ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአዚዚ የቅዱስ ፍራንችስኮስ መካነ መቃብር ጎብኝተዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአዚዚ የቅዱስ ፍራንችስኮስ መካነ መቃብር ጎብኝተዋል  (@Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአዚዚ የቅዱስ ፍራንችስኮስ መካነ መቃብር ጎብኝተዋል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአዚዚ እየተካሄደ ባለው 81ኛው የጣሊያን ጳጳሳት ጉባኤ ስብሰባ ማብቂያ ላይ ለመገኘት በሕዳር 11/2018 ዓ.ም ወደ እዚያው ማቅናታቸው የተገለጸ ሲሆን በሥፍራው እንደ ደረሱም የቅዱስ ፍራንችስኮስ መቃብርን ጎብኝተዋል፣ ይህ ጉብኝት "ዓለም የተስፋ ምልክቶችን በሚፈልግበት ወቅት" አስፈላጊ ነው ሲሉ አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"ዛሬ ወደዚህ ቅዱስ ሥፍራ መምጣት በመቻሌ በረከት ነው። ቅዱስ ፍራንችስኮስ ከእዚህ አለም በሞት የተለየበትን  800ኛ ዓመት የዝክር ቀን እየተቃረብን ስንመጣ፣ ዓለም የተስፋ ምልክቶችን በሚፈልግበት ወቅት ይህንን ታላቅ፣ ትሑት እና ምስኪን ቅዱስ ለማክበር የመዘጋጀት እድል አለን" ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

እነዚህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቅዱስ ፍራንችስኮስ ዘ አዚዚ መካነ መቃብር ፊት ለፊት ቆመው ወደ አዚዚ ሲሄዱ የተናገሯቸው የመጀመሪያዎቹ ይፋዊ ንግግሮች ነበሩ።

ይህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ማዕከላዊ የጣሊያን ከተማን ሲጎበኙ የመጀመሪያው ሥፍራ ነበር፣ በህዳር 11/2018 ዓ.ም 81ኛው ጠቅላላ ጉባኤያቸው ሲጠናቀቅ ከጣሊያን ጳጳሳት ጉባኤ አባላት ተገናኝተው ነበር።

ወደ አዚዚ ሲደርሱ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሕዳር 11/2018 ዓ.ም ጠዋት በሄሊኮፕተር ወደ አዚዚ አቅንተው የነበረ ሲሆን ወደ የቅዱስ ፍራንችስኮስ ከተማ - የኪነጥበብ፣ የታሪክ፣ የባህል እና የአምልኮ ማዕከል እና ለዘመናት ሃያ ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናን መዳረሻ በድጋሚ ጎብኝተዋል፣ በተለይም የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጣሊያነኛ ቋንቋ 'ፍራቴሊ ቱቲ' የተሰኘውን ታሪካዊውን ጳጳሳዊ መልእክት እ.አ.አ በ2020 ዓ.ም  ለመፈረም በእዚያው ሥፍራ መገኘታቸው ይታወሳል።

በታችኛው ባሲሊካ ሞቅ ያለ አቀባበል

ይህ ጊዜ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ጉብኝት የማድረግያ ተራ ነው። ከጳጳሳቱ ጋር ለመገናኘት ወደ ቅድስት ማሪያ ዴሊ አንጀሊ ባሲሊካ ከመሄዳቸው በፊት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በአከባቢው የሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 8፡30 በኋላ የጣሊያን ጠባቂ ቅዱስ ወደሆነው ወደ ቅዱስ ፍራንችስኮስ መካነ መቃብር አመሩ።

ቋሚ ዝናብ እና ኃይለኛ ቅዝቃዜ ቢኖርም፣ ጥቂት ሰዎች በአደባባዩ ላይ “ቪቫ ኢል ፓፓ!” ወይም “ሊቀ ጳጳሱ ለዘላለም ይኑር!” እያሉ ሞቅ ያለ አቀባበል አድርገውላቸው ነበር።

ከመካነ መቃብሩ በፊት የተደረገ ጸሎት

እዚያ፣ የቅዱሱን መካነ መቃብር በቀጥታ በባሲሊካው ከፍተኛ መሠዊያ ስር ከሚይዙት ጥንታዊ የድንጋይ ግድግዳዎች ፊት ለፊት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለተወሰነ  ጸጥታ እና ጸሎት ጊዜ ቆም ማለታቸው ተገልጿል። ከዚያም ለአጭር ጊዜ ተናገሩ - ቃላቶቻቸው በውጭ ድምጽ ማጉያዎች ተሰራጭተዋል - ይህ ትንሽ ግን ግዙፍ ሰው ለዘመናት ለቤተክርስቲያኗ እና ለዓለም ለማቅረብ እንደሚቀጥል የተስፋ መልእክት እንደገና አረጋገጡ።

በቅድስት ኪያራ ገዳም ለመስዋዕተ ቅዳሴ እና ለምሳ በሄዱበት በአዚዚ አቅራቢያ በሚገኘው ሞንቴፋልኮ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ወደ መካነ መቃብሩ በሄዱበት ወቅት "ለሰላም" ለሁሉም  ምእመናን ጸልየዋል።

"በብዙ ቅዱሳን ምድር ላይ ነኝ" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተናግረዋል። "ዛሬ ጠዋት በአዚዚ እና ከዚያም እዚህ በሞንቴፋልኮ በመሆኔ በጣም ደስተኛ ነኝ ... የቅድስና ድባብ አለ" ሲሉ መናገራቸው ተገልጿል።

 

21 Nov 2025, 15:36