ር.ሊ.ጳ ሊዮ በዚህ የኮሙኒኬሽን ዘመን ማንም ሰው 'አላውቅም' ሊል አይችልም ማለታቸው ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሐሙስ መስክከረም 29/2018 ዓ.ም ግጭቶች በሚከናወኑባቸው አገራት ውስጥ ለሚሰሩ ጋዜጠኞች ክብር ሰጥተዋል። ዛሬ በጋዛ፣ ዩክሬን እና በቦምብ የተደመሰሱትን አገሮች ካወቅን የእነርሱ ዕዳ አለብን ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ዓለም አቀፋዊ የዜና ወኪል ለሆኑት በእንግሊዜኛው "MINDS International" አውታረ መረብ አባላት ንግግር ባደረጉበት ወቅት “እጅግ የሚገርሙ የዓይን ምሥክሮች ዘገባዎች፣ መረጃ ከእውነትና ከሰብዓዊ ክብር ጋር ተቃራኒ ለሆኑ ዓላማዎች ጥቅም ላይ እንዳይውል ለማድረግ የሚጥሩ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች የዕለት ተዕለት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ” በማለት ገልጸዋቸዋል።
በአመጽ ግጭት እና የተሳሳቱ መረጃዎች በታየበት ዓለም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ዓለምን በመረጃ እንዲከታተሉ ለማድረግ፣ በባልደረቦቻቸው ላይ የሚያደርሱትን አደጋ እንዲገነዘቡ እና ከፍተኛውን የአቋም እና የእውነት ደረጃዎችን በማክበር መስዋዕትነታቸውን እንዲያከብሩ ጠይቀዋል።
ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም
ከዚህ በመነሳት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በግፍ የታሰሩ ወይም የሚሰደዱ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ የረጅም ጊዜ ጥያቄያቸውን በድጋሚ አቅርበዋል። "የጋዜጠኝነት ስራ መስራት እንደ ወንጀል ሊቆጠር ፈጽሞ አይችልም" ሲሉ አጥብቆ ተናግሯል። "መጠበቅ ያለበት መብት ነው" ሲሉም አክለው ተናግረዋል።
በፖለቲካዊ ወይም ርዕዮተ ዓለም ስም መረጃን ለማፈን ወይም ለማጭበርበር የሚደረጉ ሙከራዎችን ያስጠነቀቁት ቅዱስነታቸው፣ ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ባለሙያዎች ጫናዎች ቢደርስባቸውም ጥሪያቸውን አጥብቀው እንዲይዙ ጠይቀዋል፡- “አገልግሎታችሁ ብቃትን፣ ድፍረትንና የሥነ ምግባርን ስሜት ይጠይቃል" ብለዋል።
መረጃ የህዝብ ጥቅም ነው
የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ንግግር ዓለም አቀፋዊ ክስተቶች "ልዩ ማስተዋልን እና ኃላፊነትን" በሚጠይቁበት ጊዜ እና በዚህ ጊዜ የመገናኛ ብዙሃን ህሊናን በመፍጠር እና ሂሳዊ አስተሳሰቦችን በመደገፍ ሚናቸው በጣም አስፈላጊ ሆኖ በማያውቅበት ወቅት ነው ... ወይም የበለጠ አስጊ ሥራ እንዲሆን በተደረገበት ዓለም ውስጥ ነው።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በመቀጠል "በኮሙኒኬሽን ዘመን የዜና እና የሚዲያ ኤጀንሲዎች በችግር ጊዜ ውስጥ ናቸው" የሚለውን ሐሳብ እንደሚጋሩ የገለጹት ቅዱስነታቸው ብዙ ጊዜ በእውነት እና በውሸት መካከል ያለው መስመር እየደበዘዘ ስለሚሄድ ታዳሚዎችም በችግር ውስጥ መሆናቸውን አክለው የገለጹ ሲሆን ያም ሆኖ፣ በመረጃ በተሞላ ዓለም ውስጥ፣ “በዛሬው ጊዜ ‘አላውቅም ነበር’ የሚል ማንም የለም” ሲሉ ተናግረዋል።
መረጃ በዜጎች እና በጋዜጠኞች መካከል ኃላፊነት በተሞላበት ዘገባ እና ትብብር ሊጠበቅ የሚገባው "የህዝብ ጥቅም" ነው ሲል አሳስቧል። ህብረተሰቡ ከባድ እና ገለልተኛ ጋዜጠኝነትን በንቃት ሲደግፍ - ለሲቪክ ህይወት ጤና አስተዋፅኦ ሲደረግ "ጥሩ ክበብ" ይፈጠራል ብለዋል።
በሥነ-ምግባር የተሞላ ኮሙኒኬሽን የቀረበት ጥሪ
የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን በመጥቀስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ “ደፋር ሥራ ፈጣሪዎች፣ ደፋር የመረጃ መሐንዲሶች” እንጂ በሐሜት፣ በሐሰት መረጃ እና ፍትሐዊ ባልሆነ ፉክክር የኮሙኒኬሽን ልውውጥ እንዳይበላሽ ጥሪ አቅርበዋል። የመገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲዎች በግንባር ቀደምትነት ላይ መሆናቸውን እና ኢኮኖሚያዊ ዘላቂነትን ሚዛናዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት ትክክለኛ እና ሚዛናዊ ዘገባ ማቅረብ ያለባቸውን መንገዶች መፈለግ አለባቸው ብለዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ያስጠነቀቁትን የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ እድገትን በተመለከተ አዲስ ውስብስብ ነገርን ይጨምራል፣ አውቶሜትድ ስለተ ቀመር መረጃን እንዴት እንደሚሰጥ በሚቀርጽበት ወቅት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ የሰው ልጅን ያማከለ እንዲሆን እና በዲጂታል መሳሪያዎች ላይ ያለው ኃይል በጥቂቶች እጅ ውስጥ እንዳይዘዋወር ጥንቃቄ እንዲደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ከእውነት በኋላ ባለው ዓለም ውስጥ እውነትን መከላከል
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉ የደራሲ ሃና አረንድት የቶታሊታሪያኒዝም አመጣጥን በመጥቀስ የጠቅላይ ገዥዎች ዋና ርዕሰ ጉዳይ ርዕዮተ ዓለም ብቻ ሳይሆን ይልቁንም “በእውነት እና በልብ ወለድ መካከል ያለው ልዩነት፣ እንዲሁም በእውነት እና በሐሰት መካከል ያለው ልዩነት ከአሁን በኋላ የለም” ያለው ሰው እንደሆነ አስጠንቅቀዋል።
በዚህ ዓለም ውስጥ ጋዜጠኞች ወሳኝ ሚና እንዳላቸው አስገንዝቧል። "እናንተ በትዕግስት ጠንካራ ስራችሁን" በመቀጠል "በጥንታዊው የውሸት ጥበብ በመከፋፈል ለመገዛት ክፍፍል ለመፍጠር በሚፈልጉ ላይ እንደ መከላከያ እርምጃ መውሰድ ትችላላችሁ" ጋዜጠኞች ድህረ-እውነት እና ግምት ያለውቸውን አደጋ "የሥልጣኔ ምሽግ" ሆኖ ማገልገል አለባችሁ ብለዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ ለሚሳተፉ ሁሉ ግልጽነት፣ ተጠያቂነት እና ተጨባጭነት አስፈላጊ መሆናቸውን እና "ዓለም ነፃ፣ ጥብቅ እና ተጨባጭ መረጃን ይፈልጋል" በማለት በድጋሚ በመግለጽ ንግግራቸውን ደምድመዋል።
