ፈልግ

የቱርክ ሐዋርያዊ ጉዞ - የሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ጉብኝት የቱርክ ሐዋርያዊ ጉዞ - የሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ጉብኝት  (@Vatican Media)

ቱርክ በጳጳሳዊ ሐዋርያዊ ጉብኝቶች ጉዞዎች መልክአምድር ውስጥ ልዩ ቦታ ትይዛለች።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዩሐንስ 23ኛ በርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው ወደዚያ ማለትም ወደ ቱርክ አልተጓዘም ነበር፣ ነገር ግን እንደ ሐዋርያዊ ልዑክ ሆነው በኢስታንቡል (እ.አ.አ 1935-1944 ዓ.ም) ለአስር ዓመታት ያህል በቱርክ ኖረው አገልግለዋል፣ ከእዚያም የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ተረካቢ ሆነው ሲመተ ርዕሰ ሊቃነ ጵጵሳና በተሰጣቸው ወቅት በአንካራ ባለሥልጣናት ዘንድ የቅድስት መንበር ልዑክ ሆነው ለአስር አመታት በማገልገላቸው የተነሳ “በታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው የቱርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት” ተብለው ተጠርተው ነበር።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

አገሪቱ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ (እ.አ.አ 1967 ዓ.ም) አምስተኛው የጉዞ መዳረሻ ነበረች፣ እሱም በሌፓንቶ ጦርነት (እ.አ.አ 1571) ወቅት ከኦቶማን ጦር ባንዲራ ቅርጽ በተሰራው የአውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ተደርጎላቸው ነበር። ያ ሐዋርያዊ ጉዞ የጳጳስ ሞንቲኒ ወደ ቅድስት ምድር ጉዞ እና ከክርስቲያናዊ ሕብረት "ኤኩሜኒካል" ፓትርያርክ አቴናጎራስ ጋር በኢየሩሳሌም ባሳዩት ታሪካዊ አቀባበል ምክንያት ነበር። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ወደ ቱርክ የተጓዙት ሁለተኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት (እ.አ.አ 1979) ሲሆኑ፣ እዚያም ከኤኩሜኒካል ፓትርያርክ ዲሚትሪዮስ ቀዳማዊ ጋር ተገናኝተው ነበር። ከዚያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛ እ.አ.አ በ2006 ዓ.ም ያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት በታሪክ ውስጥ በአንድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ቱርክ የተደረ 5ኛ ሐዋርያዊ ጉብኝት ሲሆን የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ በ2014 ዓ.ም የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸውን 6ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ቱርክ እንደ ተጓዙ ይታወሳል፣  ሁልጊዜም በክርስቲያን ሕብረት "ኤኩሚኒዚም" ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ የተደርጉ ሐዋርያዊ ጉብኝቶች ቢሆኑም ከእስልምና እምነት ጋር በሚደረግ ውይይትም ጭምር ጠቃሚ የሆነ መግባባት እየፈጠረ መቀጠሉ ይታወቃል።

ስለዚህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፣ የኒቂያ የመጀመሪያው የክርስቲያኖች ሕብረት ጉባኤ የተከናወነበትን 1700ኛ የመታሰቢያ ዓመት ክብረ በዓል ምክንያት ቱርክን የጎበኙት የቅዱስ ጴጥሮስ አምስተኛው ተተኪ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ነበሩ። ቀደም ሲል ኒቂያ በመባል የሚታወቀው ኢዝኒክ በቡርሳ ግዛት ውስጥ በታሪክ እና በባህል የበለፀገች ከተማ ናት። እዚህ እ.አ.አ በ325 ዓ.ም የመጀመሪያው የኢኩሜኒካል (የክርስቲያኖች ሕብረት) ጉባኤ የተካሄደው በንጉሠ ነገሥት ቆስጠንጢኖስ ቀዳማዊ መሪነት ነበር። ይህ ዝግጅት በግምት 300 የሚሆኑ ጳጳሳትን ያቀፈ እንደ ነበረ በታሪክ የሚገለጽ ሲሆን፣ ከምስራቅ አገረ ግዛት ክፍል የመጡ፣  በተጨማሪም ከሌሎች ነገሮች ባሻገር ኢየሱስ ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የሚገልጸውን፣ "ከአብ ጋር የሚስማማ" እና የፋሲካን ቀን ወሳኝ ጥያቄን ጨምሮ፣ ከሲኖዶሳዊ እይታ አንፃር የተነሱ ሐሳቦች የተንሸራሸሩበት የመጀመርያ የክርስቲያኖች ሕብረት ጉባኤ ነበር። “የኒቂያ ጉባኤ ያለፈ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ወደ ሙሉ የክርስቲያኖች አንድነት የሚመራን ኮምፓስ ወይም አቅጣጫ መጠቆሚያ ነው። (…) ወደ ኒቂያ ጉባኤ በመመለስ እና ከዚህ የጋራ ምንጭ በመሰባሰብ፣ አሁንም የሚለያዩንን ነጥቦች በተለየ ብርሃን ማየት እንደምንችል እርግጠኛ ነኝ” (ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፣ ሰኔ 7፣ 2025 ለኒቂያ ጉባኤ1700ኛ የመታሰቢያ ዓመት ክብረ በዓል በተሰየመው የኢኩሜኒካል ሲምፖዚየም ላይ ለተሳታፊዎች ካደርጉት ንግግር የተወሰደ ነው)።

27 Nov 2025, 13:57