ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ እና የጣሊያኑ ፕሬዝዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ በሮም በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ እና የጣሊያኑ ፕሬዝዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ በሮም በተገናኙበት ወቅት  (@Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሰላም የተከበረ እና የበለጸገ አብሮ መኖርን ይጠይቃል ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በሮም የሚገኘው የኩዊሪናል ቤተ መንግሥት ከጣሊያኑ ፕሬዝዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ ጋር ተገናኝተው ይፋዊ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በአውሮፓ የወሊድ መጠን እያሽቆለቆለ ባለበት ወቅት ቤተሰን ለመደገፍ እና ጦርነት እየተከሰተ በሚገኝባቸው የዓለም ክፍሎች ሰላምን ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት እንደምያበረታቱ ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ማክሰኞ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም የጣሊያንን ፕሬዝዳንት ሰርጂዮ ማታሬላን ለመጎብኘት እና በቅድስት መንበር እና በጣሊያን መካከል ስላለው "የሁለትዮሽ ግንኙነት" ውይይት ለማድረግ በሮም ከተማ ወደ ሚገኘው የኩዊሪናል ቤተ መንግሥት ተጉዘዋል።

በጉብኝቱ መገባደጃ አካባቢ በንግግራቸው ላይ "እንደ ሮም ጳጳስ እና የኢጣሊያ ዋና ጳጳስ እንደመሆኔ፣ በዚህ ጉብኝት የቅዱስ ጴጥሮስን መንበር እርስዎ ከሚወክሉት የኢጣሊያ ህዝብ ጋር አንድ የሚያደርገውን ጠንካራ ትስስር ማደስ ለእኔ ጠቃሚ ነው" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የኢጣሊያ እና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ለብዙ መቶ ዓመታት ተሳስሮ የቆየ፣ የጣሊያን ጥበባዊ እና ባህላዊ ፈጠራ በወለዳቸው ስፍር ቁጥር በሌላቸው አብያተ ክርስቲያናት እና የደወል ማማዎች ውስጥ እንደሚታይ ተናግረዋል ።

እነዚህን ግዑዝ ፍጥረቶች “የዚህ ሕዝብ ተፈጥሯዊ ፈጠራ፣ ከእውነተኛ እና ጽኑ እምነት ጋር አንድነት ያለው ነው፣ ይህም የታላቅ ውበት ምስክርነት የሰጠን፣ ጥበባዊ፣ በእርግጥ ከሥነ ምግባራዊና ከሰው ሁሉ በላይ የሆነው” መግለጫ ነው በማለት ጠርቷቸዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የጣሊያን ሲቪል ባለስልጣናት የተስፋ ኢዮቤልዩ በዓልን ለማክበር፣ ለቀድሞ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ክብር ለመስጠት እና ጉባኤውን ለማየት የመጡትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናንን ለመቀበል ላደረጉት ጥረት አመስግነዋል።

በእነዚህ ዝግጅቶች ላይ የተቀመጠው ውስብስብ አሠራር ዝርዝር አደረጃጀት፣ አተገባበር እና ደህንነት ጣሊያን ከየትኛውም የዓለም ክፍል የመጡ ሰዎችን ለመቀበል ያላትን ፍላጎት “የእንግዳ ተቀባይነት እና ድርጅታዊ ቅልጥፍናን የሚያሳይ ግሩም ምስክርነት” ሰጥተዋል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ እ.አ.አ በ1929 ዓ.ም የተፈረመውንና የቫቲካን ከተማን ግዛት እ.አ.አ ከ1870 ዓ.ም ጀምሮ የኢጣሊያ ግዛት ከነበረው የላተራን ስምምነት መቶኛ ዓመትን አስታውሰዋል።

ቤተ ክርስቲያን እና የኢጣሊያ መንግሥት የጋራ ተጠቃሚነትን ለማራመድ ተቀራርበው ይሠራሉ፤ የሰውን ልጅ በማገልገል ላይ ያሉ ሥራዎችን በመጥቀስ፤ “የማይነካ ክበራቸው ሁል ጊዜ በሁሉም የማኅበራዊ ልማት ደረጃዎች በውሳኔ አሰጣጥና በተግባር ግንባር ቀደም መሆን አለበት፤ በተለይም በጣም ደካማ እና የተቸገሩትን በመከላከል ረገድ” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በመቀጠል “በዓለም ዙሪያ የሰውን ልጅ የሚያቆስል እና አፋጣኝ ሆኖም አርቆ አሳቢ ምላሽ የሚያስፈልገው ከባድ ስቃይ” አስታውሰዋል።

ሰላም የቤተ ክርስቲያን እና የአለም ፍላጎት አስፈላጊ አካል ነው፣ እናም ምድራችንን እያጠፉ ስላሉት በርካታ ጦርነቶች በማንሳት ይህ ሁኔታ እንደምያሳዝናቸው ገልጸዋል።

ዓለም በጦርነት አፋፍ ላይ በምትገኝበት ወቅት፣ ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በፊት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 14ኛ እና ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፊት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮ 12ኛን ጨምሮ፣ ለዓለም አቀፍ መሪዎች ያቀረቡትን የሰላም ጥሪ በማውሳት  የበርካታ የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሰላም ተማጽኖዎችን አስታውሰዋል።

ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ጋር፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ “በየትኛውም የዓለም ክፍል ሰላምን እንደገና ለማስፈን መሥራታችንን እንድንቀጥል፣ የመብት፣ የፍትሐዊነትና በሕዝቦች መካከል ያለው ትብብር መርሆዎች- የማይተካ መሠረት የሆነው መሠረታዊ ሥርዓት ይበልጥ እንዲዳብርና እንዲስፋፋ” ልባዊ ጥሪያቸውን እንዳደሱ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የጣሊያን መንግሥት በጦርነት እና በድህነት ሳቢያ የሚደርሱ ችግሮችን ለመቅረፍ የምያደርገውን ጥረት አመስግነዋል፣ በተለይም የጋዛ ህጻናት በቫቲካን ባምቢኖ ጄዙ ሆስፒታል እንዲታከሙ ለማድረግ እያበረከተ ያለውን ጥረት አመልክተዋል።

እ.ኤ.አ. በ2026 ዓ.ም የዚዚው ቅዱስ ፍራንችስኮስ ህልፈት 800ኛ ዓመት የሚከበርበት አመት መሆኑን ጠቁመው በዓሉ የጋራ ቤታችን የመንከባከብ አስፈላጊነት የሚጎላበት አጋጣሚ ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከቅርብ አሥርተ ዓመታት ወዲህ በአውሮፓ ውስጥ ያለው የወሊድ መጠን ማሽቆልቆሉን ጠቁመው በመላው ህብረተሰብ ውስጥ የማሕበረሰብ እና የቤተሰብ እሴቶችን ለመደገፍ ጥረቶች እንዲደረጉ ጠይቀዋል ።

"ለቤተሰቦች በተለይም ለወጣት ቤተሰቦች የወደፊትን ጊዜ በመረጋጋት እንዲመለከቱ እና ተስማምተው እንዲያድጉ መተማመንን ለመስጠት የተቻለንን ሁሉ እናድርግ" ሲሉ ተናግሯል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በተጨማሪም ጣሊያን ለስደተኞች ለምታደርገው እርዳታ እና ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመዋጋት ላደረገችው ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

"እነዚህ በጊዜያችን ካሉት ታላላቅ ተግዳሮቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፣ እናም ጣሊያን ከእነሱ ፈቀቅ አላለችም።የግል እና የአብሮነት አመለካከታችሁን እንድትቀጥሉ አበረታታችኋለሁ" ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

በማጠቃለያውም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የጣሊያን ማህበረሰብ በፋሽን ወይም በገበያ ሽፋን ስር ያሉ ሰዎችን ነፃነት ለመንጠቅ የሚገፋፋውን ፈተና በማስወገድ የቀድሞ አባቶቻቸው ያስረከቧቸውን የባህል ጥልቀት እንዲያደንቁ ጋብዘዋል።

"ጣሊያን እጅግ የበለጸገች - ብዙ ጊዜ ትሑት እና የተደበቀች ሀገር ናት - እናም ለዛውም አንዳንድ ጊዜ መገኘት እና እንደገና ማግኘት ትፈልጋለች" ብሏል። "ሁሉም ጣሊያናውያን ይህን ውብ ተግባር እንዲፈጽሙ፣ ተስፋ እንዳይቆርጡ እና የአሁኑንና የወደፊቱን ፈተናዎች በልበ ሙሉነት እንዲጋፈጡ አበረታታለሁ" ሲሉ ቅዱስነታቸው መናገራቸው ተዘግቧል።

15 Oct 2025, 15:06