ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለተማሪዎች ቴክኖሎጂ እንዲጠቀምባችሁ አትፍቀዱ ማለታቸው ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ለአለም አቀፍ የካቶሊክ የትምህርት ተቋማት ኢዩቤልዩ ለሚሳተፉ ተማሪዎች ለሳምንት የሚቆየውን ተከታታይ ዝግጅቶች በመቀጠል፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐሙስ ዕለት ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም በጳውሎስ 6ኛ የመሰብሰብያ አዳራሽ ከተገኙ ተማሪዎች ጋር ተገናኝተዋል። ንግግራቸውን የጀመሩት ለወጣት ተማሪዎች ሂሳብ በማስተማር ያሳለፉትን ጊዜ ስለሚያስታውሳቸው ለዚህ ዝግጅት ያላቸውን ደስታ እና ጉጉት በመግለጽ ነበር።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቅርቡ ሲመተ ቅድስና የተሰጠውን የጣሊያን ተማሪ የነበረውን ቅዱስ ፒየር ጆርጂዮ ፍራሳቲን ምሳሌ እና ሁለት መሪ ቃሎቻቸውን አስታውሰዋል፡- “ያለ እምነት መኖር… መኖር ማለት መኖር ማለት ብቻ አይደለም ነገር ግን በቀላሉ ዝም ብሎ መጓዝ ማለት ነው" ብሎ የተናገረውን ሐሳብ በድጋሚ ያስተጋቡ ሲሆን ከዚያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለወጣት ተማሪዎች የራሳቸውን ማበረታቻ በማከል “ወደ ከፍታ የሚወስደውን ሕይወት ሙሉ በሙሉ የመኖር ድፍረት ይኑራችሁ” ሲሉ አክለው ተናግረዋል።
ለፋሽን፣ ለመልክ ወይም ለአጭር ጊዜ ደስታዎች ብዙ ትኩረት መስጠት እንደሌለባቸው አፅንዖት ሰጥው የተናገሩት ቅዱስነታቸው ይልቁንም ቅዱስ አባታቸው “ለበለጠ ነገር ናፍቆት” እንዲኖራቸው ገፋፍቷቸዋል። ይህ የተሻለ ማህበረሰብ እንዲኖር ተስፋ የሚያደርጉ እና የሚያቅዱ ወጣቶች ፍላጎት እንዲሳካ የምያደርግ ነው። ስለዚህ "ወደ ከፍታው" ለመውጣት እንዲጥሩ አሳስበዋል።
"አንድ ቀን የእናንተ ትውልድ ለቤተክርስቲያን እና ለዓለም ላመጡት ተጨማሪ ጥረት የሚታወስ 'ትውልድ' ተብሎ ቢታወስ ምንኛ ድንቅ ነበር" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ተናግረዋል። ነገር ግን ይህንን ፍላጎት እንደ ሕልም እንዳይመለከቱት አስጠንቅቀዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ይህንን ለማሳካት የሚቻለው መልሱን በትምህርት በኩል እንደሆነ አብራርተዋል፣ "ዓለምን ለመለወጥ ከሚያምሩ እና ኃይለኛ መሳሪያዎች አንዱ ትምህርት" ነው ሲሉ ተናግረዋል።
አዲስ የትምህርት ወቅት
የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ በ2020 ዓ.ም. ወጣቱን ትውልድ በዓለም አቀፍ ወንድማማችነት ውስጥ ለማሳተፍ የተመደበውን ዓለም አቀፍ የትምህርት ስምምነት ፕሮጀክት እንዴት እንደጀመሩ አስታውሰዋል። በወቅቱ በስብሰባው ላይ የተገኙት ተማሪዎች የትምህርት ተቀባዮች ብቻ ሳይሆኑ "ዋና ገፀ-ባህሪያቱ" መሆናቸውን አስታውሰዋል።
በዚህም ምክንያት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሁሉም ሰው የእውነት እና የሰላም ምስክር የሚሆንበት "አዲስ የትምህርት ወቅት" እንዲገነቡ አሳስበዋል። ነገር ግን ይህንን ብቻቸውን ማድረግ የለባችሁም። ጓደኞቻቸውን እውነትን በመፈለግ እና የሰላም ግንባታ ውስጥ እንዲያካትቱ አበረታቷቸዋል።
ተማሪዎችን በዚህ ተግባር ለመርዳት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በአንድ ወቅት “እውቀት ሲጋራ ያድጋል፣ እና የእውነት ነበልባል የሚበራው በአእምሮ ውይይት ነው” ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን እንደ ከዋክብት፣ እውነተኛ ሰላም የሚገኘው ብዙ ሰዎች አንድ ላይ ተሰባስበው ዲዛይን ሲፈጥሩ ነው። አብረው በመስራት፣ “ወደፊት የሚመሩ የትምህርት ህብረ ከዋክብትን መፍጠር እንችላለን” ሲሉ ተናግረዋል።
ወደ ከዋክብት ተመልከቱ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በከዋክብት ላይ በማሰላሰል፣ በታሪክ ውስጥ ሰዎች እንዴት እንደ መሪ እንደተጠቀሙባቸው በመግለጽ ከመርከበኞች እስከ ፖሊኔዥያውያን፣ ከአንዲስ ገበሬዎች እስከ በገና ታሪክ ውስጥ ባለው ሰብአ ሰገል ታሪክ ውስጥ የከዋክብት ሚና በከፍተኛ ሁኔታ መገለጹን አመልክተዋል።
ልክ እንደ ቅድመ አያቶቻችን፣ እኛ ደግሞ የሚመሩን ከዋክብት አሉን፡ ወላጆቻችን፣ ፕሮፌሰሮቻችን፣ ካህናት እና ጓደኞቻችን። በህይወት ፈተናዎች ውስጥ በትክክለኛው መንገድ ላይ እንድንገኝ ይረዱናል። በተራው፣ ሁላችንም በዙሪያችን ላሉ ሰዎች “የሚያበሩ ምስክሮች” እንድንሆን ተጠርተናል። ብቻችንን፣ የግለሰብ ኮከቦች ነን፣ ግን አብረን፣ ህብረ ከዋክብትን እንፈጥራለን ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
ትምህርት ሰዎችን አንድ የሚያደርግ መንገድ ነው። ወደ ሰማይ፣ ወደ ላይና ወደ ከፍ ያለ እይታ እንዲኖረን ያበረታታናል። ትምህርት ከፊታችን ያለውን እንድናይና በሌላ መልኩ የማንፈልገውን ነገር ሳይቀር እንድናይ የሚረዳን መሳሪያ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ስልኮቻችንን ዝቅ ብለን ከመመልከት ይልቅ ተማሪዎቹ "በምትኩ ወደ ሰማይ፣ ወደ ከፍታው ተመልከቱ" በማለት አበረታቷቸዋል።
ለብዙ ነገሮች ተፈጥረናል
ወደ ዓለም አቀፍ የትምህርት ስምምነት ስንመለስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ወጣቶች ራሳቸው በዚህ ፕሮጀክት ውስጥ ካሉት አዳዲስ ተግዳሮቶች የመጀመሪያውን እንዴት እንዳቀረቡ አስታውሰዋል፡ "በውስጣዊ ሕይወት ትምህርታችን እርዱን።" ማን እንደሆንን ወይም የሕይወትን ትርጉም ምን እንደሆነ ካላወቅን ሰፊ እውቀት መኖሩ በቂ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
"ያለዝምታ፣ ያለማዳመጥ፣ ያለጸሎት፣ የከዋክብት ብርሃን እንኳን ይጠፋል" ሲሉ አስረድተዋል። አንዳንዶች በተለያዩ መንገዶች የባዶነት ወይም የእረፍት ማጣት ስሜት አጋጥሟቸው ሊሆን ይችላል፣ ይህም ዓመፅን፣ ጉልበተኝነትን፣ ጭቆናን ጨምሮ። ነገር ግን ከዚህ በስተጀርባ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አጉልተው ሲናገሩ፣ "የሰውን ልጅ መንፈሳዊ ገጽታ እንዴት መፍጠር እንደሚቻል የረሳ ማህበረሰብ የተፈጠረ ባዶነት፣ በቴክኒካዊ፣ በማህበራዊ ወይም በሥነ ምግባራዊ የሕይወት ገጽታዎች ላይ ብቻ በማተኮር" የተነሳ የተፈጠረ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የቅዱስ አውጉስጢኖስን የሕይወት ታሪክ፣ "የቅዱስ አጉስጢኖስ ኑዛዜ" በተሰኘው ግለ ታሪክ ለውስጣዊ ሕይወት ራሳችንን እንዴት ማስተማር እንዳለብን እንድናይ ሊረዳን ይችላል። እረፍት ማጣትን፣ ማዳመጥ እና ከእሱ መሸሽ ወይም ባዶነቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ባሉ ነገሮች መሙላት አለብን። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለብዙ ነገሮች ስለተፈጠርን መረጋጋት እንዳለብን አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
በዲጂታል ዓለም ውስጥ ትምህርት
ሁለተኛው የአዲሱ የትምህርት ተግዳሮት እነዚህ ወጣት ተማሪዎች በእውነቱ አስተማሪዎች የሆኑበት የዕለት ተዕለት ቁርጠኝነት ነው፡ ዲጂታል ትምህርት። እዚህ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። በዲጂታል ዓለም ውስጥ እንኖራለን፣ ነገር ግን ቴክኖሎጂ ታሪካችንን እንዲጽፍልን ወይም እንዲጠቀምብን መፍቀድ የለብንም ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ወደ ዘመናዊው ዓለም ሌላ ተግዳሮት ሲመለሱ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ጠቅሰው፣ “ብልህ” ቢሆንም፣ አሁንም በሰብአዊነት ለመንቀሳቀስ ልንጠቀምበት እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። “ዲጂታልን ሰብአዊነት መማር፣ አንድ ወንድማማችነት እና የፈጠራ ቦታ መገንባት አለብን - ሱስ ወይም ማምለጫ ሳይሆን” እዚህ ላይ፣ የቅዱስ ካርሎ አኩቲስን ሕይወት በቴክኖሎጂ ዘመን የቅድስና ምሳሌ አድርገው ጠቅሰዋል።
ሰላም እና ትምህርት
የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ፕሮጀክት ሦስተኛው ተግዳሮት ትምህርት ለሰላም የሚለው መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው “በአዲሱ ዓለም አቀፍ የትምህርት ስምምነት እምብርት ላይ” ያለው ተግዳሮት በጦርነት፣ በጥላቻ እና በመከፋፈል የተጋረጠውን የወደፊት ሕይወት የመቀየር ኃይል አለን ወይ የሚለው ሲሆን፥ መልሱ “የሰላም ትምህርት ትጥቅ የሚፈታና ትጥቅ የምያስፈታ ነው" ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
ነገር ግን ይህ የጦር መሳሪያዎችን ዝም ከማሰኘት በላይ ነው ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስረድተዋል። “ልቦችን ትጥቅ ማስፈታት፣ ሁሉንም ዓመፅና ጸያፍ ድርጊቶችን መተው አለብን” ትጥቅ የሚፈታና ትጥቅ የሚወረደው ትምህርት ለሁሉም ሰው እኩልነትና እድገት ለመፍጠር ተደራሽ ሲሆን ብቻ ነው፣ እንዲሁም የሁሉንም ሰው ክብር በመገንዘብ እና በሰዎች መካከል መከፋፈልን በማስወገድ ነው ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በስፍራው የተገኙትን ተማሪዎች ሁሉ በመጀመሪያ በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ሰላም ፈጣሪዎች እንዲሆኑ ጋብዘዋል። የሚተኮሱ ኮከቦችን እንዳይፈልጉ አሳስበዋል። ይልቁንም “ወደላይ ተመልከቱ፣ ‘የጽድቅ ፀሐይ’ ወደሆነው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እሱም ሁልጊዜ በሕይወት ጎዳናዎች ላይ ይመራችኋል” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።
