ር.ሊ.ጳ ሊዮ ትምህርት የተመሰረተው በውስጣዊ፣ አንድነት፣ ፍቅር እና ተስፋ ላይ ነው ማለታቸው ተገለጸ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ለትምህርት ዓለም ኢዮቤልዩ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከዓለም ዙሪያ ለተውጣጡ አስተማሪዎች ያደረጉት ንግግር መሰረቱን ያደርገው በቅዱስ አጎስጢኖስ የትምህርት ተቋማት መምህር በነበሩበት ወቅት በራሳቸው ላይ ተንተርሰው ነበረ ልምዳቸውን ያካፈሉት።
የውስጥ ሕይወት፣ አንድነት፣ ፍቅር እና ደስታ፣ የቅዱስ ቶማስ አኩዊናስ አስተምህሮ አራት ቁልፍ ገጽታዎች መሆናቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው እነዚህ እንደ አውጉስቲኒያን ማሕበር እንደ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ገለጻ፣ የክርስቲያን ትምህርት መሠረቶች ናቸው ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በንግግራቸው እነዚህ የትምህርት ልምምዶች "ቁልፍ አካላት" እንዲሆኑ አሳስበዋል፣ ይህም "ለብዙ ተማሪዎች እራሳችሁን ለትምህርት የምትሰጡበት የቤተክርስቲያን (...) እናት እና መምህር (...) ፊትን ለማንጸባረቅ ይረዳል" ብለው እንደምያምኑ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።
ጥልቅ የሰው ልጅ ግንኙነት
የቅዱስ አውጉስጢኖስን አባባል በመጥቀስ - "የቃላችን ድምፅ ጆሮን ይመታል፣ እውነተኛው መምህር ግን ለውስጣችን ይናገራል" በማለት የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አድማጮቻቸውን "ውብ ቃላት ወይም በሚገባ በድጋፍ መስጫ መሣሪያዎች የታጠቁ ክፍሎች፣ ላቦራቶሪዎች እና ቤተ መጻሕፍት ለማስተማር በቂ ናቸው ብሎ ማሰብ ስህተት ነው" ብለው መናገራቸውም ተገልጿል።
“እነዚህ በቀላሉ የሚገኙ እና አካላዊ ቦታዎች ናቸው፤ በእርግጥም ጠቃሚ ናቸው፤ ነገር ግን አስተማሪው በውስጡ መገኘት አለበት" ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን እውነት በድምጾች፣ በግድግዳዎች ወይም በኮሪደሮች ውስጥ እንደማይፈስ አፅንዖት ሰጥተው ተንግረዋል፣ ነገር ግን “በሰዎች መካከል ባለው ጥልቅ ግንኙነት ውስጥ ነው እውነት የሚፈሰው ያሉት ቅዱስነታቸው - ያለነዚህ እያንዳንዱ የትምህርት ሀሳብ ውድቅ ይሆናል” ብለዋል።
ውስጣዊ
ይህንን አስተንትኖ በመቀጠል፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ዛሬ ተማሪዎች “ከውስጣዊ ማንነታቸው ጋር ለመገናኘት” እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አስታውቀዋል፣ ይህም “በስክሪኖች እና በቴክኖሎጂ ማጣሪያዎች በተሞላ ዓለም” ውስጥ ያለውን የላቁነት ፈተና አፅንዖት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን በተጨማሪም አስተማሪዎች እንኳን - “ብዙውን ጊዜ በቢሮክራሲያዊ ተግባራት የሚደክሙ እና ይህንን ጉድያ የተሸከሙ ቢሆንም ቅሉ” በላቲን ቋንቋ "ኮር አድ ኮር ሎኪቱር"ን (ልብ ለልብ ይናገራል) ይህም የቅዱስ ጆን ሄንሪ ኒውማን አገላለጽ ነው፣ የመርሳት እውነተኛ አደጋ እንደሚገጥማቸው ጠቁመዋል፣ እሱም የቅዱስ አጎስጢኖስን “ከውጭ አትመልከት። ወደ ራስህ ተመለስ። እውነት በውስጥህ ትኖራለች” ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
እንደ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ገለጻ፣ እነዚህ ሁለት አገላለጾች ትምህርትን “መምህራን እና ተማሪዎች አብረው የሚሄዱበት ጉዞ" እንደ ሆነ ገልጸው - ፍለጋቸው ፈጽሞ ከንቱ እንዳልሆነ፣ ነገር ግን ካገኙ በኋላም ቢሆን መፈለግ እንዳለባቸው” ይጋብዙናል ብለዋል።
“ይህ ትሑትና የጋራ ጥረት ብቻ ነው” ብለዋል፣ “በትምህርት ቤት ውስጥ የትምህርት ፕሮጀክት መልክ የሚይዘው፣ ተማሪዎችንና መምህራንን ወደ እውነት ሊያቀርብ ሲችል ብቻ ነው” ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
አንድነት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በአንድነት ጭብጥ ላይ ተንተርሰው በላቲን ቋንቋ “ኢሎ ኡኖ ኑም ኢስት” (“አንድ በሆነው በእርሱ፣ እኛ አንድ ነን") በሚለው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘመናቸው መሪ ቃል ጽንሰ-ሀሳብ ላይ በማተኮር “በእውነት አንድነትን የምናገኘው በክርስቶስ ውስጥ ብቻ ነው፣ አባላት ራስ ከሆነው ከእርሱ ጋር ሲቀላቀሉ እና በህይወት ዘመን የመማር መንገድ ላይ እንደ ጓደኛሞች ሆነው ሲጓዙ ብቻ ነው” ብለዋል።
በቅዱስ አውጎስጢኖስ ጽሑፎች ውስጥ የሚታየው ይህ “የአንድነት” ገጽታ በትምህርት አውዶች ውስጥ መሠረታዊ ነው ብለዋል፣ ለራስ ወዳድነት ፈተና እና ለእድገት ማነቃቂያ" የሚሆን ሐሳብ ነው ብለዋል።
ፍቅር
ወደ ሦስተኛው ነጥብ ስንመለስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ለማስተማር፣ እውቀትን ማጋራት ብቻውን በቂ አይደለም-ፍቅር መኖር አለበት” ብለዋል።
“ማስተማር ከፍቅር ፈጽሞ ሊለይ አይችልም” በማለት አክለው የተናገሩት ቅዱስነታቸው “እና ዛሬ ካሉት የኅብረተሰባችን ፈተናዎች አንዱ መምህራንና አስተማሪዎች በዚህ ረገድ ለኅብረተሰቡ የሚያደርጉትን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በበቂ ሁኔታ ማድነቅ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
ፍቅር ተሳተፊ ሲሆን ብቻ ነው ማስተማር በእውነት ፍሬያማ የሚሆነው -- "በይዘቱ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም በላይ በሚያስተላልፈው ልግስና" የተነሳ ነው ብለዋል።
ደስታ
በመጨረሻም ስለ ደስታ ጭብጥ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሲናገሩ “እውነተኛ አስተማሪዎች በፈገግታ ያስተምራሉ፣ ፈተናቸውም በተማሪዎቻቸው ነፍስ ውስጥ ጥልቅ ፈገግታዎችን ማንቃት ነው” ብለዋል።
የዛሬው የትምህርት አካባቢ “በሁሉም ዕድሜ ላይ ሰፊ የሆነ የውስጥ ድክመት ምልክቶች” እያሳየ መሆኑን በመግለጽ ስጋታቸውን ገልጸዋል። “ከእነዚህ ጸጥ ያሉ የእርዳታ ጩኸቶች ፊት ለፊት ሆነን ዓይኖቻችንን መጨፈን አንችልም” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አስጠንቅቀዋል። “ይልቁኑ ጥልቅ መንስኤዎቻቸውን ለመለየት መጣር አለብን” ያሉ ሲሆን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውልኾት)፣ “ቴክኒካዊ፣ መደበኛ እና ደረጃውን የጠበቀ እውቀት” እንዳለው ለይተን ማወቅ ይኖርብናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፣ “ቴክኒካዊ፣ መደበኛ እና ደረጃውን የጠበቀ እውቀት”፣ አስቀድሞ የተገለሉ ተማሪዎችን የበለጠ የማግለል አደጋ ላይ ይጥላል፣ ይህም ሌሎች አያስፈልጋቸውም - ወይም የከፋው ለእነሱ ብቁ እንዳልሆኑ ያስባል" ሲሉ እውቀትን መርምረን መቀበል እንደሚገባን ገልጸዋል።
በዚህ አውድ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት፣ የአስተማሪው ሚና የሰው ልጅ ተሳትፎ ነው -- “እና የትምህርት ሂደቱ ደስታ ጥልቅ ሰብዓዊነት ነው፣ ነፍሳትን አንድ ላይ የሚያጣምር እና አንድ የሚያደርጋቸው ነበልባል” ነው ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።
