ር.ሊ.ጳ ሊዮ "ስህተቶቻችሁን ለመቀበል አትፍሩ" ማለታቸው ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በዕለቱ ቅዱስ ወንጌል ንባብ ውስጥ የተካተቱትን ሁለት ተቃራኒ ሰዎች አስታውሰዋል፤ ፈሪሳዊው በራሱ ጽድቅ የሚተማመን ሲሆን ቀራጩ ደግሞ ኃጢአቱን የሚያውቅ ሰው ነበር ሲሉ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።
ርዕሰ ሊቀ ጳጳሱ እሁድ ዕለት ለሲኖዶስ አዘጋጆች እና ለተሳትፎ አካላት ካሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በመቀጠል እና መልአኩ ገብርኤል ማርያምን ያበሰረበት ጸሎት ከማድረጋቸው በፊት በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው ባደረጉት አስተንትኖ የፈሪሳዊው ጸሎት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እናዳሉት ከሆነ በትዕቢት እና በመንፈሳዊ ኩራት ላይ ያተኮረው፣ “ሕግን በጥብቅ ማክበርን የሚያንፀባርቅ ነው፣ ነገር ግን በፍቅር የተዋረደ ድሀ፣ ‘በመስጠት’ እና ‘ሰጥቶ በመቀበል’ ላይ የተገነባ እና ምሕረት የጎደለው ጸሎት ነው” ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
በአንጻሩ፣ የግብር ሰብሳቢው ጸሎት ለጸጋ ክፍት የሆነ ልብን ያሳያል፡ “እግዚአብሔር ሆይ፣ እኔ ኃጢአተኛ ነኝ፣ ማረኝ” እያለ ጸሎት እንዳቀረበ ተናግረዋል።
ትህትና፡ የእውነት እና የፈውስ መንገድ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ያለፈውን እና ዝናውን ቢያሳይም በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም የሚደፍር የግብር ሰብሳቢውን ድፍረት አፅንዖት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን “ራሱን በራሱ ዓለም ውስጥ አይቆልፍም፤ ላደረጋቸው ክፋ ነገሮች ራሱን አይሰጥም” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስረድተዋል። "የሚፈራበትን፣ ደህንነቱ የተጠበቀበትን፣ በሌሎች ላይ ባለው ኃይል የተጣበቀበትን ቦታ ትቶ ይሄዳል። ወደ ቤተመቅደስ የሚመጣው ያለ አጃቢ ብቻውን ነው፣ ምንም እንኳን ጨካኝ እይታ እና ሹል የሆነ ፍርድ ቢጠይቅም፣ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ ጌታ ፊት ቆሞ ነበር" ያሉት ቅዱስነታቸው “አንድ ሰው የሚድነው የአንድን ሰው መልካምነት በማሳየት ወይም ጥፋቱን በመደበቅ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ፊት፣ በራሳችን ፊት እና በሌሎች ፊት ራሱን በሐቀኝነት በማቅረብ ነው” ሲሉ አብራርተዋል።
ጳጳሱ ቅዱስ አውጉስጥኖስን በመጥቀስ፣ ፈሪሳዊው ቁስሉን በትዕቢት የሚደብቅ ከታመመ ሰው ጋር ያነጻጽረዋል፣ግብር ሰብሳቢውን ደግሞ ጉዳቱን በትሕትና ከሚያጋልጥ ሰው ጋር አነጻጽረውታል፡- “ሕመሙን ለማሳየት ያላፈረው ይህ ቀራጭ ተፈውሶ ወደ ቤቱ መሄዱ አያስደንቀንም ወይ?” ሲሉ ቅዱስነታቸው ጥያቄ አንስተዋል።
“ስህተቶቻችንን ለመቀበል አንፍራ”
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ ምእመናንን ደካማ ጎናቸውን እንዲያውቁ እና እንዳይፈሩ፣ የግብር ሰብሳቢውን ምሳሌ በመከተል “ስህተቶቻችንን ለመቀበል አንፍራ፣ ለእነሱ ማለትም ለስህተቶቻችን ኃላፊነት በመውሰድ እና ለእግዚአብሔር ምሕረት አደራ በመስጠት አንሸሽጋቸው” ሲሉ አበረታተዋል።
ይህ የትሕትና መንገድ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እንደተናገሩት ከሆነ፣ ውስጣዊ ፈውስን እና የእግዚአብሔርን መንግሥት እድገት ያመጣል ያሉ ሲሆን እርሱ የመጣው “ለትዕቢተኞች ሳይሆን ለትሑታን ነው" ሲሉ ከገለጹ በኋላ ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።
