ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ የቫቲካን ዲፕሎማቶች ሰላም በሌለበት ሥፍራ ተስፋን እንዲያመጡ አሳሰቡ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ሰኞ ኅዳር 9/2018 ዓ. ም. ከቫቲካን ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጽሕፈት ቤቶች ወይም ኤምባሲዎች ሠራተኞች ጋር የተገናኙ ሲሆን፥ ዲፕሎማቶቹ እንደ ሌሎች በርካታ መንፈሳዊ ነጋዲያ ወደ ሮም እና ወደ ሐዋርያውቅዱስ ጴጥሮስ መካነ መቃብር የሚመጡት እምነታቸውን ለማጠናከር እና አገልግሎታቸውን ለማሳደግ ያላቸውን ዓላማ ለማደስ መሆኑን አስረድተዋል።
ወንጌልን ለዓለም ማወጅ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በንግግራቸው መጀመሪያ፥ ዲፕሎማቶቹ የወንጌልን የመዳን ቃል እስከ ምድር ዳርቻ ለማድረስ ሲሉ አገራቸውን ትተው በመሄዳቸው አመስግነዋቸዋል።
የክህነት አገልግሎታቸውን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መለማመድ ማለት የቤተ ክርስቲያኗን በሁሉም ቦታ መገኘት በተለይም የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን የሐዋርያዊ እረኝነት ተልዕኮን መመስከር ማለት ነው” ብለዋል።
ቅዱስነታቸው በመልዕክታቸው፥ “በተለይም ግጭት እና ድህነት ባሉባቸው አስቸጋሪ አካባቢዎች የሚያገለግሉ ዲፕሎማቶችን ቤተ ክርስቲያን በጸሎት መደገፏን አስታውሱ” በማለት ዲፕሎማቶችን አበረታቷቸዋል።
“ጥንካሬያችሁን ከቅዱሳት ምስጢራት፣ ከወንድማማችነት ኅብረት እና ወደ መንፈስ ቅዱስ በመሳብ ክኅነታዊ ማንነታችሁን አጠናክሩ” ሲሉ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ድፕሎማቶችን አሳስበዋል።
ራስን በሕዝቦች እና በባሕሎች ውስጥ ማስገባት
“ራስን የማግለል ፈተናን ተቋቋሙት” በማለት ዲፕሎማቶችን የመከሩት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ በማሳሰብ፥ በሚኖሩበት እና በሚሠሩበት አውድ ውስጥ በወንጌል ዘይቤ ራስን እንዲያስገቡ አሳስበው፥ “አንድ ዛፍ በሌላ ቦታ ሊተከል እና አዲስ ፍሬን ሊያፈራ ይላችል” ሲሉ አስረድተዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በንግግራቸው ማጠቃለያ፥ እያንዳንዱ መኖሪያ ቤታቸው ጨለማን እና ጭንቀቶችን የሚያስወግድ፣ ለሚጓዙበት መንገድ ብርሃን መስጠት የሚችል እውነተኛ ማዕከል የሆነው ጸሎት ቤት ያለው መሆኑን አስታውሰዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በመጨረሻም፥ በዓለም ዙሪያ በሐዋርያዊ አገልግሎት ላይ የሚገኙ የቫቲካን ዲፕሎማሲ ሠራተኞች ይህን ጸጋ አጥብቀህ እንዲይዙት በማሳሰብ በተለይም ፍትህ እና ሰላም በሌሉባቸው አካባቢዎች ለሚኖሩት ሕዝቦች የተስፋ ነጋዲያን እንዲሆኑ አደራ ብለዋል።
