ፈልግ

የጣሊያን-ቫቲካን-የአየር ንብረት-ኮንፈረንስ የጣሊያን-ቫቲካን-የአየር ንብረት-ኮንፈረንስ  (AFP or licensors)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡- ለጋራ ቤታችን እንክብካቤ ማድረግ/አለማድረጋችንን እግዚአብሔር ይጠይቀናል አሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ "በአየር ንብረት ፍትሕ" ላይ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ለተሳታፊዎች ንግግር ያደረጉ ሲሆን የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ድንቅ ሥነ ምህዳር መልእክት በላቲን ቋንቋ 'ላውዳቶ ሲ' (ውዳሴ ለአንተ ይሁን) በማንፀባረቅ ጊዜው ሲደርስ እግዚአብሔር ለጋራ ቤታችን እንክብካቤ ማድረግ/አለማድረጋችንን ይጠይቀናል ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ረቡዕ ከሰአት በኋላ መከረም 21/2018 ዓ.ም የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በላቲን ቋንቋ 'ላውዳቶ ሲ' (ውዳሴ ለአንተ ይሁን) አሥረኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በላውዳቶ ሲ ንቅናቄ ባዘጋጀው የተስፋ ማሳደጊያ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ንግግር አድርገዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በንግግራቸው ለቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ውርስ ምስጋናቸውን ገልጸው፣ መልእክቱ ትምህርት ቤቶችን፣ አህጉረ ስብከትን፣ የትምህርት መርሃ ግብሮችን እና ዓለም አቀፍ ውይይቶችን እንዴት እንዳነሳሳ ጠቁመዋል።

“ተፅዕኖው እስከ ከፍተኛ ስብሰባዎች፣ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች፣ ኢኮኖሚያዊ እና የንግድ ክበቦች፣ እንዲሁም ሥነ-መለኮታዊ እና ባዮኤቲካል ጥናቶች ድረስ ተዘርግቷል” ብሏል። ከሁሉም በላይ "ለጋራ ቤታችን እንክብካቤ" የሚለው ሐረግ መደበኛ ሐረግ ሆኗል፣ በትምህርት ተቋማት ሥራ፣ በሕዝብ እና በአህጉሮች ውስጥ እንዲሁም በሕዝብ ንግግር ውስጥ ጥቅም ላይ እየዋለ የገኛል ብለዋል።

የልብ መለወጥ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ያለፉትን አስርት ዓመታት ስኬቶች ሲያስታውሱ 'በላውዳቶ ሲ' የተገለጹት ተግዳሮቶች “ዛሬ ከአሥር ዓመት በፊት ከነበሩት የበለጠ ጠቃሚ ናቸው” ሲሉ አጽንዖት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን እነዚህ ተግዳሮቶች ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ብቻ ሳይሆኑ መንፈሳዊም መሆናቸውን በመግለጽ የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “የልብ መለወጥ” ሲሉ የገለጹትን ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ልብ ጥልቅ ፍለጋ የሚካሄድበት፣ የመጨረሻው ማንነት የሚታወቅበት፣ እና ውሳኔዎች የሚፈጸሙበት ነው” በማለት ገልጿል። እውነተኛ የስነምህዳር ለውጥ ወደ ልብ በመመለስ ብቻ ነው የሚገኘው። ይህ ለውጥ፣ “መረጃን ከመሰብሰብ ወደ እንክብካቤ፣ ከአካባቢያዊ ንግግሮች ወደ በእምነት እና በአምላክ ፍቅር ወደተነሳሱ የአኗኗር ዘይቤዎች መሸጋገር ማለት ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ሁሉም አንድ ናቸው።

የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስለ አዚዚው ቅዱስ ፍራንችስኮስ የሰጡትን መግለጫ በመጥቀስ፣ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሥነ ምህዳራዊ ጉዳይ፣ ለድሆች ፍትህ፣ ማኅበራዊ ቁርጠኝነት እና ውስጣዊ ሰላም የማይነጣጠሉ መሆናቸውን አሳስበዋል።

ሊቃነ ጳጳሳቱ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ምጻረ ቃል "COP30" (የሚያመለክተው 30ኛው የፓርቲዎች የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ማዕቀፍ (UNFCCC) የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄዎችን ለመወያየት እና ለመደራደር የሚችል ትልቁ ዓለም አቀፍ ክስተት ነው። እ.አ.አ ከሚቀጥለው ሕዳር 10-21/2025 ዓ.ም ደረስ እንደ እንዲካሄድ የታቀደ ሲሆን ሥፍራውም በአማዞን ክልል ውስጥ በምትገኘው ቤሌም፣ ብራዚል ውስጥ እንደሚካሄድ ይጠበቃል። COP30 በአለም አቀፍ የአየር ንብረት ግቦች ላይ በተለይም የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀትን በመቀነስ ረገድ መግባባት ለመፍጠር እንደ ወሳኝ መድረክ ሆኖ ያገለግላል እና ከአየር ንብረት ስምምነቶች ጋር የተያያዙ ቁልፍ አመታዊ ክብረ በዓላትን ያከብራል)"COP30" እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እ.አ.አ የ2022 ዓ.ም የተካሄደውን የውሃ ኮንፈረንስን ጨምሮ መጪውን አለም አቀፍ ስብሰባዎች በጉጉት ሲጠብቁ “የምድር እና ድሆች፣ ቤተሰቦች፣ የአገሬው ተወላጆች፣ ስደተኞች እና በመላው አለም ያሉ አማኞች” ጩኸቶችን እንዲሰሙ መሪዎቹን አሳስበዋል።

መልሳችን ምን ይሆን?

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉ የሚከተለውን ጥያቄ አቅርበዋል:- “አምላክ የፈጠረውን ዓለም መከባከባችንን ወይም አለመንከባከባችንን፣ እንዲሁም ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን መከባከባችን ወይም አለመንከባከባችንን አምላክ ይጠይቀናል፤ መልሳችን ምን ይሆን?” የሚለውን ጥያቄ ካነሱ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

 

03 Oct 2025, 15:49