ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ   (@VATICAN MEDIA)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በሜክሲኮ የጎርፍ አደጋ ሰለባ ለሆኑት ጸሎት ማድረጋቸው ተገልጿል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በሜክሲኮ በጎርፍ ለተጎዱ ሰዎች ጸሎት አድርገዋል። በየቀኑ ጥቃት ለሚደርስባቸው ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች ሁሉ እንዲጸልዩ ሁሉም ሰው እንዲተባበር አበረታተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ- ቫቲካን

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከብዙ ሺህ ምዕመናን ጋር የመልአከ ገብርኤል ጸሎት ከጸለዩ በኋላ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እ.አ.አ ከጥቅምት 6-11/2025 ዓ.ም ከባድ ዝናብ አስከፊ ጎርፍ ያስከተለበትን የምስራቅ-መካከለኛው ሜክሲኮ ሕዝብ ያስታወሱ ሲሆን ቢያንስ 76 ሰዎች ሞተዋል፣ ወደ ሶስት ደርዘን የሚጠጉ ሰዎች ጠፍተዋል፣ እና ከ100 በላይ ማህበረሰቦች  አሁንም በአጣብቂኝ ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ለቤተሰቦቻቸው እና በዚህ አደጋ ምክንያት ለሚሰቃዩ ሁሉ” ጸሎት ያደረጉ ሲሆን፣ በጥቃቱ ሰለባ ለሆኑ ዘመድ አዝማድ መጽናናትን ተመኝተዋል፣ በእመቤታችን ምልጃ አማካኝነት ለሞቱት ሁሉ ነፍሳቸውን ለጌታ በአደራ ሰጥተዋል።

ከዚህም በላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በጦርነትና በዓመፅ በተከበቡ ቦታዎች የሚኖሩትን ሁሉ አስታውሰዋል። “ሰላም ይሰፍን ዘንድ ያለማቋረጥ ጸሎት ማድረጋችንን እንቀጥል፣ በተለይም በመቁጠሪያ የጋራ ጸሎት በማድረግ ስለሰላም እንጸልይ" ሲሉ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጿል። የመቁጠርያ ጸሎት ምስጢሮች በማሰላሰል፣ “የጦርነት ሰለባ የሆኑ ልጆችን፣ እናቶችን፣ አባቶችን እና አረጋውያንን ስቃይ እና ተስፋ ተመልሶ እንዲመጣ እናደርጋለን” ሲሉ አስረድተዋል።

በጦርነት በተጎዱ ቦታዎች ለሚኖሩ ሰዎች ምልጃ በማቅረብ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የበጎ አድራጎት፣ የአንድነት እና ተጨባጭ ቅርርብ ተግባራት እንዴት ሊወጡ እንደሚችሉ አጉልተው ገልጸዋል። ለዚህ ተልዕኮ ቁርጠኛ ሆነው ለሚቀጥሉ በዓለም ዙሪያ ላሉ ሁሉ መልእክት በማድረስ፣ “ሰላም ፈጣሪዎች የተባረኩ ናቸው!” ሲሉ ደግመው ተናግረዋል።

27 Oct 2025, 13:10