ር.ሊ.ጳ ሊዮ በሕብረት መመላለስ የቤተክርስቲያን የአኗኗር ዘይቤ ነው ማለታቸው ተገለጸ።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
እነዚህ የጥናት ቀናት “በአንድነት መመላለስ የቤተክርስቲያን የህይወት ዘይቤ እና ተልእኮ እንደሆነ ለታደሰ ግንዛቤ” ያነሳሳ በማለት በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህን ተስፋ ነበር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በመካከለኛው ጣሊያን በሚገኘው በካማልዶሊ ሄርሚቴጅ እየተካሄደ ባለው የቲዮሎጂ ወይም የነገረ መለኮት ኮንፈረንስ ‘በሲኖዶሳዊው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምን ዓይነት ጳጳስ ያስፈልጋል?’በሚል አመሪ ቃል እየተካኤደ ላለው ስብሰባ ተሳታፊዎች ባስተላለፉት መልእክት የገለጹት።
እ.አ.አ ከጥቅምት 6 እስከ 9/2025 ዓ.ም ለአራት ቀናት የሚቆየው ይህ ስብሰባ የጳጳስ አገልግሎት በሲኖዶሳዊ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን መልክ እና አገልግሎት ለመዳሰስ ያለመ ሲሆን ቤተክርስቲያን የጳጳሳትን አገልግሎት ከሲኖዶሳዊ እይታ አንፃር በማሰብ እንዴት የሲኖዶሳዊ ዘይቤን እና መዋቅርን ማዳበር እንደምትችል ለማወቅ እና ለመዳሰስ የሚፈልግ ስብሰባ እንደ ሆነም ተገልጿል።
የጳጳሱ መልእክት
የቫቲካን ዋና ጸኃፊ በሆኑት በብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የተፈረመ እና የካማልዶሌዝ የቅዱስ በነዲክቶስ ማሕበር አባል ዋና አለቃ ለሆኑት ለአባ ማትዮ ፌራሪ በላኩት የጹሑፍ መልእክት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስብሰባውን “ጉልህ” ብለው ጠርተው “በመንፈስ” በስፍራው እንደተገኙም አክለው ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።
“ለሥነ መለኮት እና ለቤተ ክርስቲያን ጥልቀት ያለው” ተነሳሽነት አድናቆታቸውን ቅዱስነታቸው ገልጿል።
ተስፋው ስብሰባው “በአንድነት መመላለስን” አዲስ ግንዛቤ እንዲቀሰቅስ የምያደርግ ነው፣ ምክንያቱም “እውነተኛው ሲኖዶሳዊ በባህሪው እንደ እያንዳንዱ ጥሪ መሠረት ማዳመጥ እና የተጠመቁ ሰዎችን ሁሉ ተሳትፎ ይጠይቃል” - ነገር ግን፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አጽንዖት ሰጥተው እንደ ግለጹት “የጴጥሮስን ተተኪ ሆነው እንዲመሩ ክርስቶስ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሰጠውን ሥልጣን ችላ ማለት አንችልም" ብለዋል።
