ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ‘በፀረ-ሴማዊ ጥቃት ይብቃ!’ ማለታቸው ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የኢየሱስ ልደት ትዕይንቶች እና የገና ዛፎች “የእምነት እና የተስፋ ምልክቶች” ናቸው ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሰኞ ዕለት ታኅሳስ 07/2018 ዓ.ም የታንገሩ ሲሆን ምእመናን “እግዚአብሔር የሰላም እና የወንድማማችነት ስጦታ በውስጣችን እንዲያድስልን” ጌታን እንዲጠይቁ ጋብዘዋል።
ቅዱስ አባታቸው በጦርነት እና በዓመፅ ምክንያት ለሚሰቃዩት ሁሉ፣ በተለይም እሁድ ዕለት በሲድኒ በሚገኘው የአይሁድ ማህበረሰብ ላይ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ሰለባ ለሆኑት፣ ለጌታ በአደራ ጸሎት አቅርበዋል።
“እነዚህን መሰል የፀረ-ሴማዊ ጥቃት ዓይነቶች በቃ!” ልንል ይገባል ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ተናግረዋል፣ “ጥላቻን ከልባችን ማስወገድ አለብን” ሲሉ አክለው ተናግረዋል።
የትሕትና እና የፍቅር ምስጢር
የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የተናገሩት ለቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የገና ዛፍ እና የልደት ትዕይንትን ለለገሱ ማህበረሰቦች ተወካዮች እና ሰኞ ታዳሚዎች በተገኙበት በጵውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ውስጥ በተቋቋመው የልደት ትዕይንት ላይ በተደረገ ስብሰባ ላይ ነው።
ከኔፕልስ ውጭ ከኖሴራ ኢንፌሪዮር-ሳርኖ ሀገረ ስብከት የተገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የሚገኘው የልደት ትዕይንት ከመላው ዓለም የመጡ ምዕመናንን “እግዚአብሔር ወደ ሰው ልጅ እንደሚቀርብ፣ ከእኛ አንዱ እንደሚሆን፣ እንደ ልጅ ልጅ ወደ ታሪካችን እንደሚገባ” ያስታውሳቸዋል ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተናግረዋል።
