ፈልግ

የእግዚአብሔር መገኘት ልምምድ የተሰኘው የወንድም ላውሬንስ መጽሐፍ የእግዚአብሔር መገኘት ልምምድ የተሰኘው የወንድም ላውሬንስ መጽሐፍ  

ር.ሊ.ጳ ሊዮ 'ወንድም ሎውረንስ በየቀኑ በእግዚአብሔር ፊት የመኖርን ደስታ ያስተምረናል' ማለታቸው ተ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን ማተሚያ ቤት (LEV) በተለቀቀ አዲስ የመጽሐፍ እትም ላይ በካርሜላይት ማሕበር ወንድም ላውረንስ የተጻፈውን “የእግዚአብሔር መገኘት ልምምድ” የተሰኘውን መጽሐፍ መግቢያ ጽፈዋል። በ17ኛው ክፈለ ዘመን በኖረው እና ትሑት በሆነ በፈረንሳዊው ሃይማኖተኛ የተጻፈው መጽሐፍ በቀድሞ ስማቸው አባ ሮበርት ፕሬቮስትን፣ ከዚያን በመቀጠል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የሆኑትን መንፈሳዊ ሕይወት ይዘረዝራል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው በመጽሐፉ መቅድም ላይ የሚከተለውን ሐሳብ ጽፈዋል።

ይህ ትንሽ መጽሐፍ በአሥራ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን የኖረው የካርሜላይት ማሕበር ወንድም ላውረንስ የትንሣኤ ተሞክሮ እና ትምህርት እንደተሰጠው የእግዚአብሔርን መገኘት ልምምድ፣ በእርግጥም ልምምድ - መሃል ላይ ያስቀምጣል።

ከዚህ ቀደም እንደ ተናገርኩት፣ ከቅዱስ አውጉስጢኖስ እና ከሌሎች መጻሐፍት ጽሑፎች ጋር፣ ይህ መንፈሳዊ ሕይወቴን በጣም ከቀረፁት እና ጌታን ለማወቅ እና ለመውደድ መንገዱ ምን ሊሆን እንደሚችል አዎንታዊ ተጽኖ ከፈጠሩብኝ ጽሑፎች አንዱ ነው።

ወንድም ላውረንስ የሚያሳየን መንገድ በተመሳሳይ ጊዜ ቀላል እና አድካሚ ነው። ቀላል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔርን ዘወትር ወደ አእምሮ ከመጥራት ሌላ ምንም ነገር አያስፈልገውም፣ በእያንዳንዱ ተግባር እና በእያንዳንዱ ሀሳብ ውስጥ በትንሽ፣ ቀጣይነት ባለው የምስጋና፣ የጸሎት፣ የልመና፣ የአምልኮ ተግባራት፣ እንደ አድማሳችን፣ ምንጭ እና መጀመርያችን እና መጨረሻችን እርሱ ብቻ እንደ ሆነ አድርገን አምነን ወደ ሕይወታችን እርሱን መጋበዝ ያስፈልገናል። አስቸጋሪ፣ ምክንያቱም የመንጻት፣ የባሕሪ ተግሣጽ፣ የመካድ (አላስፈላጊ ምቾቶችን መካድ) እና የመለወጥ ጉዞን ይጠይቃል - አእምሯችንን እና አስተሳሰባችንን በተግባራችን ላይ ተጽኖ አላቸውና።

ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ምእመናን የጻፈው ይህ ነው፡- “እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ያለ ተመሳሳይ ስሜት በእናንተ ውስጥ ይኑር” (ፊልጵስዩስ 2፡5)። ስለዚህ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መጣጣም ያለባቸው አመለካከቶቻችን እና ባህሪያቶቻችን ብቻ አይደሉም፣ ነገር ግን በትክክል ስሜቶቻችን - የእኛ የስሜት መንገድ። በዚህ ውስጣዊ ማንነት ውስጥ የእርሱን መገኘት፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እና የሚነድ መገኘት፣ በጣም “ሌላ” እና ለልባችን የታወቀ ሆኖ እናገኛለን። ቅዱስ አውጉስጢኖስ እንደጻፈው፣ “አዲሱ ሰው አዲሱን መዝሙር ይዘምራል” (ስብከቶች 34፣1)።

በወንድም ላውረንስ ገጾች ላይ ከእግዚአብሔር ጋር የመተባበር ተሞክሮ፣ ከግጭቶችና ውይይቶች፣ ከመደበቅና ከመገረም ጋር የተያያዘ የግል ግንኙነት እንደሆነ ተገልጿል፣ ይህም የታላላቅ መንፈሳዊ ሕይወት የሚኖሩ ሰዎች ተሞክሮዎችን ያስታውሳል - በመጀመሪያ ደረጃ የአቪላዋ ቅድስት ቴሬዛ፣ ከጌታ ጋር ያላትን ይህንን ትውውቅ እስከ “የማሶሮ እና ድስት አምላክ” ብላ እስከመናገር ድረስ መስክራለች። ሆኖም፣ ቀላልና የዕለት ተዕለት ነገር ስለሆነ ለሁሉም ተደራሽ የሆነ መንገድን ያመለክታል።

እንደ ብዙ መንፈሳዊ ሕይወት የሚኖሩ ሰዎች፣ ወንድም ላውረንስ በታላቅ ትህትና ብቻ ሳይሆን በቀልድም ጭምር ይናገራል፣ ምክንያቱም እያንዳንዱ ምድራዊ ነገር፣ እጅግ ታላቅም ቢሆን - እንደ ድራማዊም - ከጌታ ማለቂያ ከሌለው ፍቅር በፊት በጣም ትንሽ ነገር መሆኑን በሚገባ ያውቃል። ስለዚህ፣ እግዚአብሔር “አታለለው” ብሎ በምጸት መናገር ይችላል፣ ምክንያቱም ራሱን ለመስዋዕትነትና የወጣትነቱን ኃጢአት በድፍረት ለማስተሰረይ ወደ ገዳሙ ከገባ በኋላ፣ በዚያ ፈንታ በደስታ የተሞላ ሕይወት አገኘ። ወንድም ላውረንስ ባቀረበልን መንገድ፣ ቀስ በቀስ፣ የእግዚአብሔር መገኘት ሲታወቅና ውስጣዊ ቦታችንን ሲይዝ፣ ከእርሱ ጋር የመሆን ደስታ ያድጋል፣ ጸጋዎችና መንፈሳዊ ሀብት ይበቅላሉ፣ እና የዕለት ተዕለት ተግባራትም ቀላልና ምቹ ይሆናሉ።

የዚህ የቀርሜሎሳዊ ጽሑፍና ምስክርነት የአሥራ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን ወንድም ነበር፣ እሱም በብርሃን እምነት የኖረ፣ በክፍለ ዘመኑ በችግር ውስጥ የኖረ - በእርግጥም ከእኛ ያነሰ ዓመፅ - ለሦስተኛው ሺህ ክፍለ ዘመን ላለን ወንዶችና ሴቶች ሕይወት መነሳሻና እርዳታ ሊሆን ይችላል። ከእግዚአብሔር የሚለየን ምንም ዓይነት ሁኔታ እንደሌለ፣ የእኛ እያንዳንዱ ተግባር፣ እያንዳንዱ ሥራ እና እያንዳንዱ ስህተታችን እንኳን በእግዚአብሔር ፊት ዘወትር ለእርሱ ከቀረበ ማለቂያ የሌለው ዋጋ እንደሚያገኝ ያሳዩናል።

ሁሉም የክርስቲያን ሥነ ምግባሮች በእውነት በዚህ ቀጣይነት ባለው የማስታወስ ችሎታ ውስጥ ሊጠቃለሉ ይችላሉ፡ እግዚአብሔር እዚህ አለ። ይህ መታሰቢያ፣ ስሜታችንንና ፍቅራችንን ስለሚያካትት ከቀላል ትዝታ በላይ የሆነ ነገር ነው፣ እያንዳንዱን የሞራል ዝቅጠት እና ወንጌልን ወደ ተራ ደንቦች ዝቅ ማድረግን ያሸንፋል፣ እናም ኢየሱስ ቃል እንደገባልን፣ ራሳችንን ለእግዚአብሔር አብ አደራ የመስጠት ተሞክሮ ከዚህ በታች መቶ እጥፍ እንደሚሰጠን ያሳየናል። ራሳችንን ለእግዚአብሔር መገኘት አደራ መስጠት ማለት የገነትን ተስፋ መቅመስ ማለት ነው።

ቫቲካን - ታህሳስ 2 ቀን 2025 ዓ.ም.

19 Dec 2025, 13:17