ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሰላም ህልም ብቻ ሳይሆን እውን ሊሆን የሚችል ነገር ነው ማለታቸው ተገለጸ!
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ሮም፣ ሲንቲ እና ተጓዦች ዘላኖች ኢዩቤሊዩ ላይ ሰላም ህልም ብቻ ሳይሆን እውን ሊሆን የሚችል ነገር ነው ማለታቸው ተገልጿል። (ሮም፣ ሲንቲ እና ተጓዢ ዘላኖች ከፍተኛ የሆነ ስደት እና አድልዎ የገጠማቸው የተለያየ ታሪክ እና ባህል ያላቸው ተዛማጅ የጎሳ ቡድኖች ናቸው። በታሪክ ዘላኖች ሲሆኑ፣ አብዛኞቹ አሁን የዘላን ሕይወታቸውን በመተው በአንድ ሥፍራ መቀመጥ ጀምረዋል። "ሮም" ሲንቲን ጨምሮ ለተለያዩ ንኡስ ቡድኖች የሚያገለግል የወል ቃል ሲሆን እንደ አይሪሽ ተጓዦች፣ የስኮትላንድ ጂፕሲ ተጓዦች እና የእንግሊዝ ሮማን ጂፕሲዎች ያሉ የተለያዩ የተጓዥ ዘላን ቡድኖችን ለማካተት እንደ ጃንጥላ ቃል ሆኖ የገለግላል)።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በሮም፣ በሲንቲ እና በተጓዥ ዘላኖች ህዝቦች ኢዮቤልዩ ላይ ተገኝተው የቤተክርስቲያኗ የሐዋርያዊ እንክብካቤ አገልግሎት ለተጓዥ እና ዘላን ህዝቦች፣ የቤተሰብን፣ የሥራ እና የጸሎትን ክብር እንዲቀበሉ ጋብዘዋል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ሮማ፣ ሲንቲ እና ተጓዢ ዘላን ሕዝቦች ቅዳሜ ጥቅምት 08/2018 ዓ.ም ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ጋር በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሽ የሮም፣ የሲንቲ እና የተጓዥ ዘላን ህዝቦች ኢዮቤልዩ ለማክበር በአዳራሹ መገተኛቸው ተገልጿል።
በስብሰባው እና በግንኙነቱ ወቅት ከህጻናትና ወጣቶች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስለ ጦርነት ለተነሳው ጥያቄ ሁሉም ሰው ሰላም በእውነት የሚቻል መሆኑን እንዲያምን ጋብዘው በራሳችን፣ በቤተሰባችን እና በአካባቢያችን ባሉ ሰዎች መካከል ሰላም እንድንፈጥር አሳስበዋል።
“ሁላችንም ጦርነት በሌለበት ዓለም ውስጥ መኖር እንፈልጋለን፣ እናም ሁልጊዜ የሰላም አራማጆች፣ የድልድዮች ገንቢዎች፣ ሰላም እውን ሊሆን እንደሚችል ራሳችንን አጥብቀን ማሳመን ያለብን ሰዎች- ይህ ህልም ብቻ ሳይሆን በሰላም መኖር እንደምንችል የሚገልጽ እውነታ ነው” ብሏል።
“ተስፋ እየተንቀሳቀሰ ነው— አባቴ ከቦታ ወደ ቦታ በመዞር የሚኖር ሶርያዊ ነበር” (ዘዳ. 26፡5) በማለት በንግግራቸው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የኢዮቤልዩን ጭብጥ አስታውሰዋል።
“ዛሬ ሁላችንም በጉዟችን እንደታደስን ይሰማናል ለጳጳሱ ባመጣችሁት ስጦታ፡ ጠንካራ እምነት፣ በእግዚአብሔር ብቻ ላይ ያላችሁ የማይናወጥ ተስፋ፣ በህብረተሰቡ ዳርቻ ላይ ሆናችሁ ለምትኖሩት የህይወት ችግር የሚጋፈጥ ጽኑ እምነት" እንዳላችሁ አስመስክራችኋል ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የኢዮቤልዩ በዓል እ.አ.አ በ1965 ዓ.ም ጳጳስ ጳውሎስ ስድስተኛ በፖሜዚያ (አርሜኒያ) ከተጓዙት ሕዝቦች ጋር ታሪካዊ ስብሰባ ካደረጉ ከ60 ዓመታት በኋላ መሆኑን አስታውሰው የእመቤታችንን ሥዕል “የሮማ፣ የሲንቲ እና የመንገደኞች ንግሥት” በማለት አክሊል በእመቤታችን ምስል ላይ ማስቀመጣቸውን ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።
ቤተክርስቲያኗ ከማህበረሰባቸው ጎን ለመራመድ ያላትን ፍላጎት በእረኝነት አገልጋዮች በኩል ቅዱስነታቸው አረጋግጧል።
ተጓዥ ዘላን ሕዝቦች፣ “በእግዚአብሔር ብቻ መታመን፣ ከዓለማዊ በጎ ነገር ጋር ላለመያዝ፣ እና በሥራችሁ እና በቃላቶቻችሁ ምሳሌ የሚሆን እምነትን ለማሳየት” ለሚሉት ሦስት አስፈላጊ እውነቶች ይመሰክራሉ ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
በሌሎች ማህበረሰቦች ወደ ጎን በመጣላችሁ ወደ ከተማ፣ የመብት፣ የትምህርት እና የባህል ተሳትፎ እንዳይኖራችሁ በዳርቻዎች ዙሪያ እንድትኖሩ ስላደረጓችው ህዝቦቻቸው በጉዞና በዘላንነት ከአንድ ሺህ ዓመታት በላይ እንደተጓዙ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስታውቀዋል።
“ነገር ግን፣ እናንተን ያገለላችሁ እና ያለ ሰላምም ሆነ ያለ አቀባበል እንድትንከራተቱ ያደረጋችሁ የሕብረተሰቡ አርአያ፣ ባለፈው ምዕተ ዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቁን የማህበራዊ ኢፍትሃዊ ድርጊቶችን ያስመዘገበው ይኸው ሞዴል ነው፡ በሰዎችና በህዝቦች መካከል ከፍተኛ የሆነ ኢ-ኮኖሚያዊ፣ ኢ-እኩልነት፣ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ የገንዘብ ግሽበት ቀውሶች፣ የአካባቢ አደጋዎች እና ጦርነቶች ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ እየተንጸባረቀ ይገኛል ሲሉ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በመቀጠል ሮም፣ ሲንቲ እና ተጓዥ ዘላን ህዝቦች እ.አ.አ በ2019 ዓ.ም የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ያቀረቡትን አቤቱታ እውን እንዲያደርጉ እና እንዲታዘዙ ጋብዟቸው ነበር፣ በዚህ መልዕክታቸው ምንም ዓይነት ቅሬታ እንዳይሰማቸው ይልቁንም “በቤተሰብ ክብር፣ በሥራ ክብር፣ የዕለት እንጀራችሁን የማግኘት ክብር እና የጸሎት ክብር” እነዚህን ሐሳቦች ወደፊት እንያራምዱ ጠይቀዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አክለውም “የሥራ ክብር እና የጸሎት ክብር የእናንተን ያለመተማመን እና የፍርሃት ግድግዳዎች ለማፍረስ ጥንካሬ የሚሰጡ ተግባራት ይሁኑ" ሲሉ የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከዚሁ ጎን ለጎን ተጓዥ ዘላን ህዝቦች በቤተክርስቲያን የወንጌል አገልግሎትን ተቀብለው የባህላቸውን ውበት እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።
“በሚኖሩበት ቦታ ሁሉ ከሌሎች በጎ ፈቃድ ካላቸው ሰዎች ጋር እየተመላለሱ፣ ከመተማመን በዘለለ፣ የባህላችሁን ውበት ለማሳወቅ፣ እምነትን፣ ጸሎትን እና ከቅን ሥራ የሚገኘውን እንጀራ በመጋራት የወቅቱ ለውጥ ዋና ተዋናዮች ሁኑ” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።
