ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዩ ትሑት እና የበለጠ እንግዳ ተቀባይ ቤተ ክርስቲያን እንገንባ ማለታቸው ተገለጸ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ውስጥ በተካሄደው የሲኖዶስ ቡድን እና የተሳታፊ አካላት የኢዮቤልዩ ቅዳሴ ወቅት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ተሳታፊዎቹን ሁሉ “የቤተክርስቲያኗን ምስጢር” እንዲያስቡ ጋብዘዋል። ቤተክርስቲያን ተዋረድ እና መዋቅር ያላት የሃይማኖት ተቋም ብቻ እንዳልሆነች አስታውሷቸዋል። ይልቁንም ቤተክርስቲያን “በእግዚአብሔር እና በሰው ልጅ መካከል ያለው አንድነት የሚታይ ምልክት” ናት፣ እግዚአብሔር ሁሉንም ሰው በፍቅር አንድ ላይ የሚያመጣበት ሥፍራ ናት በለዋል።
በመንፈስ ቅዱስ የተፈጠረ እና የተጠበቀ የቤተክርስቲያን ኅብረት ምን ማለት እንደሆነ በማሰላሰል፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሲኖዶስ ቡድን እና የተሳታፊ አካላት ምን እንደሆኑ መረዳት መጀመር እንደምንችል አብራርተዋል።
“በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚፈጠረውን ይገልፃሉ፣ ግንኙነቶች ለኃይል አመክንዮ ምላሽ የማይሰጡበት፣ ነገር ግን ለፍቅር ግንኙኝነት ምላሽ የሚሰጡበት ይሁን” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው የተናገሩት ቅዱስነታቸው በክርስቲያን ማህበረሰብ ውስጥ በጣም አስፈላጊው ነገር መንፈሳዊ ሕይወት መሆኑን አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
ፍቅር የበላይ ህግ ነው
ከሁሉም በላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እንዳሉት ከሆነ ሁሉም ተሳታፊዎች ፍቅር በቤተክርስቲያን ውስጥ ከፍተኛው ህግ መሆኑን እንዲያስታውሱ አሳስበዋል። “ማንም የበላይ ለመሆን አልተጠራም፤ ሁሉም ለማገልገል ተጠርተዋል” ሲሉ አስረድተዋል፣ “ማንም ሊገለል አይገባውም፣ ሁላችንም ለመሳተፍ ተጠርተናል” ብለዋል።
ስለዚህ፣ ሁላችንም አንድ ላይ እውነትን በሙሉ እንድንፈልግ ተጠርተናል። ይህ የ"አንድነት" ግብዣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የኅብረት ጥሪን እንደገና ያሳያል። የቀድመውን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን በመጥቀስ እና በመጨረሻው የዐቢይ ጾም መልእክታቸው የተናገሩትን በማስታወስ፣ ቅዱስ አባታችን “አብረን መጓዝ” የሚለውን ሀሳብ አንፀባርቀዋል። የአርጀንቲናው ሊቀ ጳጳስ “ክርስቲያኖች ከሌሎች ጎን እንዲሄዱ እንጂ እንደ ብቸኛ ተጓዦች ብቻቸውን እንዲጓዙ በጭራሽ እንዳልተጠሩ መናገራቸውን" አስታውሰዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አጉልተው እንደገለጹት፣ ፈሪሳዊው እና ግብር ሰብሳቢው ከወንጌል ምሳሌ ያጎደሉትን ነገር ነው። በአንድ ቦታ ላይ እያሉ፣ ተከፋፍለዋል እና አይግባቡም። “ሁለቱም አንድ መንገድ ይከተላሉ፣ ግን አብረው አይሄዱም። ነገር ግን ወንድማማቾች ሳይሆኑ እና ምንም የሚያመሳስላቸው ነገር ሳኖራቸው ሁለቱም ወደ አብ ይጸልያሉ” ሲሉ ገልጸዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህ መለያየት ከሁሉም በላይ የሚመነጨው ከፈሪሳዊው አመለካከት ነው፣ “ምንም እንኳን ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ቢመስልም፣ ራሱን የሚያይበት፣ የሚያጸድቅበት እና የሚያወድስበት መስታወት ብቻ ነው።” ከቀረጥ ሰብሳቢው የላቀ ሆኖ ይሰማዋል እና ወደ እሱ ይመለከታል። ስለዚህ፣ ከእግዚአብሔር እና ከሌሎች ጋር ባለው ግንኙነት ላይ ከማተኮር ይልቅ በራሱ ላይ ያተኩራል ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እንዳስጠነቀቁት ከሆነ፣ ይህ በክርስቲያን ማህበረሰብ ውስጥ ሊከሰት ይችላል። ራስ ወዳድነት በማህበረሰቡ ላይ የበላይ ሆኖ ሲነግሥ፣ እውነተኛ እና የወንድማማችነት ግንኙነቶችን የማይቻል ወደሚያደርግ ግለሰባዊነት ይመራሉ። አንድ ሰው ከሌሎች የተሻለ እንደሆነ ሲያስብም ሊከሰት ይችላል።
ነገር ግን፣ ትኩረታችንን በፈሪሳዊው ላይ ከማድረግ ይልቅ፣ ወደ ግብር ሰብሳቢው መመልከት አለብን። ትህትናው በቤተክርስቲያን ውስጥ ሁላችንም እግዚአብሔርን እና እርስ በርሳችን እንድንፈላለግ ያስታውሰናል። ክርስቶስ ለትሑታን ስለሆነ ማዳመጥ እና እርስ በርስ መራመድ መደሰት አለብን ብለዋል።
በውጥረት መካከል አንድነት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የሲኖዶሳዊነት ቡድን እና የተሳትፎ አካላት ቤተክርስቲያን እርስ በርስ በኅብረት የሚኖሩበት ምስል እንዴት እንደሆኑ አጉልተው ገልጸዋል። መንፈስ ቅዱስን በውይይት፣ በወንድማማችነት እና በፓርሄዚያ (እውነቱን በግልጽ እና በድፍረት በመናገር) ማዳመጥ እግዚአብሔርን ለመፈለግ አብረን ለመራመድ ለሚቀርብልን ጥሪ ምላሽ መስጠት እንችላለን ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የክርስቶስን ስሜት በመላበስ የቤተክርስቲያንን ቦታ እናሰፋለን ስለዚህም ሕብረት ፈጣሪዎች እና እንግዳ ተቀባይ እንድትሆን ቤተክርስቲያንን እናደርጋለን ሲሉ አብራርተዋል። በዚህ አቀራረብ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉ ውጥረቶች መካከል በልበ ሙሉነት መኖር እንችላለን - አንድነት እና ልዩነት፣ ባህል እና አዲስነት፣ ስልጣን እና ተሳትፎ ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
"እርስ በርስ በመቀናነስ ወይም ሌላውን በማሳነስ [ውጥረቶቹን] መፍታት ሳይሆን፣ በመንፈስ ቅዱስ እንዲነጹ መፍቀድ፣ በዚህም እንዲስማሙ እና ወደ የጋራ ግንዛቤ እንዲያመሩ ማድረግ ነው" ሲሉ ቅዱስ አባታቸው ያብራሩ ሲሆን የሲኖዶሳዊ የቡድን አባላት እና የተሳትፎ አካላት አባላት የቤተክርስቲያን ማስተዋል ውስጣዊ ነፃነትን፣ ትህትናን፣ ጸሎትን እና እምነትን እንደሚቀበሉ ግንዛቤ አላቸው። የአንድ ሰው አስተያየት ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ተሳትፎ ማካተት አለበት ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በዚያ የተገኙት ሁሉ “የሰውን ልጅ እግር ለማጠብ የምታጎነብስ ቤተክርስቲያን፤ እንደ ፈሪሳዊው ግብር ሰብሳቢው የማይፈርድ፣ ነገር ግን ለሁሉም ሰው እንግዳ ተቀባይ ቦታ የምትሆን ቤተክርስቲያን” እንዲገነቡ እና ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ እንዲደፍሩ ጥሪ አቅርበዋል።
