ር.ሊ.ጳ ሊዮ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች በኅብረተሰቡ በግድየለሽነት የተተወውን ክፍተት መሙላት አለባቸው ማለታቸው ተገለጸ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በንግግራቸው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በላቲን ቋንቋ "ሬሩም ኖቫሩም" (አዳዲስ ነገሮች) በሚል አርዕስት ይፋ በሆነው በቤተክርስቲያኗ የመጀመሪያ ጳጳሳዊ መልእክት ላይ የሰፈረውን “አዲስ ነገሮች” እንደገና በመንደፍ በዓለም ዙሪያ ያሉ ማኅበረሰቦችን የሚጫኑ ኢ-ፍትሃዊ ድርጊቶችን በጥልቀት አንፀባርቀዋል።
ምንም እንኳን የ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ አዳዲስ የኃይል ምንጮችን እና የኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ፈጣን እድገት የታየበት ጊዜ የነበረ ቢሆን፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 13ኛ (ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 13ኛ እ.አ.አ ከካቲት 20/1878 እስከ ሐምሌ 20/1903 ዓ.ም ድረስ የነበሩ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን 256ኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ነበሩ) ትኩረታቸውን “በዚያን ጊዜ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት፣ ከእርሳቸው በፊት የነበሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 13ኛ ከድሆች ጎን በመቆም “ከባርነት ብዙም የተሻለ ባልሆነ ሥራ” “ብዙኃኑኑ በአንፃራዊነት ለጥቂቶች ኃይል መገዛትን” አውግዘው ነበር ሲሉ ተናግረዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የሕዝብ እንቅስቃሴዎች የሚመነጩት ከኅብረተሰቡ ዳርቻዎች በመነሳት ፍትህን ለመፈለግ እና በኢ-ፍትሃዊ ሥርዓቶች ለሚተዳደሩ ሰዎች መፍትሄ ለማግኘት እንደሆነ ተናግረዋል።
“በጣም አስፈላጊው ነገር አገልግሎታችሁ በፍቅር መነቃቃት ነው ብዬ አስባለሁ” ብለዋል። “በሌሎች አገሮች ውስጥ ተመሳሳይ እውነታዎችን እና ልምዶችን አውቃለሁ፣ በእምነት፣ በተስፋ እና በተለይም በፍቅር የተሞሉ እውነተኛ የማህበረሰብ ቦታዎች፣ ይህም ከሁሉም የላቀ በጎነት ሆኖ ይቀጥላል” ሲሉ አክለው ተናግረዋል።
“ለድሆች የምትሆን ድሃ የሆነች ቤተክርስቲያን” ያስፈልጋል ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አክለውም የገለጹ ሲሆን ኢየሱስ ፊቱን በድሆች ውስጥ ስለደበቀ ቤተክርስቲያን ከሕዝብ እንቅስቃሴዎች ጋር በድፍረት፣ በትንቢት እና በደስታ መራመድ አለባት ብለዋል።
በዳርቻው ላይ ከመሆን ይልቅ ድሆች “የወንጌል ማዕከል ናቸው” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አረጋግጠዋል፣ ቤተክርስቲያኗ “የማኅበራዊ ችግሮች ሥር” የሆነውን ኢ-እኩልነት ማውገዝ አለባት ብለዋል።
እንደ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 13ኛ ዘመን ሁሉ፣ ማግለል የማኅበራዊ ኢፍትሃዊነት አዲሱ ገጽታ ሆኖ ይቀጥላል ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የተናገሩ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መሠረታዊ የሰው ልጅ ፍላጎቶቻቸውን እያጡ ባለበት በአሁኑ ጊዜ በኪሳችን ውስጥ የሚገኙትን የሰው ሰራሽ አስተውልኾት መሣርያዎች “ሥርዓታዊ የዘፈቀደ ጭቆና” በማዘን ተናግረዋል።
“በቀላል አነጋገር፣ መጥፎ አስተዳደር የእድገት ሰበብ በማድረግ ኢ-እኩልነትን ይፈጥራል፣ እና ይጨምራል” ብለዋል። “እናም የሰው ልጅ ክብር በማዕከሉ ባለመኖሩ ስርዓቱ በፍትህም ደረጃ ውድቅ ይደረጋል" ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ዘመናዊውን ማህበረሰብ የሚያጠቁ በርካታ ችግሮችን ዘርዝረዋል፣ የአየር ንብረት ቀውስ በጣም ግልፅ ምሳሌ እንደሆነ ተናግረዋል። እጅግ በጣም ቀርፋፋ እና የተዛቡ የሆኑ የሜትሮሎጂ ክስተቶችን የሚቋቋሙት ድሃ ሰዎች እና አገሮች ናቸው ብለዋል።
ማህበረሰቡን የሚጎዱ “አዳዲስ ነገሮች” ሌላኛው ገጽታ ማህበራዊ ሚዲያ በድሆች ላይ የሚፈጥረው ናፍቆት ሲሆን እነዚህም የተጋነኑ የአኗኗር ዘይቤዎችን እና ያልተገደበ የሸማችነት ስሜትን ከፍ አድርገው እንዲመለከቱ አድርጓል ብለዋል።
በተመሳሳይ ጊዜ፣ ዲጂታል የቁማር መድረኮች ከቁጥጥር ውጭ በሆኑ ክስተቶች ላይ በመመስረት የግዴታ ጥገኝነት እና ሱስ የሚያስይዙ ልማዶችን ለመፍጠር ጨለማ ቅንጦቶችን ይጠቀማሉ ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የመድኃኒት ኢንዱስትሪው “የአካላዊ ደህንነት አምልኮ፣ ማለት ይቻላል የሰውነት ጣዖት አምልኮ፣ የህመም ምስጢር ወደ ሙሉ በሙሉ ኢሰብአዊ ነገር የሚቀየርበት” የሚለውን ማስተዋወቅ የለበትም ሲሉ አውግዘዋል።
ይህ አመለካከት በተለይም በሰሜን አሜሪካ ውስጥ እንደ ኦፒዮይድ እና ፌንታኒል ባሉ ገዳይ መድኃኒቶች ላይ ጥገኛነትን ያስከትላል ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች መሰረት ላይ የሚገኘው ኮልታን ማዕድን ('ኮልታን' የኮለምባይት እና የታንታላይት ማዕድናት ድብልቅ ሲሆን ለኤሌክትሮኒክስ ኢንዱስትሪ በተለይም በሞባይል ስልኮች፣ በኮምፒውተሮች እና በቪዲዮ መጫወቻዎች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉትን ካፓሲተሮች ለማምረት አስፈላጊ ነው። ይህ ማዕድን በምስራቅ ኮንጎ ውስጥ ትላልቅ ክምችቶች ይገኛል፣ እዚያም የማዕድን ቁፋሮ ብዙውን ጊዜ ከግጭት፣ ከህፃናት ጉልበት ብዝበዛ እና እጅግ በጣም አስከፊ ሁኔታዎች ጋር የተያያዘ ነው) ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክን ጨምሮ በድሃ አገሮች ውስጥ ወታደራዊ ጥቃት እና የህፃናት ጉልበት ብዝበዛን አስከትሏል ብለዋል።
"ሊቲየም ማዕድን ሌላ ምሳሌ ነው" ብለዋል። "በታላላቅ ኃያላን አገራት እና በትላልቅ ኮርፖሬሽኖች መካከል ያለው ፉክክር ለድሃ መንግሥታት ሉዓላዊነት እና መረጋጋት ከባድ አደጋን አስከትሏል" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ተናግረዋል።
በመጨረሻም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አገሮች ድንበሮቻቸውን የመጠበቅ መብት አረጋግጠዋል፣ ነገር ግን የደህንነት መብታቸውን ከ"ጥበቃ የማድረግ የሞራል ግዴታ" ጋር ማመጣጠን እንዳለባቸው ተናግረዋል።
"እነዚህን 'የማይፈለጉ' [ስደተኞች] ቆሻሻ እንጂ የሰው ልጅ እንዳልሆኑ የሚያዩ ኢሰብአዊ እርምጃዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተወሰዱ ነው" ብለዋል። "በሌላ በኩል ክርስትና ፍቅር የሆነውን፣ እኛን የሚፈጥረንን እና እንደ ወንድም እና እህት እንድንኖር የሚጠራንን አምላክ ያመለክታል" ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከዚያም እነዚህን የሰብአዊነት ማዋረድ ዓይነቶችን በመፍታት እና "የሰብአዊነት፣ የፍትህ ምስክር እና የአንድነት ፈጣሪዎች" በመሆናቸው የህዝብ እንቅስቃሴዎችን እና የሲቪል ማህበረሰብን አመስግነዋል።
የሠራተኞች ሕብረት እና የሠራተኞች ማህበራት ቁጥራቸው በጣም በመቶኛ አነስተኛ የሆኑ ሠራተኞችን የሚወክሉ ሲሆን ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ሠራተኞች ተገቢውን ጥበቃ መስጠት አልቻሉም ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እንዳሉት ሕዝባዊ ንቅናቄዎች ቀደም ሲል የነበሩ የማኅበራዊ ተቋማትን ባዶነት ለመሙላት ከክርስቲያኖችና ከመንግሥታት ጋር እንዲሠሩ ጥሪ ቀርቧል፤ እነዚህም “ፍጹም አይደሉም” ሲሉ የገለጿቸው፣ ነገር ግን ውድቀታቸው ሰዎችን “ከበፊቱ በበለጠ ተጋላጭ” እንዲሆኑ አድርጓል ብለዋል።
“ቤተ ክርስቲያን ለመሬት፣ ለመኖሪያ ቤትና ለሥራ ያላችሁን ፍትሐዊ ትግል ትደግፋለች” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ንግግራቸውን ደምድመዋል። “እንደ ቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከዳር እስከ ዳር ያሉት መንገዶች የሚጀምሩት ከመሠረቱ ጀምሮ ብቻ እንደሆነ አምናለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።
“ዛሬ፡ መኖሪያ ቤት፣ ሥራ እና መሬት የተቀደሱ መብቶች ናቸው፣ ለእነሱ መታገል ጠቃሚ ነው፣ እና ‘እዚህ ነኝ'’ ‘ከእናንተ ጋር ነኝ!’ እኔ በዚህ ጉዳይ ከእናንተ ጋር ነኝ ለማለት እፈልጋለሁ" ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።
