስጊድ ያደረጉትን ጉብኝቶች አንስቶ እስከ የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በኢራቅ ወደ ከለዳውያን ኡር እና ወደ ሞንጎሊያ በተደረጉ ሐዋርያዊ ጉብኝቶች በተለያዩ ክርስቲያን ባለሆኑ የሃይማኖት ተቋማት መካከል ያለው ግንኙነት እንደገና እንዲሻሻል የበኩላቸውን አስተዋጾ አድርገዋል።
30 Oct 2025, 15:19
