ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እና ብፁዕ ወቅዱስ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እና ብፁዕ ወቅዱስ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ   (@Vatican Media)

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የመጀመሪያ ሐዋርያዊ ጉብኝት ‘በአንድነትና በሰላም ጎዳናዎች ላይ’!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሕዳር 18 እስከ ሕዳር 23/2018 ዓ.ም በቱርክ እና በሊባኖስ በቀድም ተከተል ለምያደርጉት የመጀመርያው ሐዋርያዊ ጉብኝት ሲዘጋጁ፣ ይህንን የቅዱስነታቸውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስመልከት የቫቲካን ዜና የአርታኢ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አንድሪያ ቶርኔሊ ይህ የቀዱስነታቸው የመጀመርያው ሐዋርያዊ ጉብኝት ለመካከለኛው ምስራቅ የአንድነትና የሰላም ምልክት እንደሆነ በመቁጠር የራሳቸውን የዳሰሳ ውጤት እንድሚከተለው ያቀርባሉ።

በአንድሪያ ቶርኒዬሊ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ የተመራው እና በጀርመን ኮለን እ.አ.አ በ2005 ዓ.ም በተካሄደው የዓለም ወጣቶች ቀን እና እ.አ.አ በ2013 ዓ.ም በብራዚል በሪዮ ዴ ጄኔሮ በቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የተመራው የአለም የወጣቶች ቀን ጋር እንደነበረው ሁሉ፣ የርዕሰ ሊቀ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የመጀመሪያ ሐዋርያዊ ጉብኝት ቀደም ሲል በቀደመው ጊዜ ወደ ነበረው የተወሰነ ቦታ ይወስደናል።

ምንም እንኳን ጦርነትና ሕመም የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የገቡትን ቃል ለመጠበቅ የመጀመሪያውን የኒቂያ ጉባኤ የተከናወነበት 1700 የመታሰቢያ አመት ክብረ በዓል ለማክበር ወደ ቱርክ ለመሄድ ያቀዱት ዕቅድ እና በጦርነት የተጎዳውን ሊባኖስን ለመጎብኘት ያቀዱትን ዕቅድ ምንም እንኳን ጦርነትና ሕመም እቅዳቸው እንዳይፈጽም ልያደርጉ አልቻሉም።

የአንድ ርዕሰ ሊቀ ጳጳሳት የመጀመሪያ ሐዋርያዊ ጉብኝት ጵጵስናቸውን ለማክበር የታሰበ ነው። እ.አ.አ በጥር 1964 ዓ.ም ወደ ቅድስት ምድር ታሪካዊ ጉዞ ያደረጉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክን አቴናጎራስን ተቀብለው ማነጋገራቸው ይታወሳል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የመጀመሪያውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ወደ ሜክሲኮ ፑብላ አድርገው የነበረ ሲሆን የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በበኩላቸው  በመጀመርያው ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በብራዚል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችን ተቀብለው አስተናግደዋል።

በአንድ አጋጣሚ፣ ሐሙስ ሕዳር 18/2018 ዓ.ም የሚጀምረው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሐዋርያዊ ጉብኝት መጀመሪያ ወደ አንካራ፣ ኢስታንቡል እና ኢዝኒክ ከዚያም ወደ ቤሩት የሚያቀና ሲሆን በእነዚህ የጵጵስና ሥልጣናቸው የመጀመሪያ ወራት ውስጥ ብቅ ያሉ ሁለት ዋና ዋና ጭብጦችን ማለትም አንድነት እና ሰላምን ያመለክታል።

አንድነት በመጀመሪያው ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህም የቤተክርስቲያኗን ታሪክ በማይሻር ሁኔታ የገለጸውን የኒቂያ ጉባኤን ለማስታወስ የሚረዳ ነው። ይህንን መደበቅ ምንም ፋይዳ የለውም፡ የኒቂያን ጉባኤ እውነታ  በተከፋፈለች ቤተክርስቲያን ቁስል፣ ደም መፍሰስ የቀጠለ እና በቅርብ ዓመታት ውስጥ አዳዲስ ክፍተቶች የሚታዩበት ቁስል ነው።

አብያተ ክርስቲያናት አንድ ሆነው ወደተገናኙበት ዘመን፣ የፋሲካን ቀን ለማዋሃድ ወደተካሄደው ጉባኤ ሕያው ትዝታ ይዞ መመለስ የተስፋ ምልክት ነው።

"ይህም ሁሉም አንድ እንዲሆኑ፥ አንተም፥ አባት ሆይ! በእኔ እንዳለህና እኔም በአንተ እንዳለሁ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ እንዲሆኑ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ ዓለም እንዲያምን ነው" (ዩሐ 21፡17) በሚለው የቤተክርስቲያኗን አንድነት፣ በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን አንድነት፣ የኅብረት ውይይትን፣ ወደ ወንጌል፣ የቀድሞ አባቶች የመጀመሪያዎቹን ጉባኤዎች መሠረት መመለስን ማሰላሰል በኢየሱስ ቃላት እንድንነካ የሚያደርገን መንገድ ነው።

በክርስቶስ የሚያምኑ ሰዎች አንድነት ለወንጌል አዋጅ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሰላምም ዋጋ አለው። ይህ ሰላም ኢየሱስ በምድራዊ ሕይወቱ በኖረበት ምድር፣ በተለይም በእስራኤልና በፍልስጤም ግዛቶች፣ እና በሊባኖስ፣ በእስራኤል ጦር በቦምብ ድብደባ ባካሄደበት የሂዝቦላ ታጣቂዎች ላይ በትክክል በወደመው አከባቢ የሰላም ምልክት ሊሆን ይችላል።

የሐዋርያዊ ጉብኝት ሁለተኛው ደረጃ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የሰው ልጆች በተለይም ሲቪሎችን በተለይም በሕፃናት ላይ መከራ ያስከተለ ግጭት ባለበት ክልል ውስጥ ያመጣቸዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሊዮ ከትንሣኤ በኋላ ኢየሱስ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” ሲል የተናገራቸውን የመጀመሪያ ቃላት በመጠቀም ራሳቸውን ለዓለም አቅርበዋል።

አሁን ለአስርተ ዓመታት ሰላምን የማያውቁትን ሕዝብ ቁስል ለመመርመር ይሄዳሉ። የጦር መሣሪያ አስከፊነት የሚገልጸውን ምስክርነታቸውን በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንኳን የቦምብ ጩኸት ወደተሰማበት ቦታ ሰላም ለማምጣት ይሄዳሉ፣ ይህም የጦርነት፣ ጥላቻ እና ዓመፅ የማይቀር ነገር እንደሆነ እና ጦርነትን ‘በቃ!’ ለማለት ነው።

በዚያች አገር እና በአጎራባች አገሮች የሚኖሩትን እና መሬታቸውን ጥለው ለመሄድ የሚፈተኑትን ክርስቲያኖች ለማጽናናት ይሄዳሉ፣ መገኘታቸው ምን ያህል ውድ እንደሆነ እና ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር የወንድማማችነት እና የሰላም አብሮ የመኖር ምስክርነታቸው ምን ያህል ውድ እንደሆነ ለማስታወስ ይህንን የመጀመርያውን ሐዋርያዊ ጉብት ቅዱስነታቸው ያከናውናሉ።

27 Nov 2025, 13:16