ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ   (@Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዩ ከኢየሱስ ጋር የተገናኘውን ደስታ አስፋፉ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ለቀደምት ለአገሬው ተወላጆች አውታረ መረቦች እና የሕንድ ሥነ-መለኮት ሊቃውንት መረብ ባስተላለፉት መልእክት የኢዮቤልዩ ዓመት የጸጋ፣ የይቅርታ እና የጋራ ተስፋ ጊዜ እንደገና መልሰው ይጎናጸፉ ዘንድ አበረታተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የኢዮቤልዩ የተስፋ ዓመትን ሲያከብሩ ለአገሬው ተወላጆች አውታረ መረቦች እና የሕንድ የሥነ መለኮት ሊቃውንት መረብ መልእክት ልከዋል።

ሐሙስ ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም በታተመው ጽሑፍ ላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የኢዮቤልዩ ዝግጅቶችን ሲያቅዱ፣ “የቤተክርስቲያንን ሁለንተናዊነት ለማጉላት የፈለጉትን፣ ቤተሰቦች፣ ልጆች፣ ወጣቶች፣ ጎርማሶች፣ አረጋውያን፣ አገልጋዮችን እና ምዕመናንን፣ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን እና ገድማዊያት/ገዳማዊያን” ያላቸውን ፍላጎት ያስታውሳሉ ብለዋል።

“በቅዱስ በር ስናልፍ፣ ወደ ውብ ቤተ መቅደስ በመግባት ምሳሌያዊ እንቅስቃሴን ከማድረግ በላይ፣ በእውነት የምንፈልገው፣ በእምነት፣ ወደ መለኮታዊ ፍቅር ምንጭ - ወደ የተሰቀለው ክፍት ጎን መግባት ነው” በማለት አብራርተዋል።

"በዚህ እምነት ወንድማማች ህዝቦች ነን፣ ከዚህ እውነት ነው ታሪካችንን እና አሁን ያለንበትን እውነታ ደግመን ማንበብ ያለብን፣ ድካም እና መከራ ቢያጋጥመንም ቅዱሱ አመት በሚጠራን ተስፋ የወደፊቱን ለመጋፈጥ " መጓዝ ይኖርብናል ብለዋል።

ከታሪክ ጋር መታረቅ

በተጨማሪም “የእኛ የቀደምት ተወላጅ ሕዝቦች የረጅም ጊዜ የወንጌል ታሪክ በብርሃንና በጥላ የተሞላ ነው” ብሏል። ቅዱስ አውግስጢኖስን በመጥቀስ የወንጌል መልእክተኞች ሁልጊዜ ከመልእክቱ ጋር የማይጣጣሙ ቢሆኑም እንኳ “እግዚአብሔር ራሱ ጸጋን ይሠራል” ሲሉ አጽንዖት ሰጥተው የተናገሩት ቅዱስነታቸው ስለዚህ፣ ኢዮቤልዩ “ወንድሞቻችንን ከልብ ይቅር ለማለት” (ማቴ. 18፡35)፣ ከራስ ታሪክ ጋር ለመታረቅ እና ለእግዚአብሔር ምሕረት የምናመሰግንበት አመቺ ጊዜ ነው" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ሰዎች በእውነት የእግዚአብሔር ሕዝብ ሊሆኑ የሚችሉት በታማኝነት ለመለኮታዊ ኃይል በመገዛት ብቻ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን ጌታ "በሁሉም ባህሎች ውስጥ የቃሉን ዘር ዘርቷል" እና በአዲስ መንገድ እንዲያብቡ እንዳደረጋቸው አስታውሰዋል፣ በዚህ አውድ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛን ጠቅሷል፡- "የወንጌል ኃይል በየቦታው እየተለወጠ እና እየታደሰ ነው። ወደ ባህል ሲገባ፣ ወንጌል ከባህል ጋር የማይገናኝ  ከሆነ ትምህርተ ክርስቶስን ማሰተማር አስቸጋሪ ይሆናል" ብለው መናገራቸውን አስታውሰዋል።

የሚያበለጽግ ውይይት

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ውይይትና ግንኙነት “ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ ያቀረበውን የተትረፈረፈ ሕይወት” ለማግኘት እንደሚያስችል አረጋግጠዋል። ይህ ሕይወት፣ “በመጀመሪያ ኃጢአት በተገለጠው” እና በክርስቶስ ጸጋ “ሕይወትን የተትረፈረፈ ሕይወት ይሆንልን ዘንድ የመጨረሻውን የደሙን ጠብታ ባፈሰሰው” በሰው ደካማነት እንደሚገለጥ ተናግሯል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የአገሬው ተወላጆች ማህበረሰቦች እና የሕንድ ሥነ-መለኮት ለቤተ ክርስቲያን ነጸብራቅ ላደረጉት አስተዋጽዖ ምስጋናቸውን ገልጸው፣ የዓለም አተያያቸው “ከፈጣሪ እና ከፍጥረት ጋር የመገናኘት ጥልቅ ጉጉት ያለው ነው” - ቤተክርስቲያን በማስተዋል መቀበል አለባት ብለዋል።

የወንጌል ድፍረት እና ተልዕኮ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክታቸውን ከማጠቃለላቸው በፊት በቀድሞው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የተወደደውን ቃል ጠቅሰዋል፣ ይህም በግሪክ ቋንቋ "parrhesia" - (ፓርሄሲያ አደገኛ በሆነ ወይም ከስልጣን ጋር በሚጋጭበት ጊዜም ቢሆን እውነቱን በግልጽ እና በድፍረት መናገርን የሚያካትት የመናገር ነፃነት ነው ) ያንን የወንጌል ድፍረት “ያለ ፍርሃትና በነፃነት ወንጌልን ለመስበክ ከራሳችን እንወጣ" ሲሉ ገልጸዋል።

በብሄሮች ትዕይንት ላይ ቀደምት ተወላጆች የራሳቸውን ሰብአዊ፣ ባህላዊ እና ክርስቲያናዊ ሃብት በድፍረት እና በነጻነት ማቅረብ እንዳለባቸው አረጋግጠዋል። አክለውም ቤተክርስቲያኗ፣ “የዘላለም ጌታ አምላክ ሆይ፣ የዘላለም ጌታ አምላክ ሆይ፣ በደስታ እንዘምርልሃለን፣ ውዳሴያችንን ላንተ እንዘምርሃለን" የሚለውን የሁሉም ሕቦችን ድምጽ መሰማት ትፈልጋለች ብለዋል።

ማርያም፣ የስብከተ ወንጌል ኮከብ

በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የስብከተ ወንጌሉን አገልግሎት “የስብከተ ወንጌል ስርጭት ኮከብ” ለሆነችው ለጓዳሉፔ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አደራ ሰጥተዋል፣ እርሱም “ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ሕዝቦችን እንዴት አንድ እንዳደረገ፣ የጠላትነትን ግንብ እንዴት እንዳፈረሰ” አሳይታለች ሲሉ ተናግረዋል።

“ከመለኮታዊ ልቡ ጋር በመገናኘት የሚገኘውን ደስታ” በማዳረስ“ሂዱና አሕዛብን ሁሉ ደቀ መዛሙርት አድርጉ” በማለት መልእክቱ የሚስዮናውያንን ተልዕኮ ለማደስ በቀረበ ጥሪ ተጠናቋል።

17 Oct 2025, 15:23