ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ሊዮ የሕዝቦችን እጣ ፈንታ የምትሰውስኑ ሁሉ ትጥቅ ለማስፈታት ድፍረት ይኑራችሁ አሉ!

ቅዳሜ ጥቅምት 01/2018 ዓ.ም ለመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መንፈሳዊ ኢዮቤልዩ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተካሄደው የጸሎት ሥነ ሥርዓተ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የመቁጠርያ ጸሎት መምራተቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ከመቁጠሪያ ጸሎት በመቀጠል የቅዱስ ቁርባን የስግደት ጸሎት መከናወኑም ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ከማርያም ቤተመቅደሶች የተውጣጡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እና በጎ ፈቃደኞች እንዲሁም የጸሎት ቅንጅት እና የጸሎት ቡድኖች አባላትን ጨምሮ  ከ30,000 የሚበልጡ ምዕመናን  በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ቅዳሜ ዕለት በቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በተመራው የጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይ አብረው በመጸለይ መሳተፋቸው ተገልጿል።

“የሰላም ስጦታን” ለማግኘት የጸሎት ጊዜ አስፈላጊ መሆኑን ቀደም ሲል ቅዱስነታቸው ባቀረቡት ጥሪ መሰረት የተከናወነ የጸሎት ሥነ-ሥርዓት መሆኑም ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በመቁጠርያ ጸሎት ወቅት ባደረጉት ገለጻ ምእመናን “ለሰላም ለመጸለይ ሳይታክቱ በትጋት እንድጸኑ፣ ከእግዚአብሔር የተሰጠን ስጦታ ለመቀበል መትጋት ያለባቸውና ለዚህም ጠንካራ ቁርጠኝነት ማሳየት እንደሚገባ ጥሪ" ማቀረባቸውም ተገልጿል።  

“ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ"

የኢየሱስን ቃል በማስታወስ "በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለው “ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ፤ ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና" (ማቴዎስ 26፡52) የሚለውን በመጥቀስ ይህ ቃል  “መሬት ላይ ወድቆ እንዲቀር ማድረግ” የለብንም በማለት የተናገሩት ቅዱስነታቸው በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ውስጥ፣ ከህማማቱ በፊት፣ “ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ” በማለት የተናገራቸውን ቃላቶች ትጥቅ ለማስፈታት በጋለ ስሜት እንደ ሚረዳን አሳይተዋል" ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

አሁንም “ሰላም ያልታጠቀና ትጥቅ የሚፈታ ነው፣​​መከልከል ሳይሆን ወንድማማችነት ነው፤ ይህ የውይይት እንጂ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ጉዳይ አይደለም” ብለዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ሰላም፣ “ፍትሕን በመዝራትና በድፍረት ይቅርታን የመዝራት ፍሬ እንጂ፣ በጠላት ላይ በተደረጉ ድሎች አይመጣም” ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በመቀጠል “‘ሰይፍህን ወደ ሥፍራው መልስ’ የሚለው መልእክት በዓለም ኃያላን አገራት፣ የሕዝብን እጣ ፈንታ ለሚመሩ እና ለሚወስኑ ሰዎች የተላለፈ መልእክት ነው፡ ትጥቅ ለመፍታት አትፍሩ፣ የሚል መልእክት እንደምያስተላለፍ አክለው የገለጹት ቅዱስነታቸው በተጨማሪም “ከዚሁ ጋር፣ ምንም ዓይነት ሐሳብ፣ እምነት ወይም ፖሊሲ መግደልን የማያጸድቅ መሆኑን እንድንገነዘብ ለእያንዳንዳችን የቀረበ ግብዣ ነው። በመጀመሪያ ልባችንን ማስታጠቅ አለብን፣ ምክንያቱም በራሳችን ልብ ውስጥ ሰላም እስካላገኘን ድረስ ለሌሎች መስጠት አንችልም" ሲሉ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

ትክክለኛ የማርያም መንፈሳዊነት

የጳጳሱ ትጥቅ የመፈታት ጥሪ የማርያምን የወንጌል ቃል መሰረት በማድረግ በማርያም መንፈሳዊነት ላይ በማንፀባረቅ የቀረበ ጥሪ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “በዚህ የማርያም መንፈሳዊ ኢዮቤልዩ ወቅት እኛ አማኞች በተስፋ ጉዟችን ላይ ወደምትመራን ወደ ድንግል ማርያም እይታችንን እናዞራለን። ምእመናንን “እጅግ እውነተኛው የማርያምን አምልኮ” የማርያምን “ሰብዓዊና ወንጌላዊ በጎነት” መምሰልን እንደሚጨምር አስታውሷቸዋል፣ እናም “መከራ ለሚደርስባቸው ወንድምና እህቶች ሁሉ እንዲሁም ለፍጥረታት ሁሉ የምሕረት ስጦታ እንዲሰጣቸው” እንዲጠይቁ ጋብዟቸዋል።

በወንጌል ውስጥ የማርያምን የመጨረሻ “የከበረ” ቃል አስታውሰው “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” ያሉት ቅዱስነታቸው “እንደ መብራት ምልክት፣ ማርያም ከራሷ በላይ ትጠቁማለች፣ የመጨረሻው መድረሻው ጌታ ኢየሱስ እና ቃሉ መሆኑን ያሳያል። የእግዚአብሔር እናት "ወንጌልን እንድንኖር፥ በቁርጠኝነት እና በደስታ እንድንኖር" ጠርታናለች፣ ይህን በማድረግ ህይወታችን "ከባዶነት እና ከደነዘዘ ሕይወት ወደ ሙሉ እና ደማቅ ወደሆነ ነገር ይለወጣል" ብለዋል።

የተለየ አመለካከት መቀበል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ከዚያ በኋላ ምእመናን ዓለምን ከኃያላን እይታ ሳይሆን “ከታናናሾቹ… የታሪክን ክንውኖች ከመበለቲቱ፣ ወላጅ አልባው፣ እንግዳው፣ የቆሰለውን ሕፃን፣ ግዞተኛ እና የሸሸ ሰውን አመለካከት እንዲተረጉሙ “የተለየ አመለካከት እንዲይዙ” ጋብዟቸዋል።

ይህን ማድረግ እስክንማር ድረስ፣ “ምንም አይለወጥም፣ አዲስ ዘመን፣ የፍትሕና የሰላም መንግሥት አይነጋም” ብሏል።

በመጨረሻም፣ “ሰላም ፈጣሪዎች ብፁዓን ናቸው” የሚለውን የጠቀሱት ቅዱስነታቸው “የድሆችን እና የእናት ምድርን ጩኸት እንድንሰማ… ለአገልግሎት ያለን ቁርጠኝነት መመሪያ እንዲሆነን … [እና] ለመኖር እና ስለ ክርስቲያናዊ ፍቅር ለመመስከር፣ ሁሉንም እንደ ወንድም እና እህቶች በመቀበል፣ ጨለማ መከተልን አቁመን፣  ራስ ወዳድነት እንድንተው እና የእውነት አምላክ የሆነውን ክርስቶስን እንድንከተል” እንድታስተምረን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ወደ ሰላም ንግሥት ማርያም መጸለያችንን ልንቀጥል ይገባል ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

13 Oct 2025, 15:42