ር.ሊ.ጳ ሊዮ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚካሄደው ዓመፅ እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል በተካሄደው አዲስ ግጭት "ጥልቅ ስጋታቸውን" ገልጸዋል። በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በተካሄደው የእሁድ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት መደምደሚያ ላይ ንግግር ሲያደርጉ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከሕዝቡ ጋር ያላቸውን ቅርበት ገልጸዋል እና በግጭቱ ውስጥ የተሳተፉት ወገኖች "ሁሉንም ዓይነት ዓመፅ እንዲያቆሙ እና ቀጣይነት ያለውን የሰላም ሂደት በማክበር ገንቢ ውይይት እንዲያደርጉ" አሳስበዋል።
በምስራቅ ኮንጎ በምትገኘው ኡቪራ፣ በምስራቅ ኮንጎ ጠቃሚ ከተማ፣ የክልል ባለስልጣናት ከ400 በላይ ሰዎችን የገደለ እና ሌሎች 200,000 ሰዎችን ያፈናቀለ አዲስ ገዳይ ጥቃት መፈጸሙን ሪፖርት አድርገዋል - ከተማዋ በሩዋንዳ የሚደገፈውን የM23 ቡድን እጅ ከወደቀች ከጥቂት ቀናት በኋላ የተፈጸመ ጥቃት ሲሆን ይህ የሆነው በቅርቡ በአሜሪካ አሸማጋይነት ከተካሄደው የሰላም ስምምነት በኋላ የተፈጸመ ጥቃት ነው።
ሲመተ ብፅዕና ያገኙ አዲስ ሰማዕታት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቀደመው ቀን በስፔን እና በፈረንሳይ ስለተከናወኑ ሁለት የምስጋና በዓላትም ተናግረዋል። በስፔን ጄኤን በመባል በሚታወቀው ሥፍራ አባ ኢማኑኤል ኢዝኪየርዶ እና ሃምሳ ስምንት ጓደኞቻቸው ከአባ አንቶኒዮ ሞንታኔስ ቺኬሮ ሰማዕት መሆናቸው እና ከስልሳ አራት ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን የሲመተ ብፅዕና ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ቅዱስ አባታችን እ.አ.አ ከ1936-38 ባለው የሃይማኖት ስደት ወቅት ሁሉም በእምነት ጥላቻ እንዴት እንደተገደሉ አስታውሰዋል።
ከዚያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አባ ሬይመንድ ኬሬ፣ የታናናሾች የቅዱስ ፍራችስኮስ ማሕበር አባል የሆኑት አባ ጄራርድ-ማርቲን ሴንድሪየር፣ ሴሚናሪ ሮጀር ቫሌ፣ ጂን ሜስትሬ እና በታህሳስ 13 በፓሪስ የሲመተ ብፅእዕና ማዕረግ የተሰጣቸውን አርባ ስድስት ጓደኞቻቸውን ጠቅሰዋል። እ.አ.አ በ1944-45 በናዚ ወረራ ወቅት በእምነት ጥላቻ የተነሳ ተገድለዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እነዚህን ሰማዕታት "ለወንጌል ደፋር ምስክሮች፣ ከሕዝባቸው ጋር በመቀራረባቸው እና ለቤተክርስቲያን ታማኝ በመሆናቸው ምክንያት የተሰደዱ እና የተገደሉ" በማለት ሁሉም ሰው ጌታን እንዲያወድሱ ጋብዘዋል።
