ር.ሊ.ጳ ሊዮ አሥራ አራተኝ የክርስቶስ ትንሳኤ የሐዘን መድኅኒት ነው ማለታቸው ተገልጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በዕለቱ የተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
እርስ በርሳቸውም “በመንገድ ሳለን ሲያናግረንና መጻሕፍትንም ሲያስረዳን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን?” ተባባሉ። በዚያችም ሰዓት ተነሥተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ዐሥራ አንዱንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትንም በአንድነት ተሰብስበው አገኙአቸው። እነርሱም “ጌታ በእርግጥ ተነሥቷል፥ ለስምዖንም ታይቷል” ይሉ ነበር። እነርሱም በመንገድ የሆነውን፥ እንጀራውንም በቈረሰ ጊዜ እንዴት እንዳወቁት ተረኩላቸው (ሉቃስ 24፡32-35)።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!
የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ አንድ ሰው ማሰላሰሉን እና ማሰቡን የማያቋርጥበት ክስተት ነው፣ እናም አንድ ሰው ይህንን በመረመረ ቁጥር፣ አንድ ሰው በሚያስገርም እና በሚያስደንቅ ብርሃን በመሳብ ይደነቃል። የእውነታውን ትርጉም በራሱ ከአሉታዊ ወደ አወንታዊነት የለወጠው የህይወት እና የደስታ ፍንዳታ ነበር፣ ነገር ግን በጣም ትልቅ እና አስደናቂ ሁኔታ አልተከሰተም፣ በጣም አነስ ባለ ኃይል፣ በእርጋታ፣ በድብቅ፣ አንድ ሰው በትህትና ሊናገር በሚችለው ሁኔታ ተከስቷል።
ዛሬ የክርስቶስ ትንሣኤ በዘመናችን ካሉት በሽታዎች አንዱን ማለትም ሀዘንን እንዴት እንደሚፈውስ እናሰላስላለን። ጣልቃ ገብ እና የተስፋፋ፣ ሐዘን ከብዙ ሰዎች ዘመን ጋር አብሮ ይመጣል። ይህ የአስቸጋሪነት ስሜት ነው፣ አንዳንድ ጊዜ ጥልቅ የተስፋ መቁረጥ ስሜት፣ ይህም የአንድን ሰው ውስጣዊ ቦታ የምያውር እና ከማንኛውም የደስታ መነሳሳት በላይ የሚያሸንፍ ይመስላል።
ሐዘን የህይወትን ትርጉም እና ጉልበት ይሰርቃል፣ አቅጣጫ ወደሌለው እና ትርጉም የለሽ ጉዞ ይለውጠዋል። ይህ በጣም ወቅታዊ ገጠመኝ በሉቃስ ወንጌል (24፡13-29) ስለ ሁለቱ የኤማሁስ ደቀ መዛሙርት ዝነኛ ዘገባ ያስታውሰናል። ተስፋ ቆርጠው እና አዝነው፣ በተሰቀለው እና በተቀበረው ኢየሱስ ላይ የነበራቸውን ተስፋ እርግፍ አድርገው ትተው ኢየሩሳሌምን ለቀው ወጡ። በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ክፍል ውስጥ በጹሑፉ በመክፈቻ መስመሮች ላይ፣ ይህ ክፍል የሰውን ሐዘን ምሳሌ ያሳያል፡ ብዙ ጉልበት የፈሰሰበት አላማ መጨረሻ፣ የሕይወታቸው ዋና ነገር የሚመስለው ነገር እንደ ጠፋ ይሰማቸዋል። ተስፋቸው ጨልሟል፣ የተስፋ መቁረጥ መንፈስ ልባቸውን ሸብቦ ይዟል። ሁሉም ነገር በአጭር ጊዜ ውስጥ፣ በአርብ እና ቅዳሜ መካከል፣ በአስደናቂ የክስተቶች ቅደም ተከተል ተሞላ።
አያዎ ወይም እርስ በእርሱ የሚጋጭ የሚመስለው አስተሳሰብ በእውነት ምሳሌያዊ ነው፣ ይህ አሳዛኝ የሽንፈት እና ወደ ተራ ህይወት የመመለስ ጉዞ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀው የፋሲካ ድል፣ የብርሃን ድል በተከናወነበት በተመሳሳይ ቀን ነው። ሁለቱ ሰዎች አሁንም በዐይናቸው እና በልባቸው ላይ ታትሞ ወደሚገኘው አስፈሪው የመስቀሉ ትእይንት ለጎልጎታ ጀርባቸውን ሰጡ። ሁሉም ነገር የጠፋ ይመስላል። ዝቅተኛ መገለጫ በመያዝ እና ለዚህ ክስተት እውቅና እንዳይሰጡ ተስፋ በማድረግ ወደ ቀድሞ ሕይወታቸው መመለስ አለባቸው።
በአንድ ወቅት አንድ መንገደኛ ከሁለቱ ደቀ መዛሙርት ጋር ይቀላቀላል። ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ ነበር፣ ነገር ግን አላወቁትም። መምህሩ ብዙ ጊዜ፣ እንደሚገደል እና በሶስተኛው ቀን ከሙታን እንደሚነሳ የገባውን ቃል ኪዳን ዘንግተው ሐዘን ዓይናቸውን ሸፍኖ ነበር። እንግዳው እየቀረባቸው ሲመጣ ለሚናገሩት ነገር ፍላጎት እንዳለው ያሳያል። ጽሑፉ እንደሚናገረው፦ እርሱም “አብራችሁ እየሄዳችሁ እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሯቸው እነዚህ ነገሮች ምንድን ናቸው?” አላቸው። እነርሱም አዝነው ቀጥ ብለው ቆሙ" (ሉቃስ 24፡17)። ጥቅም ላይ የዋለው የግሪክ ቅፅል ሁሉን ያካተተ ሐዘንን ይገልፃል፣ ነፍሳቸው ሽባ ስትሆን ፊታቸው ላይ ይታያል።
ኢየሱስ ያሳዘናቸውን የሐዘን ሸክም እንዲያራግፉ ፈቀደላቸው። ከዚያም በቅንነት “እናንተ የማታስተውሉ፤ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ" (ሉቃስ 24፡25) በማለት ገሰጻቸው። እናም በቅዱሳት መጻሕፍት ክርስቶስ መከራ መቀበል፣ መሞትና መነሣት እንዳለበት በመጥቀስ ያስረዳቸው ጀመር። በሁለቱ ደቀ መዛሙርት ልብ ውስጥ የተስፋው ሙቀት እንደገና ተቀሰቀሰ፣ ከእዚያም ቀኑ ሲመሽ እና መዳረሻቸው ሲቃረብ ምስጢራዊው የጉዞ ጓደኛቸውን አብሯቸው እንዲቆይ ይጋብዙታል።
ኢየሱስ ግብዣውን ተቀብሎ ከእነርሱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ። ከዚያም እንጀራውን ወስዶ ቆርሶ ያቀርባል። በዚያን ጊዜ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት አወቁት... ነገር ግን ወዲያው ከዓይናቸው ተሰወረ (ሉቃስ 24፡ 30-31)። የተሰበረ የሚመስለው የሐዘን ምልክት የልባቸውን ዓይኖች እንደገና ይከፍታል፣ በተስፋ መቁረጥ የጨለመውን ራዕይ እንደገና ያበራል። እናም ከዚያ ሁሉም ነገር ግልጽ ይሆናል፥ የጋራ ጉዞ፣ የዋህ እና ሃይለኛ ቃል፣ የእውነት ብርሃን... ወዲያው ደስታ ፈነጠቀ፣ ጉልበት ወደ ደከመው አካላቸው ይመለሳል፣ እናም ምስጋና ወደ ትውስታቸው ይመለሳል። ለሌሎቹም ሁሉን ነገር ለመናገር ሁለቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
“ጌታ በእውነት ተነሥቷል” (ሉቃስ 24፡34) በማለት ያውጃሉ። በዚህ ተውሳከ ግስ ቃል ውስጥ፣ በእርግጥ፣ እንደ ሰው የታሪካችን የተወሰነ ውጤት ተሟልቷል። በፋሲካ ቀን ክርስቲያኖች የሚለዋወጡት ይህ ሰላምታ በአጋጣሚ የተከሰተ አይደለም። ኢየሱስ የተነሣው በቃል ሳይሆን በተግባር፣ በአካሉ የሕማማቱን ምልክቶች በመግለጽ፣ ለእኛ ያለው የዘላለም ሕይወት ማህተም በማሳየት ነው። የሕይወት ድል ባዶ ቃል አይደለም፣ ነገር ግን እውነተኛ፣ የሚጨበጥ እውነት ነው።
የኤማሁስ ደቀ መዛሙርት ያልተጠበቀ ደስታ ገጠማቸው፣ ከባድ በሚሆንበት ጊዜ ለእኛም ቢሆን ይህ ረጋ ያለ ማሳሰቢያ ይሁንልን። የእኛን አመለካከት በእጅጉ የሚቀይር፣ የሐዘንን ባዶነት የሚሞላው ተስፋን የሚያጎናጽፈው ትንሣኤው ነው። በልባችን መንገዶች ላይ ከሙታን የተነሣው ጌታ ከእኛ ጋር እና ለእኛ ይጓዛል። የቀራንዮ ጨለማ ቢሆንም የሞትን ሽንፈት ይመሰክራል፣ እናም የህይወት ድልን ያረጋግጣል። ታሪክ አሁንም ተስፋ የሚያደርጉ ብዙ መልካም ነገሮች አሉት።
ትንሳኤውን ማወቅ ማለት ለአለም ያለውን አመለካከት መለወጥ ማለት ነው፣ ያዳነን እና የሚያድነንን እውነት ለማወቅ ወደ ብርሃን መመለስ ማለት ነው። እህቶች እና ወንድሞች፣ ከሙታን በተነሳው የኢየሱስ ፋሲካ ላይ በየቀኑ ነቅተን እንጠብቅ። እሱ ብቻ የማይቻለውን ነገር እውን ያደርገዋልና!
