ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለቫቲካን የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች 'ጸሎታችን ለውጥ ያመጣል' ማለታቸው ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
"በእየዕለቱ ትንሽ በትንሽ እያወቃችሁ መጥቻለሁ… በጣም ብዙዎቻችሁ... የጳጳሱን ቃላት እና ድርጊቶች በሁሉም ቦታ ለማሰራጨት በጋለ ስሜት እንደምትሰሩ አውቃለሁ። ይህንን በየቀኑ በጥበብ እና ብዙም ጎላ ብላችሁ ሳትታዩ በዚህ መንገድ ሥራችሁን ታከናውናለችሁ። እናንተን ለማየት እና ለመገናኘት ዕድሉን ስላገኘሁ ዛሬ ደስተኛ ነኝ፣ ምክንያቱም - በተለይም በዚህ የቤተሰብ ሁኔታ ፣ ሁላችሁም በአንድ ላይ ተሰብስባችሁ በማየቴ ደስተኛ ነኝ"።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በቫቲካን እምብርት ላይ የሚገኘው የቫቲካን የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ጋዜጠኞችና ሠራተኞች፣ “የቫቲካን ኮሙኒኬሽን ዋን ጽ/ቤት ትልቅ የሥራ እና ማህበረሰብ አቀፍ የሆነውን ሥራችሁን ለማድነቅ ከእናንተ ጋር ትንሽ ጊዜ በማሳለፌ ደስተኛ ነኝ” ብለዋል።
እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ያለ የቤተሰብ ግንኙነት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እነሱን በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጿል "በቤተሰብ ቅርፀ እንበልና በዚህም ከእናንተ ጋር ደስተኛ ነኝ። ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን ቤተሰብ ናት፣ የቤተሰብ ቤተሰብ ነች" ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
በተጨማሪም በታዋቂው ፓላዚና ሊዮን 13ኛ - በቫቲካን የአትክል ስፍራ ውስጥ በሚገኘው የማርኮኒ ሬዲዮ ጣቢያ የመጀመሪያ መቀመጫ ፊት ለፊት በመገኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል ።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ሰራተኞችን በጥረታቸው ውስጥ የጸሎትን አስፈላጊነት በማስታወስ አመስግነዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎታቸው ከጸሎት ጋር መያያዙ ምንኛ አስፈላጊ ነው!” ሲሉ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
ጸሎታችን ለውጥ ሊያመጣ ይችላል
"ጸሎት የልብ ለውጥ ያመጣል ብዬ አምናለሁ" በማለት የተናገሩት ቅዱስነታቸው በመቀጠል "አለም ይህን ላያውቀው ይችላል፣ ላያስተውለው ይችላል - እኛ ግን እናደርጋለን፣ እናውቃለን እና ሁልጊዜም ይህን ለማድረግ መሞከር አለብን፣ በየቀኑ ሥራችንን በጸሎት መጀመር አለብን" ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
"ይህ ሁሉንም ለውጥ ያመጣል እላለሁ፣ አለም ይህን ላያውቀው ይችላል፣ ላያስተውለው ይችላል - ግን እናደርገዋለን፣ እናውቀዋለን፣ እና ሁልጊዜም ይህን ለማድረግ መሞከር አለብን። የእለት ተእለት ሥራችንን እና ተግባራችንን ከጸሎት አጋር አዋጅተን መጀመር ይኖርብናል" ማለታቸው ተገልጿል።
የቫቲካን ኮሙዩኒኬሽን ዋና ጽ/ቤት ባለሙያዎች ከተለያዩ አገሮች፣ ከተለያዩ ቋንቋዎችና የሥራ ዓይነቶች መምጣታቸውን ቅዱስ አባታችን ገልፀው፣ “ይህ ሁሉ ልዩነት ግን ለአንድ ዓላማ ብቻ የሚያገለግል ነው፤ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትና ብፁዓን ጳጳሳት የሚናገሯቸውን የምሥራቹን ቃል ለዓለም ሁሉ እንዲያስተላልፉ ለመርዳት ነው” ብለዋል።
" ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በመጀመርያው መልእክቱ እንደጻፈው የጸጋ ስጦታ ልዩ ልዩ ነው፣ መንፈስ ግን አንድ ነው፤ አገልግሎት ልዩ ልዩ ነው፣ ጌታ ግን አንድ ነው፤ ሥራም ልዩ ልዩ ነው፥ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው" (1ቆሮ 12፡4-11) የሚለውን ቅዱስነታቸው ጠቀሰዋል።
ጤናማና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ያለው አውታረ መረብ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ይህንንም በማድረግ “የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንዳሉት፣ ‘በመውጣት’ ማለትም ይህንን መረብ በቅድስት መንበር እና በዓለም መካከል በመዘርጋት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ‘ወደ ጥልቁ መውጣት’ ያስፈልጋል" ሲሉ አጽኖት ሰጥተው ገልጸዋል።
"ከሁሉም በላይ አስፈላጊው ነገር ሰዎች እርስ በእርሳቸው አውታረመረብ መፍጠር መቻላቸው ነው፣ እያንዳንዳቸው የራሳቸው ክህሎት ያላቸው፣ ለቤተክርስቲያኗ የቀረቡ ... ለአለም የቀረበውን እውነትን ለመካፈል፣ ሰዎች እንዲያዩ እና እንዲረዱ ለመርዳት - ሁል ጊዜ በፍቅር መከናወን አለበት" እና " ሚናዎች የተለያዩ ናቸው፣ ነገር ግን ማንም ከሌላው የበለጠ አስፈላጊ አይደለም፣ የተለያዩ አገልግሎቶች ቢኖሯቸውም ቅሉ ሁሉም ሰዎች እኩል ናቸው" ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
የቫቲካን የኮሙዩኒኬሽን ዋና ጽ/ቤት ሰራተኞች በየአመቱ ቀለል ባለ መንገድ ለሽርሽር እንደሚሰበሰቡ ጳጳሱም አስታውሰዋል። "ይህ በጣም ጥሩ ነው፡ ከስራ ጎን ለጎን የመዝናናት እና የጸሎት ጊዜያትን ማካፈል ትችላላችሁ።"
ሆኖም፣ ቅዱስ አባታችን፣ “በዚህ ጊዜ፣ ዛሬ ለማድረግ መርጣችኋል፣ ስለዚህ በኋላ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ አብረን ተጉዘን ስለ ሰላም አብረን ለመጸለይ እንችላለን” በማለት ተናግረዋል።
በፍቅር የተደርገ ቡራኬ
ቅዱስነታቸው በመጨረሻም ለዚህ ውብ እና ስላሳለፉት መልካም ጊዜ የዋና ጽ/ቤቱን ሠራተኞች በማመስገን ንግግራቸውን አጠናቀዋል።
“ሁላችሁንም በፍቅር እባርካችኋለሁ፣ በተለይም ሕጻናትና የምትወዷቸው ታማሚዎችን በፍቅር ለመባረክ እወዳለሁ” ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትርዳችሁ፣ ቤተሰቦቻችሁንም ትጠብቅላችሁ፣ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ!" ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን በአንድነት ወደ አባታችን እንዲጸልዩ ጋብዟቸዋል፡- “አሁን ከታናናሾቹና ከትላልቅ ሰዎች ጋር እግዚአብሔር አባት እንደ ሆነ ሁላችንም እናውቃለንና ኢየሱስ እንዳስተማረን አብረን እንጸልይ" ብለው 'አባታችን ሆይ' የሚለውን ጸሎት በጋራ ካደረጉ በኋላ ቅዱስነታቸው ታዳሚያኑን ተሰናብተዋል።
