ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በጣሊያን በሚገኘው የቅዱስ አጎስጢኖስ  ገዳማት ፌዴሬሽን መደበኛ ጉባኤ አባላት ገር በተገናኙበት ወቅት  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በጣሊያን በሚገኘው የቅዱስ አጎስጢኖስ ገዳማት ፌዴሬሽን መደበኛ ጉባኤ አባላት ገር በተገናኙበት ወቅት   (@VATICAN MEDIA)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ እውነተኛ ደስታ የሚገኘው ከክርስቶስ ጋር ባለው ኅብረት ነው ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከቅዱስ አጎስጢኖስ ማሕበር አባላት ደናግላን ጋር ተገናኝተው እርስ በርስ ትሑት የሆነ ቸርነት እና ፍቅር እንዲኖራቸው እና ከክርስቶስ ጋር በደስታና በኅብረት እንዲኖሩ አበረታቷቸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐሙስ ዕለት ሕዳር 04/2018 ዓ.ም በጣሊያን በሚገኘው የቅዱስ አጎስጢኖስ  ገዳማት ፌዴሬሽን መደበኛ ጉባኤ ላይ ከተሳተፉት ጋር በቫቲካን ተገናኝተዋል።

በንግግራቸው፣ የቅዱስ አጎስጢኖስ ማሕበር ገዳማዊያት ፌዴሬሽኑን የሚያዋቅሩት እና በቅዱስ አውግስጢኖስ ሕግ መሠረት ለመኖር በገቡት ቃል የተሳሰሩ የተለያዩ የገዳማዊ እውነታዎች የሚያቀርቡትን የኅብረት ምስክርነት አድንቀዋል።

በመላው ጣሊያን ውስጥ ራሳቸውን ችለው በሚኖሩ ገዳማት ውስጥ የሚኖሩ ገዳማዊያት የጋራ ፍቅራቸውን ለመቃኘት ስለሚሰበሰቡ የድርጅቱን የሲኖዶሳዊ ገጽታ ጠቁመዋል። እርስ በርስ መደማመጥ እና በልዩነት መኖር፣ “በተለይም በብዙ መንገዶች ለመነጋገርና ለመጋራት ክፍት እየሆነ ባለ ዓለም ውስጥ የሚያስፈልግ የበጎ አድራጎት ትንቢታዊ ምስክርነት” እንደሚሰጡ አክለው ገልጸዋል። ከዚያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ እንደ ማሰላሰል ባሉ የቅዱስ አጎስጢኖስ ሃይማኖታዊ ተልእኮ ሦስት ገጽታዎች ላይ አተኩረዋል።

በፍቅር በጌታ መደሰት እውነተኛ ደስታን እንደሚያመጣ የቅዱስ አውጉስጢኖስን ማረጋገጫ በመጥቀስ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን የአንድነት ደስታ እንዲኖሩና እንዲመሰክሩ አበረታቷቸዋል። “ለሰው ልጅ፣ በተለይም ለክርስቲያን፣ እውነተኛ ደስታ የሚገኘው ከጌታ ጋር ባለው ኅብረት ነው - በሙሽራው አማካኝነት ሙሉ ህይወታችሁን የምትሰጡት ከሰማያዊው ሙሽራ ጋር ባለው ቅርበት ነው” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ በአምልኮ፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ በማሰላሰል እና በኅብረት ሕይወት ውስጥ የጋራ እርዳታ እንዲያደርጉ፣ ራሳቸውን በሙሉ ልብ ለተዘጋ ሕይወት እንዲሰጡ ጋብዛቸው። “ይህ ሰላምንና መጽናኛን ያመጣላችዋል፣ እናም ወደ ገዳማቶቻችሁ ደጆች ለሚመጡት፣ ከአንድ ሺህ ቃላት በላይ አንደበተ ርቱዕ የተስፋ መልእክት ያስገኝላችኋል” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ማሰላሰል ለቤተክርስቲያን እና ለዓለም የሚያቀርበውን የበጎ አድራጎት ምስክርነት አጉልተው የጠቀሱ ሲሆን የቅዱስ አውጉስጢኖስን ሀሳብ በመኖር፣ “የእግዚአብሔርን መልካም መዓዛ በዓለም ላይ” ያሰራጫሉ እና በጸሎት ጸጥታ ውስጥ የተደበቁትን እያንዳንዱን ወንድና ሴት ለመውደድ ይጥራሉ" ሲሉ ተናግረዋል።

“ያለ ጫጫታ ወይም ታይታ፣ እርስ በርሳችሁ እንክብካቤና ትኩረት አድርጉ፣ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜና ሁኔታ በሚፈቅድበት ቦታ ሁሉ ለሁሉም የርኅራኄ ምሳሌ ሁኑ” ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

“ዝም ያለውና የተደበቀ ፍቅራቸው” ማህበረሰባችን በመልክ ላይ በጣም ትኩረት እንዲያደርግ ስለሚያደርግ ለትሑት፣ ለዕለታዊ ምጽዋት ትልቅ ዋጋ አለው" ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በተለያዩ አባል ገዳሞቻቸው መካከል የቢሮዎችን፣ የሥራ፣ የፋይናንስ እና አንዳንድ ጊዜ ሃይማኖታዊ ስርጭትን ለማስተባበር የቅዱስ አጎስጢኖስን ፌዴሬሽንን ሥራ ደግፈዋል፣ አበረታተዋል።

“ቅዱስ አውጉስጢኖስ የተናገሩትን እናስታውስ” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የገለጹ ሲሆን “የምትፈልጉት ነገር ውብ ነው፣ እናም ለመወደድ እጅግ የተገባ ነው… ይህ ጉጉት ሥርዓትን እንድትቀበሉ ይምራችሁ፣ ምክንያቱም ያለ ሥርዓት አንድ ሰው በጣም የሚወደውን ነገር ማግኘት አይችልም” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን ደምድመዋል።

14 Nov 2025, 15:19