ፈልግ

ወደ ቫቲካን አዲስ የገቡ የስዊስ ዘብ ጠባቂዎች ቃለ መሃላ ሥነ-ሥርዓት ወደ ቫቲካን አዲስ የገቡ የስዊስ ዘብ ጠባቂዎች ቃለ መሃላ ሥነ-ሥርዓት  (@Vatican Media)

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፥ የስዊስ ዘቦች ከኢየሱስ ጋር ያላቸውን ወዳጅነትን እንዲያሳድጉ አሳሰቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ወደ ቫቲካን ለመጡ አዲስ የስዊስ ዘብ ጠባቂ ምልምሎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ምልምሎቹ ዓርብ መስከርም 23/2018 ዓ. ም. ቃለ መሃላ ባደረጉበት ዕለት ባደረጉት ንግግር፥ ሐዋርያዊ ስልጣናቸው ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ላበረከቱላቸው የጥበቃ አገልግሎት ምስጋናቸውን አቅርበው፥ ምንም ዓይነት ሕይወት ቢያጋትማቸውም ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን እምነት እና ወዳጅነት እንዲያሳድጉ አደራ ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ቅዱስነታቸው ለአዲሶቹ ምልምሎች ባደረጉት ንግግር፥ “ውድ የስዊስ ዘብ ጠባቂዎች፥ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትነቴ ቀን ጀምሮ በታላቅ ትጋት እና ቅንዓት ባበረከታችሁልኝ ታማኝ አገልግሎት መታመን ችያለሁ” ብለው፥ “የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ ለቤተ ክርስቲያን እና ለመላው ዓለም ያለበትን ተልዕኮ መወጣት የሚችለው ለደህንነቱ በምታደርጉለት ክትትል ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

የእምነታችሁ እሴቶች

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ አዲስ ለተመለመሉት የስዊስ ዘቦች ባስተላለፉት መልዕክት፥ ለወንጌል ታማኝ ሆናችሁ በምርጫችሁ የምትተማመኑ ምዕመናን የሚያደርጋችሁን የክርስትና እምነት መሠረታዊ እሴቶችን ጠብቃችሁ እንድትቀጥሉ” ሲሉ አሳስበዋል።

“እያንዳንዳችሁ በገባችሁት ቃል እና በምግባራችሁ፣ በበጎ አድራጎታችሁ እና በእምነታችሁ ለሌሎች ዓርዓያ በመሆን፥ በቅድስት መንበር ሥር ለሚገኙ ከፍተኛ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤቶች የአንድነት ምልክት መሆን ትችላላችሁ” ሲሉ አበረታትተዋል።

ውስጣዊ ሕይወታችሁን እና ከጌታ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ያሳድጉ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ የሮም ከተማ ለስዊስ ዘቦች ከሃብት ጋር በታሪክ የማይረሳ ጉዞን እንደሚያመቻችላቸው በመግለጽ፥ ይህም በሥነ ጥበብ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም በላይ በክርስትና እምነት ኢየሱስ ክርስቶስን ከተከተሉት ከቀደምት ምስክሮች እስከ ሰማዕታት ድረስ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

“በዚህ ዕድል ተጠቅማችሁ ውስጣዊ ሕይወታችሁን ለማዳበር በኅብረተሰባችን መካከል ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁትን ግንኙነት አጠናክሩ” ሲሉ አሳስበዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለአዲሶቹ ምልምሎች ባደረጉት ንግግር፥ በዛሬው እለት ቃለ መሃላ በማድረግ ወደ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ እየገቡ መሆናቸውንም ተናግረው፥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በመማር ራሳችሁን ትሑት እና ታዛዥ አድርጋችሁ ተልዕአችሁን በቅንነት እንድትኖሩ አበረታታችኋለሁ” ብለዋል።

ለወንጌል እና ለክርስትና እምነት ታማኝ መሆን

ከምልምሎቹ መካከል ብዙዎቹ ለቅድስት መንበር መልካም እና ታማኝ አገልግሎት ካበረከቱ በኋላ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ገልጸው፥ ከፊት ለፊታቸው ብዙ ዕድሎች የሚጠብቃቸው መሆኑን ተናግረዋል። ጥቂቶች ጥናታቸውን እንደሚቀጥሉ፣ ወደ ሥራው ዓለም እንደሚገቡ፣ ወደ ሌሎች አገሮች እንደሚሄዱ ወይም ምናልባትም የክህነት አገልግሎት ጥሪ እንደሚቀበሉም ተናግረዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የእነዚህ አዲስ ምልምሎች ውሳኔ ምንም ይሁን ምን በቅድስት መንበር ውስጥ ከሚገኙ ከፍተኛ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤቶች የሚያገኙት ልምድ የወደፊት ሕይወታቸውን በልበ ሙሉነት እንዲመሩት እና ለእያንዳንዱ ክርስቲያን ተስማሚ የሆነ ሁለንተናዊ አመለካከት እንዲኖራቸው የሚረዳ መሆኑን እንዲያስታውሱ ተናግረዋል።

ብስለት እና ተስፋ

ትውልዳቸውን የሚያጋጥሙ በርካታ ተግዳሮቶች መኖራቸውን ለዘቦቹ ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፥ ከእነዚህም መካከል ማስተዋልን እና ኃላፊነትን የሚሹ ማለትም የአካባቢ ጉዳዮች፣ ኢኮኖሚያዊ ለውጦች፣ ማኅበራዊ ውጥረቶች፣ የዲጂታል አብዮት፣ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ወይም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ሌሎች ውስብስብ እውነታች መኖራቸውን ዘርዝረዋል።

“በሮም የሚኖራችሁ ጊዜ በእነዚህ የማኅበራዊ ሕይወት ዘርፎች ውስጥም ቢሆን ጥልቅ ብስለት እንድታዳብር ሊረዳችሁ ይችላል” ሲሉም አስረድተው፥ ይህንን በማሰብ የተስፋ ምስክሮች፣ ለወንጌል ታማኝ እና በጌታ ባላቸው እምነት እንዲጎለብቱ አሳስበዋቸዋል።

“በዚህ በተቀደሰ ዓመት በቀላል ምስክርነት፣ ለሚያገኟቸው ሰዎች የተስፋ ልኡካን እንዲሆኑ አደራ ብለው፥ የተስፋ ብርሃን መንገዳቸውን እንዲያበራላቸው፣ ደፋር እርምጃዎችን እንዲወስዱ እና ፍቅር እንዲስፋፋ የሚያደርግ የጋራ አስተዋፅዖን ለማበርከት ድፍረትን እንዲሰጣቸው በመመኘት መልዕክታቸውን ደምድመዋል።

04 Oct 2025, 15:55