ፈልግ

ንጉሥ ቻርልስ በሲስቲን የጸሎት ቤት ውስጥ በተደርገው የኅብረት ጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል!

ንጉሥ ቻርልስ ሳልሳዊ እና ንግሥት ካሚላ በቫቲካን ይፋዊ የመንግሥት ጉብኝታቸው አካል በመሆነው ለእኩለ ቀን ጸሎት በሲስቲን የጸሎት ቤት ውስጥ ከሊቀ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ጋር የተገናኙ ሲሆን - ይህም በአንግሊካን-ካቶሊክ ግንኙነት ውስጥ ታሪካዊ ወቅትን እንደምያመልክት መሆኑ ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በማለዳው በሐዋርያዊ ሕንጻ ውስጥ ከተገናኙ በኋላ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፣ ንጉሥ ቻርልስ 3ኛ እና የታላቋ ብሪታንያ ንግሥት ካሚላ በሲስቲን የጸሎት ቤት ውስጥ ለአምልኮ ሥነ ሥርዓት ተሰብስበው ነበር። 98ኛው የዮርክ ሊቀ ጳጳስ እና በእንግሊዝ ሊቀ ጳጳስ - በእንግሊዝ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሁለተኛው ከፍተኛ ጳጳስ - ሊቀ ጳጳስ እስጢፋኖስ ኮትሬል በስፍራው መገኘታቸውም ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቀ ጳጳሱ እና ሊቀ ጳጳሱ የቀትር የመዝሙረ ዳዊት ጸሎት በጋራ ያደርጉ ሲሆን የወንጌል ንባብን ያካተተ የቀትር ጸሎት መርተዋል። የሚካኤል አንጄሎ የጥበብ ሥራዎች የተነሳ በብርሀን የተከበበው የጸሎት ቤት በበርካታ የአምልኮ ሥነ ሥርዓቶች እንግዶች ተሞልቷል፤ ከእነዚህም መካከል የዌስትሚኒስተር ሊቀ ጳጳስ እና የእንግሊዝ እና የዌልስ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት ካርዲናል ቪንሰንት ኒኮልስ እና የስኮትላንድ ኤጲስቆጶስን ወክለው የቅዱስ አንድሪያስ እና የኤድንበርግ ሊቀ ጳጳስ ሊዮ ኩሽሊ በሥፍራው ተገኝተዋል።

ታሪካዊ ጉብኝት

ይህ ጉብኝት በአንግሊካን-ካቶሊክ ግንኙነቶች ውስጥ ታሪካዊ ወቅት ነበር - ይህም በ500 ዓመታት ውስጥ ያልተከሰተ ነው። ጉዞው ሁለት ጭብጦች ነበሩት፡ የክርስቲያን አንድነት እና ለአካባቢ እንክብካቤ እንዲደረግ ግንዛቤ በድጋሚ መፍጠር።

መጀመሪያ ላይ እ.አ.አ የካቲት ወር 2025 ዓ.ም የታቀደው ጉብኝቱ በቀድሞ ርዕሰ ሊቀ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጤና መታወክ ምክንያት ተሰርዟል። ከዓላማዎቹ አንዱ ንጉሥ ቻርልስ እና የአርጀንቲና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የ 'ሎዳቶ ሲ’ ጳጳሳዊ መልእክት ከታተመ ከአስር ዓመታት በኋላ ለፍጥረት እንክብካቤ ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ማጉላት ታስቦ የታቀደ ነበር።

ከዚህም በላይ፣ በላቲን እና በእንግሊዝኛ የሚካሄደው የሥርዓተ አምልኮ ሥነ ሥርዓት፣ በቫቲካን እና በእንግሊዝ መካከል ባለው ጥሩ ግንኙነት ላይ የተገነባ ነው። እንዲሁም የእንግሊዝ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ገዥ እንደመሆናቸው መጠን ለረጅም ጊዜ በሃይማኖት መካከል ለመሳተፍ ቁርጠኛ የነበሩትን የንጉሥ ቻርልስን ምኞት ያሟላል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እና ንጉሥ ቻርለስ  በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እና ንጉሥ ቻርለስ በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (@Vatican Media)

በሁለት እምነቶች መካከል ድልድይ

ከጸሎት ሥነ ሥርዓቱ የመክፈቻ መዝሙር፣ የክርስቲያን አንድነት እና የክርስቲያን ሕብረት ጭብጥ ግልጽ ነበር። የመጀመሪያው ጽሑፍ የተጻፈው በሚላን በሚገኘው የቤተክርስቲያኗ ዶክተር በቅዱስ አምብሮስ ነበር። የተተረጎመው ወደ ካቶሊክ እምነት ከመቀየሩ በፊት ለግማሽ ሕይወቱ የአንግሊካን እምነት ተከታይ በነበሩት በቅዱስ ጆን ሄንሪ ኒውማን ነበር።

ንጉሥ ቻርልስ እ.አ.አ በ2019 ዓ.ም የእንግሊዝ የሃይማኖት ሊቅ የቀኖና ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል። ቅዱስ ጆን ሄንሪ ኒውማን በሕዳር 1/2025 ዓ.ም በርዕሰ ሊቀ ጳጳስ ሊዮ የቤተክርስቲያኗ ዶክተር ተብሎ ሊጠራ ቀጠሮ ተይዟል።

ይህንን የኅብረት ድባብ በመቀጠል፣ ጸሎት ቤቱ በዊንዘር ካስል በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት ቤት በምሽት በንጉሥ ቻርልስ እና በንግሥት ካሚላ የተጋበዙት የቅዱስ ጄምስ ቤተ መንግሥት የንጉሣዊ ጸሎት ልጆች ድምፅ ተሞልቶ ነበር። ሦስቱም ቡድኖች የቀትር ጸሎት መዝሙሮችን መዘመራቸው ተገልጿል።

24 Oct 2025, 15:49