ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ካርዲናል ዱካን 'የወንጌል ሰባኪ' ብለው እንደሚዘክሯቸው ገለጹ! ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ካርዲናል ዱካን 'የወንጌል ሰባኪ' ብለው እንደሚዘክሯቸው ገለጹ! 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ካርዲናል ዱካን 'የወንጌል ሰባኪ' ብለው እንደሚዘክሯቸው ገለጹ!

በቴሌግራም ባወጡት የሐዘን መግለጫ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ማክሰኞ ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም በ82 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን የፕራግ ሊቀ ጳጳስ የነበሩትን ሟቹን ካርዲናል ዶሚኒክ ዱካን፣ “የግል ነፃነታቸውን ነጥቀው ለክርስቶስ እና ለቤተክርስቲያን ባላቸው ታማኝነት ሳይደክሙ በስደት ጊዜ ያሳዩትን ድፍረት በአድናቆት አስታውሳለሁ” ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“በስደት ጊዜ ያሳዩትን ድፍረት በአድናቆት አስታውሳለሁ፣ የገዛ ነፃነታቸውን ነጥቀው ለክርስቶስ እና ለቤተክርስቲያን ባላቸው ታማኝነት ሳይታክቱ በመሥራታቸው አደንቃቸዋለሁ” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የቀድሞ የቼክ ሪፖብሊክ የፕራግ ሜትሮ ፖሊታን ሊቀ ጳጳስ የነበሩት የካርዲናል ዶሚኒክ ዱካ ህልፈተ ሕይወት ተከትሎ በተሌግራም ለአሁኑ የፕራግ ሊቀ ጳጳስ ጃን ግራውብነር በላኩት የሐዘን መልእክት ገልጸዋል።

እ.አ.አ በ2012 ዓ.ም በሊቀ ጳጳስ ቤኔዲክት 16ኛ ካርዲናል ሆነው የተሾሙት ካርዲናል የዶሚኒካን ማክሰኞ ዕለት ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም በፕራግ በ82 ዓመታቸው ከእዚህ አለም ድካም ማረፋቸው ተገልጿል።

የካርዲናሉን ሞት ሲሰሙ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቼክ ሪፐብሊክ ቤተክርስቲያን፣ በዶሚኒካን ማኅበር አባላቶቻቸው እንዲሁም “በእምነት የተቀረጸ እረኛ እና ደፋር የወንጌል ሰባኪ ላገኙት ካህናት፣ ገዳማዊያን/ዊያት እና ምዕመናን ያላቸውን ቅርበት" ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ "በአባት ልብ የእግዚአብሔርን ሕዝብ መርተዋል፣ እርቅን፣ የሃይማኖት ነፃነትን እና በእምነት እና በኅብረተሰቡ መካከል ውይይትን ያበረታቱ ነበር" ሲሉ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

የሟቹ ካርዲናል የጵጵስና አገልግሎት፣ በዶሚኒካን የእውነት እና የበጎ አድራጎት ቸርነት ላይ የተመሰረተው - በላቲን ቋንቋ "In Spiritu e Veritatis" (በመንፈስ እና እውነት፥ "በመንፈስና በእውነት" ማለት እግዚአብሔርን በእውነተኛና ውስጣዊ መንገድ ማምለክ ማለት ነው፣ ከውጫዊ ቦታዎች ወይም ሥርዓቶች ጋር የተሳሰረ ሳይሆን፣ ከእርሱ ጋር በግልና በጥልቅ ግንኙነት ፈጥሮ መኖር ማለት ነው። በፍቅር፣ በአክብሮት በመገዛት እና ራስን በመንፈስ እንዲመራ በመፍቀድ፣ ከውጫዊ ሥነ ሥርዓት አልፎ መሄድ ማለት ነው) ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አጥብቀው እንደተናገሩት ይህ መፈክር እንደሚያስታውሰን ፣ ለተልእኮው ታማኝ ቁርጠኝነት ምሳሌ ሆኖ መቀጠላቸውን ነው ብለዋል።

በካርዲናል ዱካ ህልፈተ ሕይወት ለሚያዝኑ እና በቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ላይ ለሚሳተፉ ሁሉ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ከመስጠታቸው በፊት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ "የእኝህን ደግ እና ለጋስ አገልጋይ ነፍስ ለመለኮታዊ ምሕረት" አደራ ሰጥተዋል። እግዚአብሔር "ወደ መንግሥቱ ደስታ እንዲቀበላቸው" ከጸለዩ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

07 Nov 2025, 14:57