ር.ሊ.ጳ ሊዮ ለጣሊያን ጳጳሳት፡ በተሰነጣጠቀው ዓለማችን የሰላም ነቢያት ሁኑ ማለታቸው ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
መጀመሪያ ወደ ኢየሱስ እንድንመለከት ተጠርተናል፣ እናም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ክርስቶስን በተግባራችን መዕከል ላይ ማስቀመጥ አለብን ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐሙስ ህዳር 11/2018 ዓ.ም በቅድስት ማሪያ ዴሊ አንጀሊ ባሲሊካ ውስጥ 81ኛው የጣሊያን ጳጳሳት ጉባኤ (CEI) ማጠቃለያ ላይ በተከናወነው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ለመገኘት ወደ አዚዚ ባደረጉት የአንድ ቀን ጉዞ ለጣሊያን ጳጳሳት ባደረጉት ንግግር ይህንን ነጥብ አጥብቀው ተናግረዋል።
ከህዳር 8 እስከ ሕዳር 11/2018 ዓ.ም የተካሄደው የአራት ቀናት ስብሰባ፣ ከመላው ጣሊያን የተውጣጡ ጳጳሳትን በሐዋርያዊ ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች፣ በመጠበቅ እና በካቶሊክ ትምህርት ላይ እንዲያሰላስሉ አሰባስበው ነበር። ውይይቶቻቸው በቅርቡ በጣሊያን ከተካሄደው የሲኖዶሳዊነት መንገድ ግንዛቤዎች የመነጩ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት እ.አ.አ በመጪው በግንቦት 2026 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ሀዋርያዊ መመሪያዎች በማጽደቅ ይጠናቀቃል።
ርዕሰ ሊቀ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ለጣሊያን ጳጳሳት ባደረጉት ንግግር፣ በአዚዚ በመገኘታቸው “ለአጭር ጊዜ” እንኳን “ዓለም አስቸኳይ ፍላጎት ላለው የእምነት፣ የወንድማማችነት እና የሰላም መልእክት እጅግ አስፈላጊ ቦታ” በመሆኑ ደስታቸውን ገልጸዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ የአዚዚውን የቅዱስ ፍራንችስኮን ደፋር እና ጽኑ እምነት አስታውሰው፣ እንዲሁም የእሱ ምሳሌ የጣሊያን ጳጳሳት “በእውነተኛ እምነት ተመስጦ ምርጫዎችን ለማድረግ ጥንካሬ...” እንዲሰጣቸው ጸልየዋል።
ወደ ኢየሱስ እንዲመለከቱ ተጠርተዋል
ርዕሰ ሊቀ ጳጳስ ሊዮ ለጣሊያን ጳጳሳት ጉባኤ አባላት የሰጡት ዋና ምክረ ሃሳብ ክርስቶስን መከተል እና በእርሱ መመራት የሚል ሐሳብ ነበር። “ወደ ኢየሱስ መመልከት” ላይ አፅንዖት ሲሰጡ፣ “እኛም የተጠራንበት የመጀመሪያው ነገር ነው፣ እዚህ የመኖራችን ምክንያት፣ እንዲያውም፣ በእርሱ ላይ በተሰቀለው እና ከሙታን በተነሣ፣ በእርሱ ላይ ያለን እምነት ነው” ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
“ኢየሱስን መመልከት የተጠራንበት የመጀመሪያው ነገር ነው። እዚህ የመኖራችን ምክንያት በእርሱ ላይ ያለን እምነት ነው...” ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሰኔ ወር የተናገሩትን ቃላቶቻቸውን በድጋሚ በማደስ “በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስን በማዕከል ውስጥ ማስቀመጥ እና ሰዎች ከእርሱ ጋር የግል ግንኙነት እንዲኖራቸው፣ የወንጌልን ደስታ እንዲያገኙ መርዳት ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ ነው” ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን “በታላቅ መከፋፈል” ወቅት፣ ወደ እምነታችን መሠረት፣ ወደ ቅዱስ ወንጌልን ማብሰር መመለስ አስፈላጊ መሆኑን አጥብቀው ተናግረዋል። “ይህ ከሁሉም በፊት ይሠራል፡ አዳኝ ክርስቶስን እንድናውቅ ከሚያደርገን እና በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ በሚገለጠው የእምነት ተግባር እንደገና መጀመር ያስፈልጋል” ያሉ ሲሆን ዓይናቸውን በኢየሱስ ፊት ላይ ማቆየት፣ የወንድሞቻችንን እና የእህቶቻችንን ፊት ማየት እንድንችል ያደርገናል ብለዋል።
“ወደ እነሱ የሚመራን የእርሱ ፍቅር ነው” በእርሱ ላይ ያለን እምነት፣ ሰላማችን፣ "የሰላሙን ስጦታ ሁሉ እንድናቀርብ ይጠይቀናል" ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ።
የጌታን ሰላም ማስተላለፍ አለብን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በብሔራዊ እና በዓለም አቀፍ አውዶች "በስብራት በተሞላበት" ዘመን ውስጥ እንደምንኖር የገለጹ ሲሆን "ለጠላትነት እና ለዓመፅ የተቀየሱ መልዕክቶች እና ቋንቋዎች ብዙውን ጊዜ ይሰራጫሉ፤ ወደ ስኬት የሚደረገው ሩጫ በጣም ደካማውን ወደ ኋላ ይተዋል፤ የቴክኖሎጂ ሁሉን ቻይነት ነፃነትን ያጨናንቃል፤ ብቸኝነት ተስፋን ይበላል፣ ብዙ እርግጠኛ ያልሆኑ ነገሮች ግን እንደማይታወቁ ነገሮች በወደፊት ኑሮዋችን ላይ ያመዝናሉ ሲሉ ተናግረዋል።
"ሆኖም ግን ቃልና መንፈስ አሁንም በማህበረሰቦቻችን ውስጥ የወዳጅነት፣ የወንድማማችነት፣ የእውነተኛ ግንኙነቶች የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች እንድንሆን ያሳስቡናል፣ ያለ ምንም ቸልተኝነትና ፍርሃት፣ ውጥረትን ማዳመጥና ማስማማት፣ የመገናኘት ባህል ማዳበርና በዚህም ለዓለም የሰላም ነቢያት መሆን አለብን" ብለዋል።
ሊቀ ጳጳሱ ከሙታን የተነሣው ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥ፣ የመጀመሪያ ቃላቱ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" የሚለው እንደሆነ የገለጹ ሲሆን ይህ ቃል ለሁሉም እንዴት ገቢራዊ እንደሚሆን አስታውሰዋል።
ለምዕመናን እንክብካቤ ለማድረግ የተሰጡ ምክሮች
ርዕሰ ሊቀ ጳጳሱ በሰኔ ወር ለጳጳሳት ባደረጉት ንግግር፣ "ወንጌልን የሚያካትት እና የእግዚአብሔርን መንግሥት ምልክት የሆነች ቤተክርስቲያን ለመሆን አንዳንድ አጋጣሚዎችን አመልክተዋል"፤ እነሱም "የመዳንን መልእክት ማወጅ፣ ሰላምን መገንባት፣ የሰውን ክብር ማሳደግ፣ የውይይት ባህል እና የክርስቲያን ስነ-ሰብዕአዊ ራዕይ" እንደሆኑ አስታውሰዋል። ስለዚህ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እነዚህ ጥያቄዎች በጣሊያን በሚገኘው የቤተክርስቲያን ሲኖዶሳዊ መንገድ ውስጥ ከተከሰቱት አመለካከቶች ጋር የሚስማሙ" መሆናቸውን ለማጉላት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
«እናንተ ጳጳሳት ለሚመጡት ዓመታት ሐዋርያዊ መስመሮችን መከተል አለባችሁ»፣ እናም በዚህ ምክንያት፣ «በጣሊያን ቤተክርስቲያን ውስጥ እውነተኛ የሲኖዶሳዊ መንፈስ እንዲያድግና እንዲበስል ለመርዳት» አንዳንድ ሀሳቦችን ማቅረብ እንደሚፈልጉ ተናግሯል።
ሲኖዶሳዊነት ክርስቲያኖችን ከክርስቶስ ጋር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚሄዱበትን ሁኔታ ያካትታል ያሉት ቅዱስነታቸው "በመጀመሪያ" ሲኖዶሳዊነት የሚያመለክተው ክርስቲያኖች ከክርስቶስ ጋር አብረው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ንዲጓዙ፣ ከሁሉም የሰው ልጆች ጋር አንድነት እንዲኖራቸው የምያደርግ መሆኑን አንርሳ" ብለዋል።
ለሰብዓዊ እና ለቤተክርስቲያን ግንኙነቶቻችን ሕያው እና ቅርፅ የሚሰጥ የኅብረት ጸጋን እንቀበላለን ያሉት ቅዱስነታቸው "ውጤታማ በሆነ የኅብረት ፈተና ላይ፣ የሁሉም ሰው ቁርጠኝነት እንዲኖር እፈልጋለሁ፣ ይህም የቤተክርስቲያን ሕብረት ቅርፅ እንዲኖረው፣ የጋራ እርምጃዎችን እና ምርጫዎችን የሚጋራ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
"ዋናው ነገር በዚህ የሲኖዶሳዊ ዘይቤ ውስጥ አብረን መሥራትን እንማራለን፣ እናም በተወሰኑ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ሁላችንም ክፍት እና እንግዳ ተቀባይ የሆኑ የክርስቲያን ማህበረሰቦችን ለመገንባት እራሳችንን መስጠታችን ነው፣ በዚህ ውስጥ ግንኙነቶች የወንጌልን አዋጅ በመደገፍ ወደ የጋራ ኃላፊነትን ይለውጣሉ" ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
ከቤተሰቦች፣ ከአረጋውያን፣ ከድሆች ጋር ተቀራርባችሁ ሥሩ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ውጤታማ የሆነ የእረኝነት እንክብካቤ አስፈላጊነትን ሲናገሩ "አብረን መጓዝ፣ ከሁሉም ጋር መሄድ፣ በሕዝቡ መካከል የምትኖር፣ ጥያቄዎቻቸውን የምትቀበል፣ ስቃያቸውን የምታረጋጋ፣ ተስፋቸውን የምትጋራ ቤተክርስቲያን መሆን ማለት ነው" ብለዋል።
"ከቤተሰቦች፣ ከወጣቶች፣ ከአረጋውያን፣ በብቸኝነት ከሚኖሩ ጋር በቅርበት መጓዛችሁን ቀጥሉ" ያሉት ቅዱስነታቸው "ለድሆች እንክብካቤ እራሳችሁን አደራ መስጠታችሁን ቀጥሉ" ሲሉ አበረታተዋል።
"ከቤተሰቦች፣ ከወጣቶች፣ ከአረጋውያን፣ ብቻቸውን ለሚኖሩ ሰዎች ቅርብ መሆናችሁን ቀጥሉ። ለድሆች እንክብካቤ እራሳችሁን አደራ መስጠታችሁን ቀጥሉ" ያሉት ቅዱስነታቸው በተጨማሪም ጳጳሳት ሁሉንም ዓይነት በደል የመከላከል ባህል እንዲያዳብሩ ከትንንሽ እና በጣም ተጋላጭ ከሆኑ ሰዎች ጋር እንዲቀራረቡ ጥሪ አቅርበዋል።
"ተጎጂዎችን መቀበል እና ማዳመጥ በማህበረሰብ ለውጥ ውስጥ ቁስሎችን እንዴት መለየት እንደሚችል የሚያውቅ እና እነሱን ለማረጋጋት የሚተጋ የቤተክርስቲያን እውነተኛ ባህሪ ነው" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዚህ ረገድ እስካሁን ላደረጉት ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል እና ለአካለ መጠን ያልደረሱ እና ተጋላጭ የሆኑትን ለመጠበቅ ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲቀጥሉ አበረታተዋል።
ከጣሊያን ጳጳሳት ጉባኤ "CEI" ጋር በተደረገው ስብሰባ መጨረሻ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ወደ ቅድስት ማሪያ ዴሊ አንጀሊ ገዳም የሄዱ ሲሆን ከዚያም ወደ ሞንቴፋልኮ ተጓዙ፣ እዚያም በቅዱስ አጎስጢኖስ ሴት መነኮሳት ገዳም ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴ ያሳረጉ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከምሣ በኋላ በሄሊኮፕተር ወደ ቫቲካን መመለሳቸው ተገልጿል።
