ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ ለጦርነት ሰለባዎች ጸልዩ፣ የማያንማርን ሕዝብ አትርሱ ማለታቸው ተገለጸ! ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ ለጦርነት ሰለባዎች ጸልዩ፣ የማያንማርን ሕዝብ አትርሱ ማለታቸው ተገለጸ!  (A)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ ለጦርነት ሰለባዎች ጸልዩ፣ የማያንማርን ሕዝብ አትርሱ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ምእመናን በጦርነት ውስጥ ባሉ አገሮች ለሚሰቃዩ ሰዎች እንዲጸልዩ፣ በተለይም ለዓመታት በእርስ በርስ ግጭት እና ውስጣዊ አለመረጋጋት ለወደመችው ማያንማር እንዲጸልዩ ምዕመናን እና በጎ ፈቃድ ያላቸውን ሁሉ መጋበዛቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ረቡዕ ዕለት ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም በተካሄደው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መደምደሚያ ላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በዓለም ላይ በብዙ የትጥቅ ግጭቶች መካከል እየተሰቃዩ ወደ ሚገኙ ሰዎች ሀሳባቸውን በማዞር ጸሎት እና ልዩ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ቅዱስነታቸው ጥር አቅርበዋል።

"በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በጦርነት ዓመፅ ለሚፈተኑ ሁሉ በጸሎት ከእኔ ጋር እንድትተባበሩ እጋብዛችኋለሁ" ብለዋል። በተለይም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለማያንማር ሕዝብ ጸልየዋል፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ "የበርማ ሕዝብን እንዳይረሱ እና አስፈላጊውን የሰብአዊ እርዳታ እንዲሰጡ" አሳስበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለማያንማር የጸለዩት ጸሎት አገሪቱ በዓለም ላይ ካሉት እጅግ የከፋ የሰብአዊ ቀውስ አንዱ እየገጠማት ባለበት በአሁን ወቅት ነው። ወታደራዊው ጁንታ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን መንግሥት በገለበጠ መፈንቅለ መንግሥት ስልጣን ከተቆጣጠረ ከአምስት ዓመታት ገደማ በኋላ፣ የእርስ በርስ ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሞት እና ሦስት ሚሊዮን ተጨማሪ ሰዎችን መፈናቀል አስከትሏል።

እ.አ.አ በ2021 ዓ.ም በተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ላይ በተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ የተጀመረው ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና በጎሳ የታጠቁ ቡድኖች መካከል በወታደራዊው ጁንታ ላይ ወደ ኃይለኛ ግጭት ተለወጠ።

መላው መንደሮች በአየር ድብደባ እና በውጊያ ወድመዋል፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ምግብ፣ መድኃኒት እና መጠለያ በበቂ ሁኔታ አያገኙም። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከግማሽ በላይ የሚሆነው የማያንማር ህዝብ አሁን የሰብአዊ እርዳታ እንደሚፈልግ ገምቷል።

የሮሂንጊያ ቀውስ

ሆኖም፣ በማያንማር የተከሰተው አስከፊ ሁኔታ የተጀመረው እ.አ.አ ከ2021 ዓ.ም መፈንቅለ መንግሥት በፊት ነበር። በወታደራዊ ኃይል የተወገደው የሲቪል መንግስት የሮሂንጊያ ሕዝቦች ቀውስን ባለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ ውግዘት ደርሶበታል፣ በዚህ ወቅት የሙስሊም እምነት ተከታይ በቁጥር አናሳ አባላት ለከፍተኛ እና ስልታዊ ጥቃት ተዳርገዋል።

የማያንማር ጦር ዘመቻውን እ.አ.አ በነሐሴ 2017 ዓ.ም ሲጀምር፣ ሰፊ ግድያዎችን፣ የጾታ ጥቃትን፣ ማሰቃየትን እና ሙሉ መንደሮችን ማጥፋትን ያካተተ ጥቃት መፈጸሙ ይታወሳል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የማያንማር የእውነታ ፍለጋ ተልዕኮ የጦር ሰራዊቱን እርምጃ “በዘር ማጥፋት ዓላማ” የተፈፀመ እንደሆነ ገልጿል።

እ.አ.አ በ2018 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ከ700,000 በላይ ሮሂንጊያ ጎሳ ሕዝቦች ወደ ጎረቤት ባንግላዲሽ ሸሽተው ከቀደምት የስደት ማዕበሎች ከተፈናቀሉት ጋር ተቀላቅለዋል። በማያንማር ራኪን ግዛት ውስጥ የቀን የእንቅስቃሴ ገደብ፣ በዜግነት መብት ተጠቃሚነት ገደብ መከልከል እና በአፓርታይድ መሰል ሁኔታዎች ውስጥ በሚኖሩበት ሁኔታ ላይ ከባድ ገደቦች እያጋጠሟቸው ነው።

ይህ ጥቃት በዋነኝነት የተፈፀመው እ.አ.አ በ2021 ዓ.ም በኋላ ስልጣን በያዘው ተመሳሳይ ወታደራዊ ኃይል ነው። ሆኖም በወቅቱ የሲቪል መንግስት እርምጃ መውሰድ አልቻለም።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እነዚህን ድርጊቶች አውግዟል፣ ነገር ግን ተጠያቂ የሆኑት ጄኔራሎች ብዙም ግድ አልነበራቸውም። ከአራት ዓመታት በኋላ፣ እ.አ.አ በየካቲት 2021 ዓ.ም ፣ በሚን አውንግ ህላይንግ የሚመሩ ተመሳሳይ ጄኔራሎች - በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የአንግ ሳን ሱ ኪይን መንግስት በመገልበጥ መፈንቅለ መንግስት አካሂደዋል። የአገሪቷን የጸጥታ ቁጥጥር በፍጥነት እንደሚያጠናክሩ ጠብቀው ነበር። በምትኩ፣ ታይቶ የማይታወቅ የሀገር አቀፍ ተቃውሞ ማዕበል አስነስተዋል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ፣ ወታደራዊው ጦር በሮሂንጊያ ላይ የተጠቀመውን ተመሳሳይ አረመኔያዊ ዘዴዎችን ተጠቅሟል፣ በዚህ ጊዜ በሁሉም የማያንማር ህዝብ ላይ በተፈጸመው ጥቃት የተነሣ የማያንማር ሕዝብ፣ ከሁሉም ጎሳ እና እምነት የተውጣጡ፣ በተከታታይ ስርዓቶች ለዓመታት ጭቆና፣ መድልዎ እና ኪሳራ እየደረሰባቸው መሆኑ ይታወሳል።

 

06 Nov 2025, 13:37