ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ   (@Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ ቱርክ እና ሊባኖስን ከመጎብኘታቸው በፊት ጸሎት እንዲደረግላቸው ጥሪ አቀረቡ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ዘወትር ረቡዕ እለት ከቫቲካን ሆነው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደምያስተምሩ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በህዳር 17/2018 ዓ.ም ካደርጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል ባስተላለፉት መልእክት ከሕዳር 18 እስከ ሕዳር 23/2018 ዓ.ም በቱርክ እና በሊባኖስ በቀድም ተከተል የምያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተሳካ ይሆን ዘንድ ምዕመናን ጸሎት እንዲያደርጉላቸው የጠየቁ ሲሆን ቅዱስነታቸው በቱርክ እና ሊባኖስ ስለሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ሲያስቡ፣ “በታሪክ እና በመንፈሳዊነት የበለፀጉ” ሁለት አገሮችን ለመጎብኘት በመዘጋጀታቸው ቅዱስነታቸው ደስታ እንደ ተሰማቸው ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው ከሕዳር 18 እስከ ሕዳር 21/2018 ዓ.ም በቱርክ ለምያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የመረጠው  አርማ
ቅዱስነታቸው ከሕዳር 18 እስከ ሕዳር 21/2018 ዓ.ም በቱርክ ለምያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የመረጠው አርማ

ቅዱስነታቸው ከሕዳር 18 እስከ ሕዳር 21/2018 ዓ.ም በቱርክ ለምያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የመረጠው  አርማ "አንድ ጌታ፥ አንድ እምነት፥ አንድ ጥምቀት" (ኤፌሶን 4፡5) የተሰኘ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የተካተተበት ሲሆን የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት እንዳስታወቀው፣ በዐርማው ላይ የድልድይ ምስል ይታያል፣ በድልድዩ ስር የጥምቀት ውሃዎችን እንዲሁም የኢዝኒክ ሐይቅን ለመግለጽ የተጠቀሙበት ሞገዶች ይታያሉ። በአርማው በስተቀኝ እ.አ.አ የ2025 ዓ.ም የኢዮቤልዩ መስቀል አለ፣ ከላይ በግራ በኩል ደግሞ ሦስት የተጠላለፉ ቀለበቶች ቅድስት ሥላሴን የሚወክሉ ምስሎች ተቀምጠዋል። ዐርማው በክብ ምስል የተሰራ ነው፣ ክቡ የእግዚአብሔርን አንድነት ያመለክታል፤ ድልድዩን፣ ሕዝቦችን አንድ የሚያደርግ አንድ እምነት፤ እንዲሁም ማዕበሎቹ፣ ለእግዚአብሔር ልጆች አዲስ ሕይወት የሚሰጥ ጥምቀት ይገልጻል” ሲል የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽሕፈት ቤት ተናግሯል። “ይህም በምስራቅና በምዕራብ አገራት መካከል ወንድማማችነትንና ውይይትን እንድንገነባ ይጋብዘናል” ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።

ቅዱስነታቸው ከሕዳር 21 እስከ ሕዳር 23/2018 ዓ.ም በሊባኖስ ለምያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተመረጠው አርማ
ቅዱስነታቸው ከሕዳር 21 እስከ ሕዳር 23/2018 ዓ.ም በሊባኖስ ለምያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተመረጠው አርማ

ከሕዳር 21 እስከ ሕዳር 23/2018 ዓ.ም በሊባኖስ ለምያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተመረጠው የዚህ ጉዞ አርማ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን በቀኝ እጃቸው በእየባረኩ የምያሳይ ምስል የተካተተበት ሲሆን፣ ከርግብ ምስል ጎን ለጎን ሰላምን የሚያመለክት እና የሊባኖስን የበለፀገ የእምነት እና የሃይማኖት መካከል ያለውን ስምምነት የሚወክል የዝግባ ዛፍ ያሳያል። በምስሉ በስተቀኝ እ.አ.አ ከ2025 ዓ.ም የኢዩቤሊዩ አርማ የተወሰደ መስቀል ምስል ተቀምጧል፣ በክርስቶስ ላይ ባለ እምነት ላይ የተመሠረተ ጽኑ ተስፋን ያመለክታል።

“ጥልቅ ሰማያዊ፣ ለስላሳ ሮዝ ወይም ሐምራዊ፣ አረንጓዴ እና ቀላል ሰማያዊ ቀለሞች ጸጥታን ወይም ሰላምን ይገልጻሉ፣ በነጭ የተዋሃዱ፣ የሊባኖስን የሰላም ናፍቆት ለማንፀባረቅ በማሰብ የተቀመጠ ነው” በማለት የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽሕፈት ቤት መግለጫ ያመለክታል።

ከማቴዎስ ወንጌል የተወሰደው “ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው" (ማቴ. 5፡9) የሚለው ጥቅስ “የጉብኝቱን ዋና መልእክት የያዘ ሲሆን ይህም የሊባኖስን ሕዝብ ማጽናናት እና በሁሉም ማህበረሰቦች መካከል ውይይት፣ እርቅ እና ስምምነትን ለማበረታታት ታስቦ የተቀመጠ መሆኑን የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽሕፈት ቤት መግለጫ አክሎ ገልጿል።

ይህ ረቡዕ ሕዳር 17/2018 ዓ.ም የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካደረጉ በኋላ ቅዱስነታቸው ወደ ቱርክ እና ሊባኖስ የምያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ከመጀመራቸው በፊት በሮም ካደረጓቸው የመጨረሻ ይፋዊ ንግግሮች አንዱ ነበር

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በእለቱ በተከናወነው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ማብቂያ ላይ  ስለሚያደርጉት የመጀመሪያ የውጭ ጉዞ ጉብኝት፣ የሚጓዙባቸውን አገሮች “በታሪክ እና በመንፈሳዊነት የበለፀጉ” ሲሉ ገልጸው ነበር።

ጉዞአቸው፣ በቱርክ ውስጥ በኒቂያ፣ በዘመናዊው ኢዝኒክ፣ በቱርክ ውስጥ በኒቂያ በተካሄደው “የመጀመሪያው የክርስቲያኖች ሕብረት ጉባኤ "ኤኩሜኒካል"1,700ኛ ዓመት መታሰቢያ ዓመት በዓል ለማክበር” እና “ከካቶሊክ ማህበረሰብ፣ ከክርስቲያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እና ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር ለመገናኘት” እድል እንደሚፈጥር የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ምዕመኑ “በጸሎታቸው እንዲያስቧቸው እና በመንፈስ አብሮዋቸው እንዲጓዙ" በመጠየቅ አስተያየታቸውን አጠናቀዋል።

የመጀመሪያው ሐዋርያዊ ጉብኝት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሐሙስ ሕዳር 18/2018 ዓ.ም እኩለ ቀን አካባቢ ላይ ቱርክ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፣ እናም ከቱርክ ባለስልጣናት ጋር ከመነጋገራቸው በፊት ከቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር በግል ይገናኛሉ።

አርብ ዕለት ሕዳር 19/2018 ዓ.ም በዘመናዊቷ ኢዝኒክ፣ ኒቂያ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የክርስቲያን ሕብረት ጉባኤ በመባል የሚታወቀውና እ.አ.አ በ325 ዓ.ም የተከናወነው የክርስቲያኖች ሕብረት ጉባኤ 1,700ኛ የመታሰቢያ ዓመት ክብረ በዓልን ለማክበር በሚደረገው የጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይ ይሳተፋሉ።

ቅዳሜ ዕለት ሕዳር 20/2018 ዓ.ም በኢስታንቡል ቮልስዋገን አሬና በተሰኘው ሥፍራ ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴን ያሳርጋሉ፣ እሁድ እለት ሕዳር 21/2018 ዓ.ም ወደ ሊባኖስ ይጓዛሉ። እዚያም ከአካባቢው ባለስልጣናት፣ ከቤተክርስቲያን መሪዎች፣ ከሌሎች ሃይማኖቶች ተወካዮች እና ወጣቶች ጋር ይገናኛሉ።

ማክሰኞ ዕለት ሕዳር 23/2018 ዓ.ም በቤሩት የውሃ ዳርቻ ሕዝብ በተሰበሰበበት ሥፍራ መስዋዕተ ቅዳሴ እንደሚያሳርጉ የሚጠበቅ ሲሆን ከእዚያም በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር አመሻሹ ላይ 12፡00 ገደማ ወደ ሮም እንደሚመለሱ ለቅዱስነታቸው ከወጣው የሐዋርያዊ ጉብኝት የድርጊት መርሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል።

'ቀጥሉ፣ አይዟችሁ'

የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ብጽዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ከቫቲካን ኒውስ ጋር ባደረጉት ቆይታ  ቅዱስነታቸው በቱርክ የምያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት "የመጀመሪያዎቹ ማህበረሰቦች የተቋቋሙበት የክርስትና መገኛ ነበረች" ብለዋል።

“የኒቂያ ጉባኤ” ካርዲናል አፅንዖት ሰጥተው እንደ ተናገሩት ከሆነ “ኢየሱስ ክርስቶስን ሙሉ በሙሉ መለኮታዊ እና ሙሉ በሙሉ ሰው አድርጎ ማመን የምያስችለውን የእምነታችንን መሠረት ጥሏል፤  ብለዋል።

ካርዲናል ፓሮሊን የሊባኖስን ጉብኝት አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተውታል፤ “በቅርብ ዓመታት ውስጥ ተጽዕኖ ያሳደረውን ቀውስ በመፍታት ረገድ የተወሰነ እድገት አሳይቷል” ብለዋል።

አሁን አገሪቱ “ፕሬዝዳንት፣ መንግሥት አላት፤ እናም ሁኔታው መልካም ነው” ሲሉ ካርዲናል ፓሮሊን ተናግረዋል። “ነገር ግን የሕዝቡን ግምት ሊያዘገዩ ወይም ሊያደናቅፉ የሚችሉ ብዙ ችግሮች፣ መዘግየቶች እና እንቅፋቶች አሁንም አሉ” ብለዋል።

በዚህ አውድ ካርዲናል ፓሮሊን ሲናገሩ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክት “ማበረታቻ” የሚል ሲሆን “መሄድህን ቀጥል፣ ድፍረት ይኑርህ፣ በጀመርከው መንገድ ቀጥል” የሚል ግብዣ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

26 Nov 2025, 16:32